2012-07-04 14:08:47

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለበጋ ዕረፍት ወደ ካስተልጋንዶልፎ


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለበጋ ዕረፍት ወደ ካስተልጋንዶልፎ መሄዳቸው ያስታወቀው የቅድስት መንበር መግለጫ፣ ቅዱስነታቸው በዚህ የበጋው ዕረፍት ወቅት እሁድ እኩለ ቀን በይፋ ከሚያሳርጉት ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር በስተቀረ RealAudioMP3 ጠቅላላይ ሕዝባዊ መርሃ ግብሮች እንደማያከናውኑ አመለከተ።
ስለዚህ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የበጋው ዕረፍት በተመለከተ በኢጣሊያ የአልባኖ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቸሎ ሰመራሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እ.ኤ.አ. ሐምሌ ወር አጋማሽ ቅዱስነታቸው በፍራስካቲ ከተማ ሐውጾተ ኖልዎ በማከናወን በከተማይቱ ካቴድራል መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚመሩና እንዲሁም ከባቭየራ በሚመጡት ምእመናንና የውሁድ ጥዑም ሙዚቃ ቡድን ለክብራቸው የውሁድ ጥዑም ሙዚቃ ትርኢት እንደሚያቀርብ ገልጠው፣ ዕረፍት ለሰው ልጅ ምንኛ አስፈላጊ መሆኑ የሚያሳስብ ብቻ ሳይሆን፣ ከተለመደው ዕለታዊ ኑሮ ወጣ ተብሎ፣ ለየት ባለ መልኩ ጽሞናና ቃል በማጣመር ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግኑኝነት፣ ጥናት፣ አስተንትኖ ንባበ መጻሕፍት በተለይ ደግሞ ንባበ ቅዱስ መጽሐፍ በመፈጸም ጤናማ ዕረፍት ማከናወንና ወላጆች ከልጆቻቸው ከወዳጆቻቸው ያላቸው ግኑኝነት የሚያጎለብቱበት፣ ትብብርና መደጋገፍ የሚያረጋግጡበት ወቅት መሆን እንዳለበት ያስተምሩናል።
የተፈጥሮ ውበት በማስተንተንና የሁሉም ወበት መሠረት ከሆነው ጋር የምንገናኝበት ለየት ያለው ጊዜ መሆን እንዳለበት፣ ቅዱስ አባታችን ባንድ ወቅት ያሉትን ሃሳብ ብፁዕነታቸው አስታውሰው፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በካስተልጋንዶልፎ ለበጋ ዕረፍት መገኘት እ.ኤ.አ. ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ የጀመሩት ልምድ መሆኑ ገልጠው ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለበዓለ ፍልሰታ ለማርያም የሚያርገው መስዋዕተ ቅዳሴ በመምራትም ሁሉንም ለእምነት ዓመት እንደሚያነቃቁ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.