2012-07-02 14:14:22

ጳጳሳዊ የቅዱስ ቶማስ ዘአኵይኖ ተቋም 12ኛ ሙሉ ዓመታዊ ጉባኤ


ቅዳሜ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ጳጳሳዊ የቅዱስ ቶማስ ዘአኵይኖ መንበረ ጥበብ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ቅዱስ ጳውሎስ፣ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ የቅዱስ ቶማስ ዘአኩይኖ ጳጳሳዊ መንበረ ጥበብ 12ኛው ሙሉ ዓመታዊ ጉባኤ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴና ባሰሙት ስብከት RealAudioMP3 ማስጀመራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ ብፁዕነታቸው ባሰሙት ስብከት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. የእምነት በር በሚል ርእስ ሥር ባቀረቡት ሐዋራያዊ መልእክት አማካኝነት እንዲከበር ያወጁት የእምነት ዓመት “ሞትን አሸንፎ ለተነሣው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታማኞችና ደስተኞች ምስክሮች እንድንሆን የሚደግፍ ነው። ብፁዕነታቸው እግዚአብሔር የሕይወት ምንጭ በመሆኑ፣ በሕይወት ላይ ኃይል ያለው፣ ሞትን በጠቅላላ በምድራዊ ሕይወት አጋጣሚዎች ላይ ድል የነሣው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር እንደማይለየን በቅዱስ ቁርባን አማካኝነት ቀጣይነቱ እስከ ፍጻሜው ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ በማለት ያረጋገጠልን መሆኑ አብራርተው፣ ቅዱስ ቶማስ ዘአኵይኖ፣ ጽኑና ሕያው እምነት ቅዱስ ቁርባን በመኖር በቅዱስ ቁርባን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወት ምንጭ መሆኑ በመመስከር በተጨባጭነት መልክ በመካከላችን መሆኑ እንታመናለን፣ ስለዚህ ሁሉም ነገር በሞት የሚጠቃለልና የሚዘጋ ነው እየተባለ በተለያየ መልኩ በሚሰበከው ባህል ሳንበገር፣ ከሕይወት ባሻጋር ያለው ሕይወት እርሱም በሞት ላይ ድል ለነሳው ሕይወት በእምነት መስካሪዎች በመሆን የሕይወት ልጆች ሆነን እንገኝ ብለዋል።
መጽሐፈ ጥበብ “እግዚአብሔር ሞትን አልፈጠረምና የሕያዋንም ጥፋት ደስ አያሰኘውምና” (2፣ 13)። “እግዚአብሔር ሰውን አለ ሞት ፈጥሮታልና በራሱም አምሳል ፈጥሮታልና” (2፣24)። ቤተ ክርስትያን ይኸንን እውነት በመመስከር በእምነት ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር የሚደረገው ጉዞ በቅዱሳት ምሥጢራት፣ በሥልጣናዊ ትምህርቶችዋ አማካኝነት በመምራት የሚሆነውን ከወዲሁ እያጣጣምን እንድንኖር ትመራናለች፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያወጁት የእምነት ዓመት ይኸንን ያረጋግጥልናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.