2012-07-02 14:09:45

የር.ሊ.ጳ. የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. 01/07/2012)
“ሕይወት ቁሳዊና አግዳሚ ዕይታ መሠረት መግለጥ እንዲቀር”


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና እኩለ ቀን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በብዙ ሺ የሚገመቱት ከውስጥና ከውጭ የመጡት መእመናን በተገኙበት ከሐዋርያዊ መንበር መስኮት ሆነው ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ከመድገማቸው ቀደም በማድረግ “ሕይወት በቁሳዊና በአግዳሚ ዕይታ መሠረት መግለጥ እንዲቀር” RealAudioMP3 በሚል ሃሳብ ላይ በማተኮር፣ ኢየሱስ የመጣው የሰውን ልጅ ልብ ለመፈወስ፣ የድህነት ጸጋ ለማደልና በእግዚአብሔር አንድያ ልጅ እንዲያምን ጥሪ ለማቅረብ ነው፣ በማለት በላቲን ሥርዓት የዕለቱ ንባበ ወንጌል መሠረት ኢየሱስ የመጣው የሰውን ልጅ በሙላት እውነተኛ ነጻነቱን ለማቀዳጀት ነው፣ ኢየሱስ የፈጸመውና ፈውስ፣ ኢየሱስ ምንኛ በጥልቅ ወደ ሰው ልጅ ስቃይ በመግባት ሥጋዊ ፈስው መታደልን የሚገልጥ፣ ሆኖም የሚሰጠው ፈውስ ውጫዊ አካልን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን፣ የሰው ልጅ በእምነት አማካኝነት ለአብ አንድያ ልጅ ገዛ እራሱን በእምነት ክፍት ለማድረግ ውስጣዊ መለወጥን የሚያድል የፈውስ ጸጋ ነው። “ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር ከተለያዩ ችግሮች ነጻ ያወጣን ዘንድ ችግሮቻችንን ይፈታ ዘንድ ወደ እርሱ እንጸልያለን፣ ተጨባጭ ፍላጎት የሚመለከትም፣ ትክክልም ነው። ሆኖም ግን ዘወትር ካለ መታከት እርሱን መጠየቅ ያለብን፦ ጌታ ሕይወታችንን እንዲያድስ የእርሱ ፍቅር ፈጽሞ ለብቻችን እንደማይተወን የሚያረጋግጥልን በእርሱ አሳቢነት መታመንን የሚያጎናጽፈን ጽኑ እምነትን ነው” ብለዋል።
ቅድስነታቸው አክለውም ለታመሙትና በችግር ላይ ለሚገኙት ቅርብ በመሆን የጌታን ፍቅርና አሳቢነትን የሚመሰክሩ የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች፣ ውስጣዊ ጸጥታንና ተስፋን የሚያስፋፉ መሆናቸውም ሲገለጡ፦ የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች በሥነ ሕምክናና ጤና ጥበቃ ሙያ በሚገባ የታነጹ መሆን ይገባቸዋል፣ ሆኖም ሙያዊ ሕንጸት ለብቻው በቂ አይደለም፣ ሙያው ሰብአዊነት እና ልባዊ አተኩሮ የሚጠይቅም መሆኑ መገንዘብ ይኖርባቸዋል። ስለዚህ በክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ ፍቅርን የሚያነቃቃ ከሚፈጽሙት ሙያዊ አገልግሎት ባሻገር በሚሰጡት ሙያዊ አገልግሎት ልባቸው ወደ ሌላው ክፍት ለማድረግ የሚያበቃቸው ሰብአዊ ሕንጸት ያስፈልጋቸዋል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በመጨረሻም በእምነት ጉዞና በምንሰጠው ሰብአዊና መንፈሳዊ አገልግሎት ቅድስት ድንግል ማርያም ትደግፈን በማለት ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ደግመው እንዳበቁ፣ ሁሉም በሚቀበለው ጥሪ የእግዚአብሔር አሳቢነትና ቅርበትን እንዲመሰክር አደራ ካሉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መልካም የበጋ ዕረፍት ተመኝተው ወደ መጡበት ሸኝተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.