2012-07-02 14:16:36

ክርስትያኖች በማህበራዊ ጉዳይ


“በማበራዊ ጉዳይ የክርስትያኖች ሚና” በሚል ርእስ ሥር የኤውሮጳ ኅብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተጠሪዎች የተሳተፉበት የሰብአዊ ክብር ተቋም ያነቃቃው የሁለት ቀናት ዓውደ ጥናት RealAudioMP3 መካሄዱ ሲገለጥ፣ በዚህ እ.ኤ.አ. ከሰኔ 29 ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. በተካሄደው ዓወደ ጥናት የተቋሙ የክብር ሊቀ መንበር ጳጳሳዊ የፍትሕና ሰላም ምክር ቤት ሊቀ መንበር የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ረናቶ ራፋኤለ ማርቲኖ የተሳተፉም ሲሆን፣ ይኽ የሰብአዊ ክብር ተቋም ጋር በኤውሮጳ ኅብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕንፃ እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ክብር ጉዳይ የሚከታተል ኮሚቴ በኤውሮጳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ኑርጅ ደቫ ሊቀ መንበርነት የሚመራ መመሥረቱም የሚዘከር ሲሆን፣ ዓውደ ጥናቱን የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት እንደተቻለውም፦ ብፁዕ ካርዲናል ማርቲኖ ባሰሙት ንግግር፣ ጳጳሳዊ የፍትሕና ሰላም ምክር ቤት የካቶሊክ ሥርወ እምነት ትምህርት የሰው ልጅ ሰብአዊነትና ክብር ጉዳይ በተመለከተ ለሚያስተምረው መሠረታዊ ሃሳብ መሠረት የሆነው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት አስተዋጽኦ ያቀረበ መሆኑ ዘክረው፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በዓለማዊ ትሥሥር ዓለማዊነቱ መረጋገጥ የሚገባው ትብብርና መደጋገፍ ነው ያሉት ሃሳብ ወሳኝ መሆኑ እንዳስታወሱም ለማወቅ ሲቻል፣ የኤውሮጳ ኅብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የአየር ላንድ ተወላጅ ጋይ ሚትሸል፣ ኤኮኖሚና ገበያ በተመለከተ የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት “የገበያ ማኅበራዊ ኤኮኖሚ” በሚል ርእስ ሥር በደረሱት ሰነድ አማካኝነት የሰጡት አስተዋጽኦ የሚደነቅ ነው። ስለዚህ በንዋይ ላይ የተመሠረተ ገበያ፣ የገበያ ማኅበራዊ ኤኮኖሚ የሚወክል እንዳልሆነ ያስረዳሉ፣ ስለዚህ የገበያው ማእከል ሰው መሆን አለበት፣ በአሁኑ ወቅት ኤኮኖሚ ሰብአዊነትን ማእከል ያደረገ መሆን አለበት ለሚለው በተለያየ መልኩ በመገለጥ ላይ ላለው አስተሳሰብ መነሻው የብፁዓን ጳጳሳቱ ሰነድ ነው። እንዲህ በመሆኑም ብፁዓን ጳጳሳት በማኅብራዊ ፖሊቲካዊና ኤኮኖሚያ ጉዳይ የሰው ልጅ ማእከል መሆን እንዳለበት የሰጡት ትምህርት የፖለቲካ አካላት ሊመሩበት የሚችሉ መሠረታዊ ሃሳብ ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ስፐራንዛ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.