2012-06-29 14:08:48

የተባበሩት መንግሥታትና የአፍሪቃ ኅብረት


በሰሜን ኡጋንዳ የተመሠረተው በአገሪቱና በደቡብ ሱዳን በዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎና በማእከላዊት ረፓብሊክ አገሮች የሚንቀሳቀሰው ገዛ እራሱን የጌታ ታጣቂ ሠራዊት በሚል መጠሪያ RealAudioMP3 የለየው የተዋጊ ኃይል አባላትና የዚሁ ኃይል መሪ ጆሰፍ ኮንይ በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተባበሩት መንግሥታትና በአፍሪቃ ኅብረት መካከል 5000 የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ከሚቀጥለው ታህሳስ ወር ለማሰማራት ስምምነት መደረሱ ከትላትና በስትያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጽ/ቤት ለተባበሩት መንግሥታት የማእከላዊ አፍሪቃ ጉዳይ ወኪልና አስተባባሪ አቡ ሙሳ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።
ይኽ በተባበሩት መንግሥታትና በአፍሪቃ ኅብረት የተደረሰው ስምምነት አምስት ግቦች ያለው ሆኖ፣ በቅድሚያ ትጥቅ ማስፈታት፣ ብሎም ተዋጊው ኃይል እንዲበታተን በጠቅላላ እንዲፈርስ ማድረግ፣ የተዋጊው ኃይል አባላት ከኅብረተሰብ ጋር በሰላም ተቀላቅለው ለመኖር እንዲችሉ ማዋሃድ፣ የክልል ነዋሪው ሕዝብ ደህንነትና ጸጥታ ጥበቃ፣ በተለይ ደግሞ የሕፃናት ጉዳይ በተመለከተ በመጨረሻም ሰላምና እርቅ ማረጋገጥ፣ የሰብአዊ መብትና ክብር ጥሰት ተጠያቂዎችን ለፍርድ ማቅረብና የሕግ ሉአላዊነት ማስጠበቅ የተሰኙት መሆናቸው ሙሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራራታቸው ሚስና የዜና አገልግሎት ከሰጠው የዜና ምንጭ ለመረዳት ተችለዋል።
የአፍሪቃ ኅብረት የጌታ ታጣቂ ኃይሎች ጉዳይ የሚከታተለው ልዩ ወኪል ፍራንሲስኮ ማደይራ፣ በዚህ ተልኮ የሚሰማራው የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል፣ የጌታ ሠራዊት ከሚንቀሳቀስባቸው አራቱ አገሮች የተወታጡ ሆነው ዋናው ጠቅላይ መቀመጫውም በደቡብ ሱዳን ያምቢዮ ከተማ እንደሚሆን የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የጠቀሰው ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.