2012-06-29 14:05:29

የር.ሊ.ጳ. ሳምንታዊ የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ( እ.ኤ.አ.27/06/2012)
“እግዚአብሔር ታላቅነትን ሳይሆን አገልግሎትን ነው የሚሻው”


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንደተለመተደው ባለፈው ረቡዕ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ በብዙ ሺ የሚገመቱት ከውስጥና ከውጭ የመጡት ምእመናን ተቀብለው በቅዱስ ጳውሎስ መልእክቶች ሥር ስለ ጸሎት የጀመሩት ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል “ሰብአዊ አመክንዮ ስልጣንን የበላይነትን ኃይለኛ መሣሪያ RealAudioMP3 የሚሻ ሲሆን፣ ገዛ እራስ በግንዛቤ ለማረጋገጥ የሚቻለው ገዛ እራስን ባዶ በማድረግ” መሆኑ፣ ቅዱስ ጳውሎስ ለፊሊጲሲዩስ በጻፈው መልእክት ዘንድ የሠፈረው “ሥነ ክርስቶሳዊ ማሕሌት ተብሎ የሚገለጠው በምዕራፍ 2 ያሉትን ክፍለ ምዕራፎች ወይንም ቤቶች በማስድገፍ፦ “ወደ እግዚአብሔር የሚወጣው ገዛ እራስን ወደ አገልግሎት ዝቅ በማደግ ወይንም አገልጋይ በመሆን ነው በማለት፣ በክርስቶስ የተመለከተው መንገድ ጽማሬ ሃሳቡን ገልጠው፣ የባርያ (ተገዥ) ሁኔታና መልክ የገዛ እራሱን በማድረግ ገዛ እራሱን ሙሉ በሙሉ ዝቅ የሚያደርግ፣ እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ወዳለው የክብር ሥፍራ ከፍ ያደርገዋል”። የመስቀል መንገድ ገዛ እራስን በትሕትና “ለእግዚአብሔር ፈቃድ” እንደ መሥዋዕት ማቅረብ የሚለው ቅዱስ ጳውሎስ ለገዛ እራሱ መርኃ ሕይወት በማድረግ “ምናልባት በሮማ ሳይሆን አይቀርብም ተብሎ የሚነገርለት እርሱም በወህኒ ቤት እያለ ለፊሊጲሲዩስ በጻፋት መልእክት ዘንድ ዕለተ ሞቱ ማለት የደም ሰማዕትነት የሚቀበልበት ዕለት መቃረብ የተገነዘበ ቢሆንም ቅሉ፣ ኢየሱስ ነጻ ለሆኑት ሰዎች ሳይሆን ለባሮች የሚታቀበው በመስቀል ተሰቅሎ በመሞት የመጨረሻው የትህትና ደረጃ በመኖር የገለጠው ሕይወት የደስታና የመረጋጋት ምክንያት እንደሆነለት” ገልጠው “የሰው ልጅ ገዛ እራሱን እግብ ለማድረስ ሰብአዊ አመክንዮ የሚያቀርበው አማራጭ መንገድ ይሻል፣ ሰብአዊ ፍጥረት አሁንም የእግዚአብሔር ታላቅነትን ዘንድ ለመድረስ እንደ እግዚአብሔር ለመሆን በገዛ እራሱ ኃይል የባቢሎን ግንብ መገንባቱን አላቋረጠም ብለዋል።
“ወደ እግዚአብሔር የሚወጣው ወደ አገልጋይነት ዝቅ በማለት ነው” በተሰኘው ጽማሬ ሃሳብ በክርስቶስ የተመለከተልንን መንገድ ሲያስረዱ “በሰው ምሳሌ በመግለጥ የባርያ መልክ በመውሰድ በገዛ ፈቃዱ ገዛ እርሱን ድኻ አደረገ…በዚህ ምክንያትም እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ወዳለው የክብር ሥፍራ ከፍ አደረገው”።
ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻው እራት የፈጸመው ተግባር ማስታወስ አስፈላጊ መሆኑ ገልጠው፣ የደቀ መዛሙርት እግር በማጠብ ይኸንን ተግባር እርስ በእርሳቸው እግራቸው በመተጣጠብ እንዲኖሩት ማሳሰቡንም በማስታወስ፣ ‘እግዚአብሔር ታላቅነት ሳይሆን ለፍቅርና ለአገልግሎት ገዛ እራስን በማቅረብ፣ ወደ እግዚአብሔር የሚወጣው በዚያ የሰው ልጅ በማንጻት እግዚአብሔርን እንዲያይና እንዲያስተውል የሚያበቃው በትህትናና በአገልግሎት ነው” ብለዋል።
ከገዛ እራስ መውጣት ወደ ገዛ እራስ መግባት ወይንም ከገዛ እራስ ጋር መገናኘት ማለት መሆኑ ሲያስረዱ፣ “በጸሎትና ከእግዚእብሔር ጋር በምንፈጽመው ግኑኝነት አማካኝነት ወደ የሕይወት ኃይል ለመግባት አእምሮአችንና ልባችንና ፍላጎታችን ለመንፈስ ቅዱስ ተግባር ክፍት ለማድረግ የሚያበቃን መሣሪያ ነው”፣ ጸሎት ሁለመናችንን የሚያጠቃልል ጸጥታና እርጋታ ቃልና መዝሙር እንዲሁም ምልክት አቀፍ መሆኑ ሲያብራሩ “በቅዱስ ቍርባን ፊት መንበርከክ ወይም ለመጸለይ ጉልበትን አጥፎ መገኘት፦ በሁለመናህ እግዚአብሔርን ማምለክ ማለት ነው። በጌታ ፊት ስንንበረከክ እርሱ ብቸኛ ሕይወታችን መሆኑ የሚያረጋግጠው እማኔ ላይ ያለንን እምነት ነው የምንታመነው” ካሉ በኋላ “በቅዱስ ቍርባን ፊት አምልኮን ለመፈጸም ስንገኝ ሕይወታችንን ወደ እርሱ ከፍ እንዲያደርጋት ገዛ እራሱ በትህትና አማካኝነት ወደ ወረደው የእግዚአብሔር ፍቅር ለመግባት ነው”። በማለት በጣልያንኛ ቋንቋ ያሰሙትን የዕለቱን ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አጠናቀው በአበይት ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ድጋሚውን አጠር በማድረግ ካሰሙ በኋላ በማሰማት በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታን አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.