2012-06-29 14:07:18

የሃይማኖት ነጻነት ጉዳይ የሚከታተል ማእከል


የኢጣሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ቢሮና የሮማ ከተማ ምክር ቤት በመተባበር በኢጣሊያ የሃይማኖት ነጻነት ጉዳይ የሚከታተል ማእክል መቋቋሙ ሲገለጥ፣ ይኸንን የሃይማኖት ነጻነት ታዛቢ RealAudioMP3 ማእከል በይፋ የሚሰጠው አገልግሎት ለማስጀመር በተካሄደው ጉባኤ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የባልቲሞራ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዊሊያም ሎሪ መሳተፋቸው ሲታወቅ፣ የጣቢያው አስተባባሪ የሥነ-ኅብረተሰብ ሊቅ በኤውሮጳ የደህንነትና የትብብር ማህበር የጸረ ዘረኝነትና ጸረ ክርስትያን እንዲሁም በሌሎች ሃይማኖቶች ላይ የሚፈጸመው አድልዎ ለሚከታተለው ቢሮ ተጠሪ በመሆን ያገለገሉት ማሲሞ ኢንትሮቪኘ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የሃይማኖት ነጻነት ታዛቢ ቢሮ ዋነኛ ዓላማው የኢጣሊያ የውጭ ግኑኝነት በዚሁ የሁሉም ነጻነት መሠረት በሆነው ዘርፍ ለመደገፍና በሚፈጽማቸው ግኑኝነቶች ለማበረታታት መሆኑ ጠቅሰው የሃይማኖት ነጻነት እቅድ በሁሉም መንግሥታትና በዓለም አቀፍ ደረጃም ትኵረት እንዲደረግለት የሚንቀሳቀስ መሆኑም ነው ብለዋል።
ከብፁዕ አቡነ ሎሪ ጋር በመሆን ይኸንን የሃይማኖት ነጻነት ታዛቢ ጣቢያ ሥራውን በይፋ ማስጀመር በርግጥ ደስ የሚያሰኝ ነው። ምክንያቱም የሃይማኖት ነጻነት በምዕራቡ ዓለም ሳይቀር በተለይ ደግሞ የሕሊና ነጻነት ጉዳይ ለአደጋ እየተጋለጠ መሆኑ የሚመሰክር መሆንና የጣቢያው ዓላማ ሁለት ገጽ እንዳለው ገልጠውም፣ በማያያዝ የኢጣሊያ መንግሥት በሌሎች አገሮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት ሳይሆን፣ የሃይማኖት ነጻነት ጉዳይ በተመለከተ መንግሥታትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ካለው ክብር አንጻር ትኵረት እንዲያደርጉበትና ስለ ጉዳዩ እንዲያስተነትኑ የሚያነቃቃ ነው። በናይጀሪያ እንዲሁም በፓኪስታን ብቻ ሳይሆን በተለያየ መልኩ በተለያዩ አገሮች የሃይማኖት ነጻነት ሲጣስ ይታያል፣ የተለያዩ መንግሥታት የሚያረቁትና የሚያጸድቁት ሕጎች የሃይማኖት ነጻነት በተመለከተ አሻሚ ትርጉም ያለው በመሆኑም የብዙሃንና የውሁዳን ሃይማኖት ጉዳይ የህሊና ነጻነት መጣስ በምዕራቡ ዓለም እየተሳፋ በመሆኑም የቤተ ክርስትያን ህሊና ብቻ ሳይሆን የአባላቶቿ ጭምር የሚመለከትም ነው። ስለዚህ እስያንና አፍሪቃን ብቻ የሚመለከት እንዳልሆነ የሚመሰክር ነው ብለዋል።
የባልቲሞራ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዊሊያም ሎሪ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የሃይማኖት ነጻነት ታዝቢ ቢሮ ማቋቋም በጣም አስፈላጊ ነው፣ በዓለማችን የሃይማኖት ነጻነት ጥበቃና ጥሰት በተመለከተ ያለው ሁኔታ የሚከታተል በመሆኑም፣ ከዚህ አኳያ በኤውሮጳ ብቻ ሳይሆን በሁሉም አገሮች ጭምር መረጋገጥ ያለበት ዓላማ ነው ካሉ በኋላ አክለውም ሕግ በመጠቀም የሰው ልጅ የህሊና ነጻነት መጣስ ተገቢ አይደለም፣ የሕሊና ነጻነት መጣስ ጸረ የሰብአዊ መብትና ክብር ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.