2012-06-29 17:48:39

በነዲክት 16ኛ የቁስጢጢንያ ፓትርያርክ ልዑካን ተቀብለው አነጋግርዋል ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት የቤተ ክርስትያን አንድነት የቁስጢንጢንያ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ባርተሎመዮ አንደኛ ልዑካን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ልዑካኑ ውደ ቫቲካን የመጡት በላቲን ሥርዓተ አምልኮ ዛሬ ሮም ውስጥ በሚክበረው የቅዱሳን ጰጥሮስ እና ጳውሎስ ዓመታዊ በዓል ለመስታፍ እንደሆነ ይታወቃል።

ቅድስነታቸው የቁስጢንጢንያ የቤተ ክርስትያን አንድነታዊ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ባርቶሎመዮ አንደኛ በአብያተ ክርስትያናት መካከል ውይይት እንዲደረግ እና ቅዱስ ወንጌል እንዲሰበክ የሚያካሄዱት ጥረት ማመስገናቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

በነዲክት 16ኛ ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ከ50 ዓመታት በፊት የአብያተ ክርስትያናት ሕብረት እንዲገኝ በነሱ መካከል ውይይት እንዲካሄድ ያሳለፈ ውሳኔ መሰረት በማድረግ ውይይቱ ቀጣይ እና ስኬታማ እንዲሆን ያላቸውን ተስፋ መግለጻቸውም ተዘግበዋል።የሮም ከተማ ጠባቂዎች በቅዱሳን ጰጥሮስ እና ጳውሎስ ስብከተ ቅዱስ ውንጌል አለት ላይ የተመሰረች መሆንዋ ክብረ በዓሉ በስታወስ ማስገንዘባቸው ተግልጠዋል።ቤተ ክርስትያን ሐውርያት እና ሰማዕታት የጰጥሮስ እና ጳውሎስ ዱካ እንደምትከልም ቅዱስ ኣአባችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት መግለጻቸው ተመልክተዋል።

ፊታችን ጥቅምት ወር አስራ ሀንድ ቀን ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ የተካሄደበት ሐምሳ ዓመት እንደሚከበር ያስታወሱት በነዲክት 16ኛ በዚህ 50 ዓመት የኤኩመኒዝም የክርስትያን አንድነት ጉዞ እንደሚታወስ ማውሳታቸው ተገልጠዋል። ከ50 ዓመታት በፊት ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ በተካሄደበ ግዜ የቁስጢንጢንያ ፓትርያርክ ልዑካን ቡድን ተሳታፊ መኖራቸው ቅድስነታቸው አስታውሰዋል።

ስለዚህ በቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና የቁስጢንጢንያ ተዋህህዶ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን መካከል ከረጂም ዓመታት በፊት የጀመረ ወንድማማችነታዊ ግኑኙነት መጀመሩ በነዲክት 16ኛ አስምረውበታል።

በነዲክት 16ኛ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን የጋራ ሀገራት አቀፍ የውይይት ጦሎግያዊ ኮሚስዮን ኤኩመኒዝም የቤተ ክርስትያን አንድነት በተመልከተ ዕድገት እንድያሳይ ያላቸውን ከፍተኛ ተስፋ መግለጣቸው ተመልክተዋል።

በሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ የቁስጢንጢንያ ኦሮቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ የነበሩ ከ40 ዓመታት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ብጹዕ ውቅዱስ አተናጎራስ ብጹዕ ዮሐንስ 23ኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ለቤተ ክርትያን አንድነት ያልሰለሰ ጥረት ማካሄዳቸው ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ማስገንዘባቸው ተገልጠዋል።

በነዲክት 16ኛ አያይዘው የወቅቱ የቁስጢንጢንያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የአንድነት ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ባርቶሎመዮ አንደኛ ከሳቸው በፊት የነበሩ ፓትርያርካት አተናጎራስ እና ዲሚትርዮስ ዱካ በመከተል ለአንድንነት ክርስትያን የሚያካሄዱት ጥረት መልካም እና የሚመስገን እና የሚወደስ እንደሆነ አስታውቀዋል።

የቤተ ክርስትያን አንድነት እግዚአብሔርን በአንድ ልብ እና በአንድ ነፍስ ብቻ እንድናመስግነው እንድናገለግለው እና እንድንወድሰው ይረዳናል ካሉ በኃላ ኅያል እና ከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር የክርስትያን አንድነት እንዲቸርልን እንለምነው እንማጸነው ለዚሁም እንጸልይ በማለት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ማመልከታቸው ተዘግበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.