2012-06-25 15:01:47

ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም”


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ክርስትያን የቅዱስ ዮሓንስ መጥምቅ ዓመታዊ በዓል ባከበረችበት ዕለተ ሰንበት እኵለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ፊት ካለው ሐዋርያዊ መስኮት ሆነው ከውስጥና ከውጭ አገር ከተሰበሰቡት በብዙ ሺ የሚቆጠሩት ምእመናን በተገኙበት ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከመድገማቸው ቀደም በማድረግ ባሰሙት ስብከት፣ እ.ኤ.አ. ስኔ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. RealAudioMP3 ባለፈው ወር በተከታታይ በጣም አደገኛ በሆነው ርእደ መሬት በተጠቃው ሰሜን ኢጣሊያ “የኩላዊት ቤተ ክርስትያን ትብብር ቅርበትና ድጋፍ ለማረጋገጥ” ሐዋርያዊ ዑደት እንደሚፈጽሙ ገልጠው፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የግብረ ሠናይ አገልግሎት በሁሉም መስክ እግብር ላይ ለማዋል የመላ ዓለም ካቶሊካውያን ምእመናን የሚሰጡት ድጋፍ አመስግነው፥ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በሁሉም መስኩ የሚደግፍ ለባለንጀራው ቅርብ ይሆናል ካሉ በኋላ፣ በሰሜን ኢጣሊያ ለሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ዑደት ሁሉም ምእመናን በጸሎት ይዘክሩዋቸውም ዘንድ አደራ ብለዋል።
ቅዱስነታቸው በዕለቱ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ያከበረችው የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በዓል በማስታወስ፣ ውዶቼ፦ “ቅድስት ድንግል ማርያም በእድሜ የገፋቸው ዘመዷ ኤልሳቤጥ በማሕጸንዋ የተሸከመቸው ሕፃን ዕለተ ልደቱ እስኪደርስ ቅርብ ሆና በሰጠቸው አገልግሎት የግብረ ሠናይ አብነት መሆንዋ ተገልጦልናል ካሉ በኋላ፣ ሁሉ ያ መጥምቅ ዮሐንስ በታላቅ ትሕትናና በጋለ ነቢያዊ መንፈስ ያወጀው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን በሚገባ ይከተልም ዘንድ እርሷ ድገፍ ነች” ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር አሳርገው እንዳበቁም በአምሥቱ ዓለም አቀፍ አበይት ቋንቋዎች በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ከአርባ ሺሕ በላይ ለሚገመቱት ምእመናን ሰላምታን አቅርበው፣ የኩላዊት ቤተ ክርስትያን የግብረ ሠናይ አገልግሎት እግብ ለማድረስ ሁለገባዊ ትብብር የሚሰጡትን አመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መልካም ሰንበት ተመኝተው ሁሉንም ወደ መጡበት ሸኝተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.