2012-06-25 15:03:28

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፥ “በተስፋ ጉዞ የሚያጋጥም ሞት”


ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፣ ጦርነት እርሃብ ስቃይ ጥላቻ በስተቀረ ተጨባጩ ጊዜ ምንም ነገር ሊያቀርብለት ስለ ማይችል መጪው ብሩህ ይሆንለት ዘንድ ተስፋ በማድረግ ቤቱንና ንብረቱን አገሩንና ቤተሰቡንም ጥሎ ለስደት የሚያቀናው ዜጋ ወደ RealAudioMP3 ተስፋ ምድር በሚያደርገው ጉዞ በሞት አደጋ የሚቀጭ፣ ተስፋን ሲጠባበቅ ሞት የሚያጋጥመው ዜጋ ማእከል በማድረግ ቀጥለው፣ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ርክስትያን እ.ኤ.አ. ሰኔ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ተዘክሮ የዋለው ዓለም አቀፍ የስደተኞችና የተፈናቃዮች ቀን ምክንያት ስለ ስደተኞችና ተፈናቃዮች የጸሎት ቀን በማለት በሁሉም ሰበካዎችና ቁምስናዎች በተስፋ ጉዞ የሚያጋጥም ሞት በሚል ርእስ ታስቦ መዋሉ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ ገልጠው፣ በገዛ እራስ አገር ከሚያጋጥም ጭቆናና አድልዎ የሰባአዊ መብትና ክብር ጥሰት፣ እርሃብ ከመሳሰሉት የስቃይና የሞት ምክንያቶች ገዛ እራሱን ለማዳን ሲል ለመሰደድ በየብስና በባህር በሚያደርገው ጉዞ የሚያጋጥመው አሰቃቂው ሞት፣ በዚህ ጉዞ ከዚህ ዓለም በሞት የሚለው አስከሬኑ ሳይገኝ የሚቀረው ዜጋ ለዓለም አቀፍ የኅሊና ጥያቄ ነው ብለዋል።
ባለፉት የመጨረሻ ዓመታት 20 ሺሕ ስደተኞች በስደት ጉዞ የሞት አደጋ እንዳጋጠማቸውና ባለፈው ዓመት 3 ሺሕ ስደተኞች ወደ ኢጣሊያና በኢጣሊያ በኵል ወደ ተለያዩ የኤውሮጳ አገሮች ለመሰደድ በተናንሽ ባለ ሞተር ጀልባዎች ተሳፍረው የሜዲትራኒያን ባህር በማቋረጥ ላይ እያሉ ለሞት መዳረጋቸውንም ጠቅሰው፣ ስደት ወደ በለጸጉት አገሮች ብቻ እንዳልሆነም፣ ባለፉት ጥቂት ወራት ከማሊ ወደ ማሪታኒያ የተሰደዱት 70 ሺሕ ዜጎች በማስታወስ ከገለጡ በኋላ፣ ዓለማችን ሥፍር ቁጥር የሌለው የስደተኞች መጠለያ ማእከል ሆናለች። በስደት ጉዞ የሚያጋጥመው አመጽና ቅትለት፣ በስደተኞች ሴቶች ላይ የሚፈጸመው የግብረ ሥጋ አመጽ፣ ሁሉን ትቶ አለ ምንም ቀርቶ ዕለታዊ ኑሮውን አንድ ብሎ ለመጀመር ታልሞ በስደት ላይ እያለ ለከፋው አደጋ ተጋልጦ ዳግም መጀመር የሚለው የተስፋ ዕድል ርቆት ብሎም ተነፍጎት አስከሬኑ የትም የቀረ ዜጋ በእውነቱ ዝም ተብሎ መታለፍ የሌለበት አቢይ የኅሊና ጥያቄ ነው።
የስደተኞች ጉዳይ ለዓለም ለምእመናን መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ ተጋርጦ ቢመስልም፣ ሰብአዊና መንፈሳዊ ልክነት የተጎናጸፈ የበለጠ ዓለም ለመገንባት አወንታዊ ግፊት ይሁነን በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.