2012-06-25 15:05:07

ዓለም አቀፍ የመናብርተ ጥበብ ጉባኤ


እ.ኤ.አ. ሰኔ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. የሮማ ሰበካ የመናብርተ ጥበብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ቢሮ ያዘጋጀው 9ኛው ዓለም አቀፍ የመናብርተ ጥበብ አስተማሪዎች ጉባኤ እ.ኤ.አ. ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. RealAudioMP3 መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ ይኽ “ለመናብርተ ጥበብ የወጣት ትውልድ መንፈስ ዳግም ማጎናጸፍ፦ ወጣት ትውልድ በእሴት ላይ የሚታነጽበት ሥፍራና ጊዜ” በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ በተካሄደው ጉባኤ አስተምህሮ የሰጡት በሮማ ላ ሳፒየንዛ መንበረ ጥበብ መምህር ፕሮፈሰር ማሪና ቦርጂ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “በአሁኑ ወቅት ተክስቶ ያለው ኤኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቀውስ ከባዶ የተከሰተ ሳይሆን ላለለፈው ስህተት የዋጋ ክፍያ ነው። የዛሬው ጉዞ የበለጠ መጻኢ ለመገንባት ላይ ያነጣጠረ ካልሆነ በስተቀረ በሚደጋገም ስህተት መኖር ይሆናል። ማእከላዊ ለረዥም ያቀና ውጥን አስፈላጊ ነው። መጪው ተፈርቶ ዛሬ በገዛ እራሱ በተዘጋ ዓይነት ፖለቲካዊ ማኅበራዊና ኤኮኖሚያው ሂደት መመራት የለበት” ብለዋል።
የሥነ መረጃ ምህንድስና ሥነ ጥናት ማኅበር ሊቀ መንበር ሚከለ ቺናሊያ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የመናብርተ ጥበብ መርሃ ግብር መጻኢ በማሕጸኑ ያቀፈ መሆን አለበት፣ ዛሬ በሚለው የሰዓት አቆጣጠር የሚታጠር መሆን የለበትም ብለዋል።
የተካሄደው ጉባኤ ባሰሙት ንግግር የዘጉት የሮማ ሰበካ የመናብርተ ጥበብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ቢሮ አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ሎረንዞ ለውዚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “መናብርተ ጥበብ በወጣት ትውልድ ላይ የሚያተኵሩ መሆን ይገባቸዋል የሚለው ግንዛቤ በግልጽ ያሳሰበ ጉባኤ ነው። ስለዚህ ለመናብርተ ጥበብ፣ የመናብርተ ጥበብ ዋነኛው ጥሪ ዳግም ማጎናጸፍ ያስፈልጋል። ሥራ ለማግኘት የሚለው ብዙዉን ጊዜ መናብርተ ጥበብ የሚበሩበት አመለካከት በርግጥ ሥራ አቢይ ክብር ያለው ጥሪ መሆኑ የማይዘነጋ ቢሆንም ቅሉ የእውቀት ሥፍራ ብቻ ሳይሆን የጥበብ መንበር መሆኑ ታምኖ ዓለም የሚያቀርበው ጥያቄ በጥልቀት የሚያነብ በእርሱ አማካኝነት ሕንጸት የሚሰጥበተ መሆን አለበት” ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.