2012-06-25 15:07:18

ቅድስት መንበር ስለ ሕይወትና አካባቢ ጥበቃ


የዛሬ 20 ዓመት በፊት ስለ መሬት ጉዳይ በተመለከተ የተካሄደው ጉባኤ በሚታወስበት ዕለት ይኸው ተቀባይነት ስላለው የልማት እቅድ በሚል ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የቡድን ሃያ የሁለት ቀናት RealAudioMP3 ጉባኤ እ.ኤ.አ. ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ለበለጠው መጻኢ ግንባታ የተሻለ መንገድ መሆኑ የተባበሩት መ ንግሥታት ድርጅት የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታትና ብራዚል የሚገኙባቸው አገሮች በታመነበት “የምንሻው ዓለም” በሚል ርእስ ሥር በተጠናቀረው የፍጻሜ ሰነድ መጠናቀቁ ተገልጠዋል።
ከዚህ የአካባቢ መጻኢ እድል ላይ በማነጣጠር ከተካሄደው ጉባኤ ጎን የሕዝቦች ጉባኤ በሚል መጠሪያ የተለያዩ የተቃውሞ መርሃ ግብሮች መከናወናቸውም ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህ የቡድን 20 በሪዮ ጉባኤ የተሳተፉት የመላ ኢጣሊያ የበጎ ፈቃድ ማኅበራት ፈደረላዊ ማኅበር ሊቀ መንበር ሰርጆ ማረሊ ከጉባኤው ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ “የኤኮኖሚ እድገት አካባቢ ወይንም ተፈጥሮ ማክበር ከሚለው አመለካከትና በተለይ ደግሞ የተፈጥሮ ሃብት ዘለዓለማዊነት ያለው እንደሆነ አድርጎ ከሚያስበው የኤኮኖሚ መርሃ ግብር መላቀቅ አለበት የሚል፣ አረንጓዴ ኤኮኖሚ ገቢራዊ የሚሆንበት መንገድ ማፈላለግ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ የተሰመረበት” መሆኑ ገልጠዋል።
የተካሄደው ጉባኤ ለግብርና ኤኮኖሚ ድጋፍ እሱም ለተናንሽ የግብርና ማኅበራት በድኾች አገሮች ለሚገኙት ድጋፍ እንዲሰጥ የሚል ነገር ግን የሚሰጠው ድጋፍ ምን ያክል መሆን እንዳለበት በአኃዝ የተተመነ መለኪያ ያጠቃለለ አይደለም። በጉባኤው የፍጻሜ ሰነድ ለሕይወት የሚስማማ ወይንም የሚደግፍ፣ “የሴቶች የወሊድነት ሰብአዊ መብትና ክብር” የሚል ሃሳብ ተካቶበት ይገኛል፣ የሴቶች የወሊድነት ሰብአዊ መብትና ክብር ሲባል ምን ማለት ነው? በእውነቱ ለተለያየ ትርጉም ክፍት እንዲሆን የተተወ ሃሳብ ነው የሚመስለው። ስለዚህ ቅድስት መንበር ይኽ የሴቶች የወሊድነት ሰብአዊ መብትና ክብር የሚለው ሃሳብ ጸረ ሕይወት የሆኑትን አመለካከቶችና ውሳኔዎች የሚያገል ሆኖ በግልጽ የሕይወት ባህል የሚያነቃቃና የሚደግፍ የሞት ባህል የሚያገል መሆን አለበት በሚለው ሃሳብ መሟላት ይኖበታል በማለት ለጉባኤው ስታሳስብ “የሴቶች የወሊድነት ሰብአዊ መብትና ክብር” የሚለው ሃሳብ ካለው አሻሚነት አንጻር ተገዳ ነው ብለዋል።
በሚቀጥለው ዓመት የቡድን 20 ጉባኤ እ.ኤ.አ. 2015 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሚሊዮኒዩም በሚል መጠሪያ በዓለማችን የሚታየው ድኽነት በግማሽ ለማጉደል የሚል ግብ ላይ በማነጣጠር እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. ላጸደቀው የልማት እቅድ ትግባሬው የሚገመግም፣ ቀጣይነቱን ፈር ለማስያዝ፣ እቅዱ ላለ መረጋገጥ ፈተና የሚያጋልጡት እንቅፋቶችንም በሚገባ ለመወጣት የሚያግዝ መንገድ የሚቀይስ እንደሚሆን አልጠራጠርም በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
ቅድስት መንበር በተባበሩት የዓለም አቀፍ ድርጅት የቋሚ ታዛቢነት መብት ሲኖራት፣ ሆኖም ይህ የሪዮ ጉባኤ፣ በተባበሩት መንግሥታት ሳይሆን በኅብረ-ብሔራውያን መንግሥታት የተጠራ በመሆኑም፣ የቅድስት መንበር ሱታፌ ባለ ሙሉ መብት ነው። በጠቅላላ በዚህ የሪዮ ጉባኤ ሥር ቅድስት መንበር ባካሄደቻቸው ክሌአዊ ግኑኝነቶች የተንጸባረቀ መሆን በቡድን 20 ጉባኤ ቅዱስ አባታችንን ወክለው ንግግር ያሰሙት በብራዚል የሳን ፓውሎ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኦዲሎ ፐድሮ ሽረር መግለጣቸውም የሚዘከር ነው።







All the contents on this site are copyrighted ©.