2012-06-23 08:38:34

የእምነት አመት፦ ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል አቅጣጫ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የእምነት ዓመት እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲከናወን “Porta fidei-የእምነት በር” በሚል ርእስ ሥር ባስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት አማካኝነት በይፋ እንዳወጁት የሚዘከር ሲሆን፣ ይህ የእምነት ዓመት አዋጅ በተመለከተም ትላትና RealAudioMP3 በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ RealAudioMP3 በይፋ መግለጫ ተሰጥቶበታል።
የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የመሩት የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ፣ በ“Porta fidei-የእምነት በር” ሐዋርያዊ መልእክት በ ቍ. 7 ሰፍሮ ያለው “በማመን ብቻ ነው እምነት የሚያድገውም የሚጎለብተውም” የሚለው ሃሳብ በመጥቀስ የእምነት ዓመት የመክፈቻ ዕለት ከዝክረ 50ኛው ዓመት የቫቲካን ሁለተኛው ጉባኤ እንዲሁም ከዝክረ 20ኛው ዓመት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ጋር አብሮ የሚሄድ ነው። ዋና ዓላማውም ሁሉም አማኝ በዕለታዊ ኑሮ ድካምነት፣ በታማኝነትና በቆራጥነት መላ ኅልውናውን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አደራ ለመስጠት የሚያበቃው እምነቱን ለመደገፍ መሆኑ ገልጠው፣ የመጨርሻው የእምነት ዓመት በኵላዊት ቤተ ክርስትያን አዋጅ መሠረት የቅዱስ ጴጥሮስ ሰማዕትነት ለመዘከር ማእከል በማድረግ እ.ኤ.አ. በ 1968 ዓ.ም. መካሄዱንም ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ በማስታወስ፣ እ.ኤ.አ. 1968 ዓ.ም. ማኅበራዊ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ታሪኩን ጠቅሰው የቅዱስ ጴጥሮስ ዝክረ ሰማእነት አማካኝነትም ተአምኖተ ሃይማኖትን ዳግም ተማምኖ አሜን ለማለትና በዚህ መሠረትም የሕዝበ እግዚአብሔር ተአምኖተ ሃይማኖት ለወቅቱ ዳግም ለማሰማት መሆኑ ካብራሩ በኋላ፣ 50ኛው ዓመት ዝክረ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እንዲሁም ዝክረ 20ኛው ዓመት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ፣ ተዘክሮው ካለው ወቅታዊው ጠቅላይ ቀውስ በመንደርደር በማስተንተን ሁነት አድርጎ ለመኖር ነው። ስለዚህ የእምነት ቀውስ አለ ቦሎ ለመናገር ቤተ ክርስትያን አትፈራም፣ የእምነት አዋጅ ይኸንን የሚመለከት ነው ብለዋል።
በዚህ ሃይማኖትና ግብረ ገብ የሚያገል ዓለማዊነት፣ እግዚአብሔረ እንደሌለ አድርጎ የመኖር ባህል ልማድ እያስፋፋ ላለው ዓለም ዓለም፣ አማኞች በታደሰ እምነታቸው አማካኝነት በቃልና በሕይወት የተሸኘ ምስክርነት ሥር አዲስ አስፍሆተ ወንጌል እንዲያቀርቡ የሚያግዝ ነው። የቅዱስ አባታችን ፖርታ ፊደይ ሐዋርያዊ መልእክት መሠረትም የእያንዳንዱ ምእመን ዕለታዊ ሕይወትና ወቅታዊው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ሆኖ እንዲቀርብ የሚያስገነዝብ ነው ብለዋል። በዚሁ ዘርፍም የሥርዓት አምልኮና የቅዱሳት ምሥጢራት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር በትክክል ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል የሚገባ የተደረሰው የገዛ እራሱ የቅዳሴ ሥርዓት ሊጡርጊያ መመሪያ መደንገጉንም አስታውሰው፣ እያንዳንዱ የተለያዩ የቤተ ክርስትያን ማኅበራት እና እንቅስቃሴዎችም በእምነት ዓመት መሠረትም አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለቤተ ክርስትያን እድገት የጋራ ሱታፌ አካፋይ ወይንም መሠረታዊ ነገር ነው።
የመጀመሪያ ቀን የእምነት ዓመት ይፋዊ የመግቢያ ቀን ጥቅምት 21 ቀን 2012 ዓ.ም. ስድስት የእምነት አናዛዥ አበ ነፍሳት ሰማዕታት ብፅዕና የሚታወጅበት ዕለት መሆኑ ገልጠው፣ በ 2013 ዓ.ም. በሪዮ ደ ጃይነሮ ለሚካሄደው ለዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለዓለማውያን ምእመናን በወንድማማችነትና በሕዝብ መንፈሳዊነት ገጠመኝ የማካኝነት ለማነጽ የሚያግዙ የተለያዩ ጅማሬዎችም ይኖሩታል ካሉ በኋላ ሕዝባዊ መንፈሳዊነት አስፈላጊ የእምነት ሕይወት መግለጫ ነው። ይኽ ሲባልም ቅዱሳት ሥፍራን ከመንፍሳዊ ንግደት ጋር በማያያዝ የሚመለከት መሆኑ በማብራራት፣ ስለ እምነት ዓመት በተመለከተ በሚገባ ማስታወቂያና መግለጫዎች ለማግኘትም ዳብሊው ዳብሊው ዳብሌው አኑስፊደይ ነጥብ ቪኤይ የተሰየመው ድረ ገጽ ለመጎብኘት እንደሚቻል ገልጠው የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አጠናቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.