2012-06-23 08:43:14

የቅድስት መንበር አቋም ስለ ምሥራቅ ኢየሩሳሌም ጉዳይ


በሮማ በተካሄደው የምስራቅ አቢያተ ክርስትያን ደጋፊ ተግባር ጉባኤ የተሳተፉት በእስራኤልና ፍልስጥኤም የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ፍራንኮ በቅርቡ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ቅድስት መንበር ስለ ምስራቅ ኢየሩሳሌም ያላት የአቋም እንደ ለወጠት የሚያስመስል የሰጡት RealAudioMP3 ዜና በተመለከተ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የመገናኛ ብዙሃን የሰጡት ዜና በማስተባበል፣ የቅድስት መንበር አቋም ያለ ሆኖ፣ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. አቋሙ መሠረትም ከፍልስጥኤም ጋር በመወያየት ስምምነት የተደረገበት ለሰላም የውይይት ሰነድ እንዱ መሠረት መሆኑ ተፈራርመውበታል። ስለዚህ ቅድስት መንበር ከእስራኤል ጋር እያካሄደቸው ያለው ውይይትና ይረጋገጣል የምትለው የጋራው ስምምነት፣ በእስራኤል የምተገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የግብር ክፍያ ጉዳይ እንዲሁም የቤተ ክርስትያንዋ እንቅስቃሴና አገልግሎት በእስራኤል የሚመለከት ነው። ስለዚህ ይህ ከእስራኤል ጋር የምታካሂደው ውይይት ቅድስት መንበር ስለ ምስራቅ ኢየሩሳሌም ካላት አቋም ጋር የሚያገናኝም ምንም ነገር የለውም፣ ለፍልስጥኤም ብሔራዊ መንግሥት ጭምር በትክክል የተገለጠ ጉዳይ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.