2012-06-23 08:40:40

ብፁዕ ካርዲናል ሸረር፦ ቅድስት መንበር ስለ ሕይወትና አካባቢ ጥበቃ


ከትላትና በስትያ 20 ዓመት ስለ መሬት ጉዳይ በተመለከተ የተካሄደው ጉባኤ በሚታወስበት ዕለት ይኸው ተቀባይነት ስላለው የልማት እቅድ ዙሪያ የቡድን ሃያ የሁለት ቀናት ጉባኤ ትላትና መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ ይህ ስለ የአካባቢ መጻኢ እድል ላይ በማነጣጠር ከተካሄደው ጉባኤ ጎን የሕዝቦች ጉባኤ RealAudioMP3 በሚል መጠሪያ የተለያዩ የተቃውሞ መርሃ ግብሮች መከናወናቸውም የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ አምብሮጀቲ አስታወቁ።
ይህ በብራዚል ሪዮ ደ ጃነይሮ ከተማ የተካሄደው የቡድን 20 ጉባኤ የተወያየበት ሰነድ ብዙ በሚያሳድረው ጉጉትና ከዓለም አቀፍ ምኞች አንጻር ሲታይ ደካማ ነው በማለት የተለያዩ የዓለም አቀፍ ታዛቢ አካላት አስተያየት የሰጡበት ሲሆን፣ በዚህ ጉባኤ የቅዱስ አባታችን ልዩ ልኡክ በመሆን የተሳተፉት የሳን ፓውሎ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኦዲሎ ፐድሮ ሸረር ከቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የቡድን 20 ጉባኤ፣ የተለያዩ አበይት የዓለም አቀፍ መሪዎች የበለጸጉት ታላላቅ አበይት አገሮች መሪዎች የሚያገናኝ ነው። ከዚህ ጉባኤ ውጭ በጉባኤ ተሳታፊያን የተለያዩ አገሮች መንግሥታት ድርገቶችና በቅድስት መንበር ልኡካን መካከል ግኑኝነት መካሄዱ ብፁዕነታቸው ገልጠው፣ የውይይቱ ሰነድ ተቀባይነት ላለው ልማት አስፈልጊና መሠረታዊ የሆኑትን ሊደረሱ የሚገባቸው ግቦች የተኖረበት ነው። ለምሳሌም ሕይወት ለማቀብና ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ ፈጽሞ መነጣጠል እንደሌለበት የሚያሳስብ በድኽነት ጫንቃ ሥር የሚገኙት አገሮች በበለጸጉት አገሮች ሊደገፉ እንደሚገባቸውና ልማት በመተባበር የሚል መሆኑ ገልጠዋል።
ቅድስት መንበር በተባበሩት የዓለም አቀፍ ድርጅት የቋሚ ታዛቢነት መብት ሲኖራ፣ ሆኖም ይህ የሪዮ ጉባኤ የተባበሩት መንግሥታት የጠራው ሳይሆን የኅብረ-ብሔራውያን መንግሥታት ጉባኤ ነው። ስለዚህ በዚሁ ጉባኤ ቅድስት መንበር ሱታፌ ባለ ሙሉ መበት ነው። በጠቅላላ በዚህ የሪዮ ጉባኤ ሥር ባካሄደቻቸው ክሌአዊ ግኑኝነቶች እንደ የታዛቢነት መብት ሳይሆን እንደ ባለ ሙሉ መብት አገር ሆና ነው የቀረበቸውም የተገለጠችውም በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.