2012-06-23 08:36:30

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ጥልቅ ልባዊ ሀዘን የሚያንጸባርቅ ለሶሪያ የሰላም ጥሪ አቀረቡ


የምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን የድጋፍ ተግባር 85ኛው ጠቅላይ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም. የምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ለዮናርዶ ሳንድሪ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ተጀምሮ እ.ኤ.አ. 21 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በአገረ ቫቲካን በቅዱስ ቀለመጦስ ሓዋርያዊ አዳራሽ ተጋባእያኑን በመቀበል በሰጡት ሥልጣናዊ መሪ ቃል መጠናቀቁ የቅድስት መንበር RealAudioMP3 መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ ኣባታችን ባሰሙት ሥልጣናዊ ንግግር፣ ሶሪያ ከታመሰችበት ወቅታዊው ዓመጽ ትገላገል ዘንድ፣ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አለ ማመንታት መላ ኃይሉንና ብቃቱን አጣምሮ ያላሰለሰ ጥረት እንዲያደርግ፣ ለህዝብ ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት የዋስትና ጥሪ በማቅረብ መላ ሶሪያና ሕዝቧን ስቃዩንና መከራውን በጥልቅ በማስተዋል የገዛ እራሳቸው ስቃይ በማድረግ በሶሪያ አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሰላም እንዲረጋገጥ፣ ረዥሙ አመጽና ቀውስ መላ አገሪቱ የአመጽ አውድማ በማድረግ መወጣጫ ወደ ማይገኝለት ውስጣዊና ክልላዊ ሁከት ከማሸጋገሩ በፊት የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ለሰላም ያልታከተ ጥረት እንዲቆም በማሳሰብ ሰላም የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ እንዳብራሩ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
በክርስቶስ ላይ የጸናው የወንድማማችነትና የመተሳሰብ መንፈስ በጸሎት በመተሳሰብ፣ ለሶሪያ እንዲጸለይ፣ ሕዝቡ ተስፋውን እንዳያመነምን የኩላዊት ቤተ ክርስትያን ጸሎት የማጽናኛ ቅብአ ቅዱስ እንዲሆንለት፣ ለመንግሥታት አካላትም ጥበቡን እንዲያድላቸው አመጽ ስቃይና ሞትን እንጂ ሰላም የማያስገኝ በመሆኑ ያለው ሁኔታ ለእርቅ ለስምምነትና ለሰላም ቦታ ይተውም ዘንድ የሚማጠን ነው።
በዚህ በተካሄደው ለምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን የድጋፍ ተግባር ጉባኤ ለእስራኤልና ለፍልስጥኤም የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ አንቶኖዮ ፍራንኮ የሚገኙባቸው ከቅድስት መሬት የተወጣጡ በህንድ የሶሪያ ማላባረስ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጆርጅ አለንቸርይ በኡክራይን የግሪክ ሥርዓት ለምተከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስታይን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ስቪኣቶስላቭ ሸቭቹና በሶሪያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ዘናሪ መሳተፋቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን በአበይት የቤተ ክርስትያን አካላት ተሳታፊነት የቤተ ክርስትያን ኵላዊነት ባህርይ መግለጫ ከመሆኑም ባሻገር በሁሉም አገር የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የእይታዋ ማእከል የኵላዊነት አድማስ ማደሪያ ወደ ሆነችው የሮማ ቤተ ክርስትያን መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማስታወስ፣ ሁሉም የምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን መንፈሳዊና ቁሳዊ ድጋፍ እንዳይለያቸው አደራ ካሉ በኋላ በምሥራቅ ክልል የሚታየው ጥንታዊና ታሪካዊ መቃቃር በክልሉ ሰላማዊ የጋራው ኑሮ ውይይትም በቀላሉ ሊደፈርስ ከሚያደርጉት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ መሆኑ አብራርተው፣ የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን የጋራው ውይይት እንዲጠነክርና የሰብአዊ መብትና ክብር በተለይ ደግሞ ግላዊና ማኅበራዊ የሃይማኖት ነጻነት ዋስትና እንዲያገኝ አደራ ማለታቸውንም የጠቆመው የቅድስት መንበር መግለጫ አይያዞም የሃይማኖት ነጻነት በባህል ደረጃ ሳይሆን በብሔር ደረጃ ማለትም በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት፣ በሕንጸት መርሃ ግብሮች፣ በሰብአዊና በመንፈሳዊ እርዳታ አቅርቦት መስክ ሁሉ መገለጥና መኖር ያለበት በመሆኑም ያለው የሃይማኖት አድማስ ሊከበር ይገባዋል። ቤተ ክርስትያን በተለያዩ ማኅበሮችዋ በኩል ተጨባጭ የክርስቶስ የሚሰዋው ፍቅር ምልክትና ተግባርም በመሆን ለዓለም የቤተ ክርስትያን እውነተኛ መለያዋና ተልእኮዋ ህልው በማድረግ ፍቅር ለሆነው እግዚአብሔር የምታገለግል መሆንዋ ትመሰክራለች፣ በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን የእምነት ዓመት ለዚህ ለምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን የድጋፍ ፣አተግባር ፍርያማነት አስተዋጽኦ እንዲኖረው ለሚሰጠው አገልግሎትና ድጋፍ ሊከተለው የሚገባው መንገድ የሚያበራ ነው፣ ለሁሉንም አቢያተ ክርስትያን አባታዊና ወንድማዊ ፍቅራቸውን በማረጋገጥ ሐዋርያዊ ቡራኪ በመስጠት ያሰሙት ሥልጣናዊ ንግግር ማጠናቀቃቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.