2012-06-20 19:06:03

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን። በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን። በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ። በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን። በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።” (ኤፌ 1:3-11)
ውድ ውንድሞችና እኅቶች፧ በቅዱስ ጳውሎስ መልእክቶች ስላለው ጸሎት የማቅረበውን አስተምህሮ በመቀጠል ዛሬ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኤፌውሶን ሰዎች በጻፈው መልእክት መጀመርያ ላይ ያሰፈረውን ትልቅ የምስጋናና የቡራኬ ጸሎት እናስተነትናለን፣ ቅዱስ ጳውሎስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት የሆነውን አምላካችንን የእርሱ ዘለዓለማዊ የደህንነት ዕቅድ የሆነውን “የፈቃዱ ምሥጢርን ስላሳውቀን” “በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤(ኤፈ 1፡9) በማለት ይባርከዋል፣ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እግዚአብሔር ልጆቹ እንድንሆንና የክብር ውርሻችንን እንድንቀበል በኢየሱስ ክርስቶስ መርጦናል (1፡4) “ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።” በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ደም የመሐሪ ፍቅሩ ጥልቀት አሳየን፣ ኃጢአታችንን ይቅር አለለን፣ ከእርሱ ጋርም አስታረቀን፣ ጊዜው በደረሰ ወቅትም በመንፈስ ቅዱስ ስጦታም የወሳኙ ደህንነታችን ማኅተምና ስለት ሰጠን፣ የቅዱስ ጳውሎስ ጸሎት በታሪክ የሚገለጠውን የእግዚአብሔር የደህንነት ዕቅድ በማስተንተን በሕይወታችንና በቤተክርስትያን ሕይወት ያሉትን ት እምሮቶች እንድረዳ ይጠራናል፣ በጸሎታችን በክርስቶስ ስለመመረጣችን ምሥጢር እግዚአብሔርን እንወድስ፤ ሕይወታችንና ልቦቻችንን ዘወትር ለሚለውጠን የቅድስት ሥላሴ ህላዌ ክፍት እናድርግ፣
የናይጀርያ ሽብር እንዲቆም ያቀረቡት ጥሪ፧
ከናይጀርያ የሚደርሰን ያለው፡ ሽብርተኞች በተለይ በክርስትያን ምእመናን ላይ የሚፈጽሙት ያለ ዓመጽን የሚገልጥ አስጨናቂ ዜና በጥልቀት እየተከታተልኩት ነው፣ የዚህ ሽብር ሰለባ በመሆን ለሞቱትና ለሚሰቃዩ ስጸልይ ለዚሁ ዘግናኝ የሽብር ተግባር ኃላፊዎችን የብዙ ንጹሓን ሰዎች ደም ማፍሰስ ወዲያውኑ እንዲያቆሙ ጥሪ አቀርባለሁ፣ በተጨማሪም የመበቀል እርምጃ በመውሰድ ሌላ የባሰ ሽብር እንዳይነሳ፤ የናይጀርያ ኅብረተሰብ ተቋሞች ሁላቸው እንዲተባበሩና የሃይማኖት ነጻነት መብት የሚያከብር የሰላምና የዕርቅ ኅብረተሰብ እንዲያቋቋሙ አደራ እላለሁ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.