2012-06-18 13:39:58

የብፅዕና አዋጅ


እ.ኤ.አ. ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢጣሊያ ቪተርቦ ክፍለ ሃገር በምትገኘው በነፒ ከተማ እናቴ ቸቺሊያ ኤውሰፒ ሦስተኛ ደረጃ የቅድስት ድንግል ማርያም አገልጋዮች የደናግል ማኅበር አባል እ.ኤ.አ. በ 1928 ዓ.ም. ገና በ 18 ዓመት እድሜዋ ባደረባት ከባድ በሽታ ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየች፣ RealAudioMP3 መስቀልን በሙላት በመቀበል መላ ሕይወቷ ሙሉ በሙሉ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስጠት የኖረች በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ውሳኔ መሠረት ቅዱስነታቸውን በመወከል የቅድስትና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ አማካኝነት በይፋ ብፅዕና እንደታወጀላት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቸቺሊያ ኤውሰፒ ገና በዘጠኝ ዓመት እድሜዋ ቅድስት ተረዛ ዘ ሊሰ የአንዲት ነፍስ ታሪክ በሚል ርእስ ሥር የደረሰችው መጽሐፍ በማንበብ፣ ለቅዱስ ቁርባንና ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት ልዩ የአክብሮት መንፈሳዊነት ቀናተኛ በመሆን ሕይወቷ በሙሉ ካለ ምንም ማመንታት ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለማዋል በመመኘት በዚህ ቀናተኛ ፍቅር ስትኖር በ 18 ዓመት ዕድሜዋ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየች መሆንዋ ብፁዕ ካርዲናል አማቶ ባሰሙት ስብከት ገልጠው፣ ልክ የዛሬ ሁለተ ዓመት በፊት ቅድስት ቤተ ክርስትያን ብፅዕና ያወጀችላት የ 18 ዓመት ዕድሜ ወጣት የአፍቅሮተ ዘቤት አባል ኪያራ ባዳኖ በማስታወስም፣ ምንም’ኳ በ18 ዓመት የወጣትነት ዕድሜ ከዚህ ዓለም የተለየች ብትሆንም፣ የነበራት መንፈሳዊ ሰብአዊ ብስለት ከነበራት ዕድሜ የላቀ፣ ሁሉንም በእምነት ዓይን በማንበብና በመኖር ያጋጠማት ሁሉ በእምነት ልዩ ትርጉም ለመስጠት የበቃች የቤተ ክርስትያን ልጅ በማለት ከገለጡዋት በኋላ፣ ባደረባት ሕመም የሥጋ ስቃይ ቢታይባትም በዚሁ ሳትበገር በጸና የጸሎት መንፈስ ተግታ፣ ስቃይ ገዛ እራሷ ለክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ለመሰዋት የላቀ የፍቅር መግለጫ ነው በሚል ትርጉም የኖረች ነች። ሊከተለኝ የሚወድ ገዛ እራሷን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ በማለት ጌታችን ኢየሱስ የተናገረው ቃል በመቀበል በታማኝነት የኖረቸው ጥሪ የሚመሰክር የቅድስና ታሪክ ነው ብለዋል።
ይህችን ወጣት ብፅዕት የጽናትና የተስፋ መልእክተኛ በማለት ብፁዕ ካርዲናል አማቶ ከገለጡዋት ብኋላ፣ የዘመናችን ወጣቶች የእርሷ አብነት እንዲከተሉ አደራ በማለት፣ ወጣት ትውልድ ልቦናውና እይታው ወደ ሰማይ ቀና በማድረግ ልቡና አእምሮው ወደ የዘለዓለም ሕይወት አድማስ ላይ በማነጣጠር እንዲኖር በብፅዕት ቸቺሊያ አማላጅነት ጸልየው ያሰሙት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.