2012-06-18 13:43:18

የብሔር አየር ማረፊያ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት


“አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በብሔር የአየር ማረፊያ” በሚል ጠቅላይ ርእስ ሥር የስደተኞችና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያዘጋጀው 15ኛው ዓለም አቀፍ የብሔር አየር ማረፊያ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መሪዎችና ተባባሪዎቻቸው የካቶሊክ ካህናት ጉባኤ ባለፈው ሳምንት መከናወኑ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ስለ ጉባኤው በማስመልከትም የስደተኞችና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት RealAudioMP3 ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የተካሄደው ስብሰባ አወንታዊ ነበር፣ ስብሰባው በካርዲናሎች የጉባኤ አዳራሽ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መሪ ቃል በመቀበል የተጀመረ መሆኑ ገልጠው፣ “የሰው ልጅ ማእከል የማድረጉ ሂደት በሁሉም መስክ ገቢራዊ እንዲሆንና ይኽንን ሰብአዊነት ማእከል የማድረጉ ጥረት የሚያሰናክሉ በተጨባጩ ዓለም በተለያዩ መስኩ ጎልተው የሚታዩት በተዛማጅ ባህልና በአለማዊነት አመለካከት የሚጋባው እምነት የማግለሉ ዝንባሌ እንዲወገድ ቅድስት ቤተ ክርስትያን ከምታነቃቃው ዘርፈ ብዙ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ውስጥ ይህ የብሔር አየር ማረፊያ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት አንዱ መሆኑ በማስታወስ፣ በዚህ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ተልእኮ ወንጌል የሚፈጽሙ ካህናት ሰብአዊነት ያስቀደመ ባህል እንዲያነቃቁ አደራ እንዳሉ ያስታወሱት ብፁዕ ካርዲናል ቨሊዮ፣ በዚሁ ሐዋርያዊ ተልእኮ የሚያገለግሉ ሁሉ ቃል እግዚአብሔርን በቃልና በሕይወት በማቅረብ ክርስቶስን እንዲያገለግሉ የተጠሩ መሆናቸው የተሰመረበት ጉባኤ ነበር ብለዋል።
ተጋባእያኑ ቅዱስ አባታችን ባቀረቡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ የብሔር አየር ማረፊያ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት አባላት ተጓዦችና በዚሁ የአገልግሎት መስጫ በሆነው ክፍለ ከተማ የሚገኙት ለሚተላለፉት ሰብአዊና መንፈሳዊ ሕንጸት ለማቅረብ ብቃት ያላቸው ሆነው መገኘት ይጠበቅባቸዋል፣ በማለት ያመለከቱት ሐሳብ ያለው አንገብጋቢነት መገንዘባቸውና እንዲህ በመሆኑም ተገቢ እና ልዩ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ለመገንዘብ እንዳበቃቸው ቀርበው ለማረጋገጥ እንደቻሉ ከገለጡ በኋላ ከዚህ ግንዛቤ በመንደርደርም ቤተ ክርስትያን ለተጓዦች የምታቀርበው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ለተጓዦች ጥያቄ የሚገባ እንዲሆን በቋንቋም ሆነ በሥልት ብቃት ያለው መሆን እንዳለበት ጠንቅቃ የምታውቀው መሠረተ ሐሳብ መሆኑ ቅዱስ አባታችን የገለጡት ቃል የዚህ ሓዋርያዊ አገልግሎት ኃላፊነት የሚያብራራ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.