2012-06-18 13:45:00

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ


ሶሪያና ሕዝቧ ችላ እንዳይባል የሶሪያ ሕዝብ ወቅታዊ ሁኔታ የሚያስገነዝበው ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታም መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓነቅጽ በመቀጠል፣ በሶሪያ ያንዣበበው RealAudioMP3 ጨለማ ሕዝቡና አገሪቱን ለአደጋ ያጋለጠ ሲሆን፣ የሚታየው አስከፊው አመጽ አብቅቶ ሰላማዊ ሕይወት እንዲረጋገጥ የሁሉም ፍላጎት ነው ብለዋል።
አባ ሎምባርዲ የሶሪያ ሕዝብ ጥሪ ላይ ያተኮረ ባቀረቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በአገሪቱ በተለያዩ ክልሎችና ከተሞች የሚታየው የዛሬ 15 ወር በፊት የተቀጣጠለው ግጭት እልባት ያጣ እንደሚመስልና፣ ብዙዎችም የእርስ በእርስ ጦርነት ነው በማለት እንደሚገልጡት ጠቅሰው፣ ኅብረ ኅብረተሰብ፣ ኅብረ ሃይማኖትና ኅብረ ባህል የጸናባት ሰላማዊ ማህበራዊ ኑሮ የሚታይባት ሶርያ ቀስ በቀስ ወደ ሲዖል እያዘገመች ትመስላለች፣ በማለት በአገሪቱ ያለው አመጽና ስቃይ ምን እንደሚመስል በሶሪያ ለቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ ኣቡነ ዘናሪን የገለጡት ሃሳብ በማስታወስ፣ ነጻነት የሕዝብ ተሳትፎ የጎላበት ፖለቲካ መረጋገጥ ሕዝብ በተለይ ደግሞ ወጣት የኅብረሰብ ክፍል የሚያቀርበው ጥሪና የሚገልጠው ፍላጎት በመንግሥታት ችላ እየተባለ፣ በተለያዩ አገሮች ለተለያዩ ችግሮች መንስኤ እየሆነ ይኸንን ውጥረት በመጠቀምም ሁከትና ብጥብጥ ለሚሹት ተቃዋሚዎች ጥቃትና አመጽ አመች መሆኑም እየታየ ነው። ቅዱስ አባታችን የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች የፖለቲካ አካላት ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ያቀረቡት የሰላም ጥሪ አወንታዊ ምላሽ አለ ማግኘቱና የሶሪያ መረጋጋት ለመካከለኛው ምስራቅ ሰላማዊ ሁኔታ ሚዛን መሆኑ አባ ሎምባርዲ ገልጠው፣ የተባበሩት መንግሥታት የቀረበው የሰላም ሰነድ አለ መከበሩ በማብራራት፣ የዓለም አቀፍ ወታደራዊ ኃይል ገብነት አስፈላጊ ነው ተብሎ የሚገለጠው ሃሳብ አሳሳቢ ነው ካሉ በኋላ የሰላም የውይይት መድረኮች ይነቃቁ ዘንድ በማሳሰብ የሶሪያው ሁከት በሰላማዊ መንገድ እንዲፋታ በሚደረገው ጥረት ተስፋ እንዳይቆረጥ የሁላችን ጸሎት ነው በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.