2012-06-18 13:41:51

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ፦ “ጸሎት የመብራት ቦግታ ነው”


ትላትና የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፉ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ በቅዱስ ዮሓንስ ሮቶንዶ የተገኙት ዓለም አቀፍ የቅዱስ ፒዮ ዘፐትራልቺና የጸሎት ማኅበር ጉባኤ ፊት ተገኝተው ባሰሙት ሥልጣናዊ አስተምህሮ እነዚህ የጸሎት ማኅበራት ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል የተጋረጠበት መሰናክል ለማሸነፍ RealAudioMP3 ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.ና ለብፁዓን ጳጳሳት ጥሪ የተገባ መልስ ለመስጠት ዝጉጁዎች መሆን አለባቸው በማለት የጸሎት ማኅበራት ሊከተሉትና ሊያከብሩት የሚገባቸው ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ያጸደቀችው አዲሱ ደንብ በይፋ በማብራራት ማስተዋወቃቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ገለጠ።
አዲሱ መመሪያ እ.ኤ.አ. በ 1986 ዓ.ም. የነበረው ደንብ የሚከተልና ቀጣይ ያደረገ ሆኖ፣ የግልና የኅብረት ጸሎት ላይ በማተኮ፣ር በፍቅር አገልግሎት መትጋት የሚል የሕይወት ባህል መስካሪያን ቤተሰብ ቤተአዊ ቤተ ክርስትያን መሆንዋ የሚገልጥ ሆኖ መገኘት እንዳለበት የሚያሳስብ መሆኑ ብፁዕነታቸው በማብራራት፣ እሴቶችና ግብረ ገብ በመከተል ለይቶ ለመኖር የሚያግዝ በተዛማጅ ባህል ለተጠቃው ኅብረተሰብ ሊከተለው የሚገባው የሕይወት መንገድ ለይቶ ለመክተል እንዲችል ምስክርነት የሚያቀርብ የጸሎት ቡድን መሆን ይጠበቅበታል የሚል መሠረታዊ ሃሳብ የሰፈረበት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.