2012-06-15 14:42:10

የሥነ ስፖርት ባህል ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ


የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤትና የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት በመተባበር ስፖርት ወደ ፍጹምነት ክፍት ለሆነው ሰው ልጅ እርባና በሚል ርእስ ሥር ትላንትና ጧት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት በአገረ ቫቲካን አዘጋጅነት በተካሄደው ዓወደ ጥናት ፍጻሜ RealAudioMP3 አንድ የሥነ ስፖርት ባህል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ቢሮ እንዲቋቋም የቀረበው ሃሳብ እንደተቀበሉት አወደ ጥናቱን የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሉካ ኮሎዲ አስታወቁ።
በአውደ ጥናቱ ፍጻሜ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ስፖርት፣ ስፖርተኞችና ደጋፊዎች የሰው ልጅ በኑባሬ ወደ ፍጹምነት ያቀና ባህርዩ እንዲያከብርና እንዲንከባከብ የሚያግዘው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት ለማነጽ ታቅዶ ብዙውን ጊዜ ስፖርት ጤናማው ተግባሩንና ትርጉሙን የሚጎዱ አንዳንድ በስፖርት መድረኮችና በአንዳንድ ስፖርተኞች ደጋፊዎች አማካኝነት የሚፈጸሙት መጥፎ ተግባሮች እንዳይኖሩ የሚያግዝም ይሆናል ብለዋል።
ስፖርት፦ የሰብአዊ ተግባር፣ በተለየ መልኩም ወጣቶችን የሚያሳትፍ በሦስተኛ ደረጃ ለሰብአዊ እድገት መሣሪያ መሆኑ በመገንዘብ፣ እነዚህ ሦስት ደረጃዎችን በማጤን የስፖርት ቲዮሎጊያዊ፣ መንፈሳዊ፣ ሥነ ሰብአዊ ገጽታው በጥልቀት ተረድቶ ለማስገንዘብና ለማሳወቅ ሰብአዊና መንፈሳዊ እድገት ላይ ያነጣጠረ እቅድ መሆኑ አብራርተው፣ ስፖርት ድል አድራጊነት ብቻ የሚል ሳይሆን ሰብአዊ ግኑኝነት፣ ጤናማ ድል፣ አወንታዊ ውድድር የሚታይበት መሆን አለበት። አሸናፊነት ደስ የሚያሰኝ ድል ነው። ሆኖም ግን ተሸናፊው አካል የሚያንቋሽሽ፣ ሥፍራ እንደሌለው የሚያደርግ፣ የሚያገል መሣሪያ መሆን የለበትም። በጠቅላላ ስፖርት ከጠጨባጩ ዓለም ጋር የተቆራኘም በመሆኑ፣ ያለው ኅብረ-ግኑኝነቱ ለምሳሌ ከኤኮኖሚ ጋር ያለው ትስስር በሥነ ምግባር የተካነ ግኑኝነት እንዲሆን የሚያግዝ ሐዋርያው ግብረ ኖልዎ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.