2012-06-15 14:40:35

ቅድስት መንበርና የቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ የካህናት ወንድማማችነት ማኅበር ግኑኝነት


የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ትላትና ጧት በኵላዊት ቤተ ክርስትያን የሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ የ“Pontificia Commissione Ecclesia Dei - ጳጳሳዊ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስትያን ተንከባካቢ ድርገት” ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዊሊያም ለቫዳ ከትላትና በስትያ የካህናት ወንድማማችነት ቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ ማኅበር ጠቅላይ አለቃ RealAudioMP3 ብፁዕ አቡነ በርናርድ ፈልይ መካከል በካቶሊክ የሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ሕንጻ ተቀብለው ሁለት ሰዓት የፈጀው ያካሂዱት የጋራ ውይይት በማስምልከት ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ተገለጠ።
የሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር እ.ኤ.አ. መስከረም ወር 2011 ዓ.ም. ለቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ የካህናት ወድማማችነት ማኅበር የሰጠው የሥርወ እምነት ሕጋዊ የመግቢያ ሰነድ በማስደገፍ የፒዮስ ማኅበር እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2012 ዓ.ም. በተራው ለሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር የሰጠው ሰነዳዊ መልስ ላይ ያተኮረ ግኑኝነት እንደነበር አባ ሎምባርዲ ገልጠው፣ የቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ የካህናት ወድማማችነት ማኅበር መልስ በተገባ የጊዜ ገደብ የደረሰ ነው። በእውነቱ ይህ በሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተና በቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ የካህናት ወድማማችነት ማኅበር መካከል የተካሄደው ግኑኝነት፣ በዚህ እ.ኤ.አ በተያዘው ዓመት ሐምሌ ወር የቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ ማኅበር ለሚያካሂደው ጠቅላይ ጉባኤ ርእሰ ጉዳይ እንደሚሆንና ጠቅላይ ስብሰባውም የተካሄደው ግኑኝነትና የተሰጠው መልስ ዙሪያ በመወያየት ግምገማ እንደሚሰጥበት አባ ሎምባርዲ ገልጠዋል።
በብጹዕ ካርዲናል ለቫዳና ብፁዕ አቡነ ፈለይ መካከል የተካሄደው ግኑኝነት የቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ የካህናት ወንድማማችነት ማኅበር በኵላዊት ቤተ ክርስትያን ሕገ ቀኖናዊ እውቅና ከተሰጠው በሚል አወንታዊ ቅድመ አስተያየት መሠረትም፣ የቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ የካህናት ወድማማችነት ማኅበር በሐዋርያዊ መንበር በኵል የሚቆመው በገዛ እራሱ ግላዊ ነገር ግን በቀጥታ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን ሐዋርያዊ መንበር ትእዛዝ ሥር በሚመራ በጳጳሳዊ ሥልጣን ሥር እንዲተዳደር የሚል ከሁኔታው ጋር የሚስማማ ሃሳብ የሠፈረበት መሆኑ አባ ሎምባርዲ አብራርተው፣ ይህ የቀረበው ሃሳብ ከዚህ በፊት በቅድስት መንበርና በቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ ማኅበር መካከል ያለው ሥርወ እምነታዊ ልዩነት መፍትሄ ያገኘ እንደሆነ ነው የሚለው ሃሳብ ያለው አስፈላጊነቱ ተሰምሮበት እንደነበርም አስታውሰዋል። ስለዚህ ሙሉ ውህደት ብሎ ማሰብ የሚቻል ነው ብለዋል።
አባ ሎምባርዲ ቀጥለውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 እ.ኤ.አ. ከመስከረም 14 ቀን እስከ መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ.ም. በሊባኖስ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያካሂዱና ይኽ ሐዋርያዊ ጉብኝቱ ለማሰናዳት የሚከናወኑት ቅድመ ዝግጅቶችን የሚያጠናውና የሚከታተለው ቡድን በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ሊባኖስ እንደሚጓዝ ነው ብለዋል። ስለዚህ ቅድስት መንበር በሶሪያ ያለው ወቅታዊው ሁኔታ የቅዱስ አባታችን በሊባኖስ ሊያካሂዱት የወሰኑት ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠራጣሪ ያደርገዋል እንደማትል ገልጠዋል።
ከፊታችን ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ለበጋ የዕረፍት ወቅት ሮማ አቅራቢያ በምትገኘው ከተማ ጋስተል ጋንዶልቾ ወዳለው ሓዋርያዊ ሕንጻ እንደሚሄዱና በዚሁ የዕረፍት ወቅት የር.ሊ.ጳ. ሳምንታዊ የዕለተ ረቡዕ አስተምህሮ ትምህርተ ክርስቶስ እንደማይከናወን ሆኖም ግን በየእህዱ እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር እንደሚመሩና እ.ኤ.አ. ሐምሌ 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው በፍራስካቲ መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚመሩና ለክብራቸውም ሁለት የተለያዩ የውሁድ ጥዑም ሙዚቃ ትርኢቶች እየተዘጋጀ መሆኑ ነው ካሉ በኋላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እፊታችን እሁድ በዱብሊን በማሄድ ላይ ያለው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ መዝጊያ ምክንያት በልሳነ-ምስል ግኑኝነት አማካኝነት መሪ ቃል እንደሚሰጡ ገልጠዋል።
እፊታችን ሓሙስ የእምነት ዓመት መርሃ ግብር ዙሪያ በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን፣ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል የምስክር ወረቀት ያላቸው የዓለም አቀፍ ልኡካን ጋዜጠኞች በአገረ ቫቲካን የሚገኘው IOR - የሃይማኖት ተግባር ማስፈጸሚያ ተቋም እንደሚጎበኙ በማስታወስም የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.