2012-06-11 14:54:48

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “ኅላዌ ቤተ ክርስትያንና ቅዱስ ቁርባን ለሁሉም”


የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል ቅዳሜ እ.ኤ.አ. ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. ኅላዌ ቤተ ክርስትያንና ቅዱስ ቍርባን ለሁሉም በሚል ርእስ ሥር በቅዱስ ቍርባን ሱታፌ RealAudioMP3 ባይኖርም ከቤተ ክርስትያን ጋር ሙሉ ውህደት እንዳለን መገንዘብ ይኖርብናል፣ በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ከግንቦት 30 ቀን እስከ ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚላኖ በተካሄደው ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ተገኝተው በሰጡት ሥልጣናዊ ትምህርት የገለጡት ሃሳብ ሲያብራሩ፣ በርግጥ ቅዱስ ቍርባን ለመቀበል የሚያግዱ ምክንያቶች ቢኖሩም አለ መቀበል ከቤተ ክርስትያን ጋር ለሚኖረን ውህደት የሚያሰናክል መሆን የለበትም፣ ስለዚህ ላለ መቀበል የሚያነቃቃ እንዳልሆነ የሚያመለክት መሆኑ ገልጠው፣ ቅዱስነታቸው ምሥጢረ ተክሊክ ያፈረሱት የቤተ ክርስያን ልጆች ላይ በማተኮር ያስተላለፉት ሥልጣናዊ ሃሳብ መሆኑ ኣባ ሎምባርዲ ባቀረቡት ርእሰ ዓንቀጽ በማብራራት፣ አክለውም ሓሙስ ቅዱስነታቸው “Corpus Domini- ቅዱስ ሥጋሁ ወክቡረ ደሙ” ዓቢይ በዓል ምክንያት በቅዱስ ዮሐንስ ዘ ላተራኖ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴና የቅዱስ ቁርባን ፊት የሚደረገው ሥርዓተ ቡራኬና በቅዱስ ቁርባን የተመራ ዑደት እስከ ባሲሊካ ቅድስት ማርያም ማጆረ በመምራት ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት፣ ቅዱስ ቁርባን በቅዳሴ ሥነ ሥርዓት የሚታጠር ሳይሆን ከቅዳሴ ውጭ ጭምር የሚኖር መሆኑ በመግለጥ፣ እርሱም የጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ኅያው ኅላዌ በሁሉም ሥፍራ የሚል መሆኑ ገልጠዋል።
የቅዱስ ቁርባን ኅላዌ እውነተኛነቱና ተጨባጭነቱ ለክርስትያናዊ ሕይወት መሠረት ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሚላኖ በተካሄደው ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ተገኝተው፣ ምሥጢረ ተክሊል ያፈረሱ፣ ከሥርዓት ውጭ በሆነ ጋብቻ ውስጥ የሚገኙትን በማሰብ፣ ምንም’ኳ ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል የተቆጠቡ ቢሆኑም በመንፈሳቸው ከጌታችን ኢየሱስ ክስቶስ ጋር ሙሉ ውህደት ሊኖራቸው እንደሚችል በማስገንዘብ፣ ስለዚህ ማኅበረ ክርስትያን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅያውነት ማረጋገጫ በመሆኑ ከማኅበረ ክርስያን ጋር ውህደት መፍጠር ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት ማጽናት ማለት ነው። ስለዚህ ሥጋሁ ወደሙ በመቀበል የሚፈጠረው ተጨባጩን ውህደት በመንፈስ መኖር የሚቻል መሆኑ እንደገለጡ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ ካብራሩ በኃላ በእምነት ዘንድ ያለው ሕይወትና በማኅበረ ክርስትያን ዘንድ ያለው ሕይወት የሚገልጥ ነው። በሌላው አገላለጥ ማኅበረ ክርስትያን የተረጋጋና ቀጣይ የፍቅር መስካሪያን ሆነው መገኘት እንደሚጠበቅባቸውና፣ ምሥጢረ ተክሊል የተረጋጋና ቀጣይ ፍቅር የሚኖርበት ትዳር መግለጫ መሆኑ ለማስገንዘብ ብሎም ለቤተ ክርስትያን አቢይ ጸጋ መሆኑ ለማስረዳትኑ የተጠቀሙበት ጥልቅ መፍነሳዊና ቲይሎጊያዊ ሓሳብ ነው በማለት ያቀረቡት ርእሰ ዓንቀጽ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.