2012-06-11 14:52:41

ሕይወትንና ቤተሰብን መከላከል


የቅደስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ እ.ኤ.አ. ግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. በፖላንድ ሎድዝ ከተማ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በአገሪቱ የፈጸሙት የመጀምሪያ ሐዋርያዊ ዑደት 25ኛው ዝከረ ዓመት ምክንያት እሁድ የላቲን ሥርዓት በምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ተከብሮ የዋለው ዓቢይ “Corpus Domini- ቅዱስ ሥጋሁ ወክቡረ ደሙ” በዓል ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት RealAudioMP3 ስብከት፣ ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊን በማስታወስ በሳቸው አማላጅነት፣ ክርስትያኖች ሕይወትና ቤተሰብ ዓቢይ የኅብረተሰብ ሃብት መሆኑ ተገንዝበው የላቀው እሴቶት እንዲከላከሉ በማሳሰብ፣ ክልላዊ ቤተ ክርስያን ተብሎ የሚገለጠው ቤተሰብ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ምልክት ነው። እያንዳንዱ ቤተሰብ ቤተ ክርስትያን ነው። እንዲህ በመሆኑም ሕይወትና ቤተሰብ መከበር፣ መከላከል በተለይ ደግሞ መፈቀር ይገባዋል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢሳበላ ፒሮ ገለጡ።
ቤተ ሰብ፣ እምነትና ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር የሚነቃቃበት የሚጠነክርበት ባህርያዊ ሥፍራ ነው። የአዲሱ ትውልድ ዕለታዊ ኑሮና ሂደትም ጭምር መልካም ፍሬ የሚያስገኝ እንዲሆን በቤተሰብና በትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች መካከል ትብብር ወሳኝ ነው ካሉ በኋላ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ቅድስት ቤተ ክርስትያን የምታከብረው “Corpus Domini- ቅዱስ ሥጋሁ ወክቡረ ደሙ” በመጥቀስ ቅዱስ ቁርባን ክርስቶስ ገዛ እራሱን የሰጠበት ጸጋ ነው፣ በቅዱስ ቁርባን ፊት ግድ የሌላቸው ሆኖን መኖር አንችልም፣ በየዕለቱ በመሥዋዕተ ቅዳሴ ሊጡርጊያ ሱታፌ ያለው ውበት በእኛ ዘንድ እምነት ተስፋና ፍቅር የሚያነቃቃ ነው። በተለይ ደግሞ በሰዎች ሕይወት የክርስቶስ መጋረድ በስፋት በሚታይበት በአሁኑ ወቅት እምነት የሚያነቃቃ መሆኑ እንዳብራሩ የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አክለውም፣ ቤተሰብ ለመከላከል ያለው አስፈላጊነት ሴቶችን ሕጻናትን ወጣቶችን አዛውንቶችም መከላከል የሚል ጭምር መሆኑ ብፁዕነታቸው በሎድዝ የባህልና የሥነ ጥናት ሊቃውንት ጋር ተገናኝተው ባሰሙት ንግግር እንዳሰመሩበት ገልጠዋል።
በዚሁ ከባህልና ከሥነ ጥናት አካላት ጋር በመገናኘት የሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማው ታሪክና ትምህርት ላይ በማተኮር ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሕይወት ባህል መምህርና በቃልና በሕይወት መስካሪ መሆናቸው ላይ ያነጣጠረ ንግግር በማሰማት፣ ሕይወት በየትም ደረጃና ሁኔታም ይገኝ መከላከሉ ሥነ ምግባራዊ ባህል አድማስ መሠረት ያለው ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ገልጠው፣ በአሁኑ ወቅት ለእግዚአብሔር እምቢ ብሎ ጀርባ መስጠት የሚነቃቃው በዓለማችን የሚሰበከው የሞት ባህል የኅሊና ሕንጸት አማካኝነት በመቃወም፣ በዚሁ ዘርፍና የሰላም ባህል ግንባታ በተመለከተም የመገናኛ ብዙኃን ሊሰጡት የሚገባቸው አስተዋጽዖ አስፈላጊነቱን ገልጠው፣ ይኽንን ዓላማ እንዲያነቃቁ ምሁራንና መላውን ኅብረተሰብ ስለ ጉዳዩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መሁሉም መስክ ጥረት መደረግ አለበት ካሉ በኋላ ሕይወት ጸጋ በመሆኑም ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት መከበር አለበት እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.