2012-06-08 14:58:57

የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ለአንድነት ያቀናው የጋራው ውይይትና መደጋገፍ


ከትላትና በስትያ በሮማ ከተማ በቄጵሮስ መንግሥትና በካቶሊክ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር መካከል ለአንድነት ባቀናው በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን በሚደረገው RealAudioMP3 የጋራው ውይይት በመደጋገፍና ሰላም ለማረጋገጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚከናወኑት ጥረቶች የጋራ ትብብር በሚል ስምምነት ላይ መፈራረማቸው ሲገለጥ፣ የስምምነቱን ሰነድ ቄጵሮስን ወክለው የፈረሙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤራቶ ኮዛኩ ማራኩሊስና የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ሊቀ መንበር ማርኮ ኢምፓሊያዞ መሆናቸው የተካሄደው ግኑኝነት የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ዳቪደ ማጆረ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
በተካሄደው የስምምነት ሰነድ መፈራረም መርሃ ግብር ፍጻሜ የቅዱስ ኢጂዲዮ ማኅበር ሊቀ መንበር ኢምፓሊያዞ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ እዳመለከቱት፣ የተደረሰው ስምምነት በቅድሚያ በሪፓብሊካዊት ቄጵሮስና በቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር መካከል በአሲዚ ለሰላም አልሞ በየዓመቱ በሚካሄደው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖት የጋራ ግኑኝነትና መንፈሳዊ መርሃ ግብር መሠረት ይኽ መርሃ ግብር ለማረጋገጥና በየዓመቱ ለማዘጋጀት በሚደረገው ጥረት ለመተባበርና የአሲዚ መንፈስ ተከትሎ እ.ኤ.አ. መስከረም ወር 2008 ዓ.ም. በኒኮሲያ የተካሄደው በጋራ በሰጡት አስተዋጽዖ ላይ የጸና ያረጋገጡት ጥልቅ ወዳጅነት የሚገልጥ ነው።
ቄጵሮስ፣ የደሴት መከፋፈል የሚታይባት ቢሆንም፣ በሜዲትራኒያን ክልል አቢይ ሚና ያላት አገር ነች። ከዚህ አኳያ በመነሳትም በሰላም ጉዳይ እንዲሁም በሜዲትራኒያን ክልል ኅብረት በተመለከቱት እቅዶች አቅምና ብቃትን ካለ መቆጠብ በጋራ አስተዋጽዖ መስጠት አስፈላጊ ነው ካሉ በኋላ አብሮ መኖር አብቆትለት የተደረሰ ግብ ሆኖ የሚኖር ሳይሆን አብሮ መኖርን ዕለት በዕለት መማር ያስፈልጋል ብለዋል።
ቀጥለውም የቄጵሮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ካዛኩ ማራኩሊስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የቅዱስ ኢጂዲዮ ማኅበር በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ አገሮች ወደር የማይገኝለት የገላጋይነት ሚና የተጫወተና በዚሁ መስክ አቢይ አስተዋጽዖ ከመስጠት ያልተቆጠበ ለሰላም መረጋገጥ አቢይ ጥረት የሚያደርግ የካቶሊክ ማኅበር ነው። ስለዚህ እንዲህ ካለው ማኅበር ጋር የጋራ ስምምነት መፈራረም ለረፓብሊክ ቄጵሮስ ክብር ነው።
አንዱ የረፓብሊዊት ቄጵሮስ በተረኛ የኤውሮጳ ኅብረት ሊቀ መንበርነት ተልእኮ የምታስቀድመው መርሃ ግብር እርሱም ከወዲሁ በኤውሮጳ ኅብረትና በአረብ አገሮች ማኅበር ዘንድ የጋራ ትብብር ለማጎልበት መሆኑ ጠቅሰው፣ ቄጵሮስ ይኽንን ሚና ለመጫወት ያላት መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ያደላት የተልእኮ ኃላፊነት ነው። የኤውሮጳና የመካከለኛው ምስራቅ ክልል አገናኝ ድልድይ አገር ነች በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.