2012-06-08 15:00:46

የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ባህርይ ወደ ዳር አልቦነት-ነገር (ወሰን አልባ) ያቀና ነው


እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 19 እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. የሚካሄደው የዘንድሮው 33ኛው “Comunione e Liberazione-ሱታፌና አርነት” የተሰየመው በሥመ ጥር RealAudioMP3 አባ ጁሳኒ የተቋቋመው ማኅበር በኢጣሊያ ሪሚኒ ከተማ የሚዘጋጀው ዓለም አቀፍ ጉባኤ፣ ከእኚህ ሥመ ጥር የቤተ ክርስትያን ልጅ “Il senso religioso- የሃይማኖት ትርጉም“ በሚል ርእስ ሥር ከደረሱት መጽሐፍ የተወሰደ፣ የሰው ልጅ ተፈጥሪአዊ ባህርይ(በኑባሬ) ወደ ዳር አልቦነት ነገር ያቀና ነው በሚል ዋና ርእስ የሚመራ ሲሆን። ፍጥረት (ሰው) አለ ፈጣሪ የተገኘ እንዳልሆነና፣ ደረት አልቦ እንዳለ ልብ የማለቱ ዝንባሌ በኑባሬ ያለው ባህርይ ሲሆን፣ የታደለው ባህርይ ነው። ስለዚህ በዚህ ጥልቅ ቲዮሎጊያዊና ፍልስፍናዊ ሃሳብ ላይ በማተኮር በጠቅላላ አንድ መቶ እውደ ጥናቶች 10 በጉባኤው ርእሰ ጉዳይ ላይ ያነጣጠሩ ትርኢቶች 26 ትእይቶች 10 የስፖርት መግለጫዎች ያጠቃለለ መሆኑ ስለ ጉባኤ በማስመልከት የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
በሰውና በዳር አልቦነት ፍጹም ነገር መካከል ያለው ግኑኝነት ላይ ያተኮረ የዘንድሮው የሪሚኒ ጉባኤ ሰው ወደ ፍጹምና ወደ ዳር አልቦነት ነገር በባህርዩ ያቀና ነው። ይኸ የሰው ልጅ ቅርብ የህልውና ተመክሮ፣ ሰው ከዚህ ዳር አልቦነት ጋር ለመገናኘት ያለው ጥልቅ ፍላጎት ጭምር የሚዳስስ ነው። ወደ ዳር አልቦነት ማቅናት ባህርይ ዳር አልቦነትን መሻትንም ጭምር ያሰማል፣ ይኽ አቢይ ከነገር ባሻገር ላይ የሚያተኩረው ጉባኤ ከተጨባጩ ዓለም ጋር በማጣመር በዚሁ ባህርይ ሥር ኅላዌና ወቅታዊው ዓለም በመዳሰስም ወጣት ትውልድ ለእድገት በሚል ርእስ ሥር የኢጣሊያው መራሔ መንግሥት ማሪዮ ሞንቲ በሚያሰሙት ንግግር እንደሚጀመር ዶኒኒ ካጠናቀሩት ዘገባ ለማወቅ ሲቻል፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጠቅላይ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ናሲር አብዱላአዚዝ አል-ናሲር፣ ጳጳሳዊ የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ግኑኝነት ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ቱራን፣ ጳጳሳዊ የኅብረተሰብ ሥነ እውቀት ተቋም ሊቀ መንበር መርይ ኤን ግለንዶን፣ የግብጽ የሕገ መንግሥት አስከባሪው የበላይ ፍርድ ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ጣሃኒ አል ገባሊ ንግግር እንደሚያሰሙም ሲገለጥ፣ ካለ መኖር የሚፈጥረ በገዛ እራሱ የጸናው እግዚአብሄር ኅላዌ የሰው ልጅ በተፍጥሮአዊ ባህርዩ የሚያስተውለው እውነት ነው። ስለዚህ ከዚህ በመንደርደር ሰው “Homo religiosus- ሃይማኖተኛ ሰው” በሚል ርእስ ሥር የሥነ ሃይማኖት ሊቅ የሃይማኖት ሥነ ታሪክ ተመራማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዚሁ ዘርፍ የላቁ ምሁር ተብሎ የሚነገርላቸው የቤልጂም ተወላጅ ብፁዕ ካርዲናል ኹሊየን ራይስና የቡድሃ ሃይማኖት ተከታይ ገዳማዊ ሾዶ ሃቡካዋ ጥልቅ አስተምህሮ እንደሚያቀርቡ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ ያስተላለፉት ዘገባ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.