2012-06-06 14:38:45

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ፦ “ቅዱስ አባታችን በሚደርሰው ጥቃት የሚደናገጡ አይደሉም፣ በእምነት የጸኑ እምነትን የሚያጸኑ”


እ.ኤ.አ. ከግንቦት 30 ቀን እስከ ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በተካሄደው ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ቅዱስ አባታችንን በመሸኘት የተሳተፉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ የተካሄደው ዓቢይ ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ጠቅላይ ሂደቱ ምን እንደሚመስል ግምገማ RealAudioMP3 እንዲሰጡበትና በተለይ ደግሞ አንዳንድ የታቀቡ የግል የቅድስት መንበር የውስጥ ግኑኝነት ጉዳይ ሰነዶች (የመልስ ልውውጥ ደብዳቤዎች) በሥውር ቅጆችን በማስወጣት በተለያዩ የኢጣሊያና የወጭ አገር የመገናኛ ብዙኃን በቤተ ክርስትያን ውስጥ መከፋፈልና ሽኩቻ እንዳለ በመጥቀስ እያቀረቡት ስላለው ሓተታ በተመለከተ ለጠየቃቸው ለኢጣሊያ ራይ ኡኑ በመባል ለሚጠራው የቴሌቪዥንና የራዲዮ ጣቢያ ክፍል ለሆነው የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲመልሱ፣ በርግጥ አንዳንድ ሰነዶች እውነትን ለማሳወቅም እንደማያስችሉ ነው ካሉ በኋላ፣ እውነት ለማሳወቅ በቂ ማስረጃ ሊሆን አይችልም ብለዋል።
በቅድስት መንበር በውስጥ ሥራ በተለያዩ የውስጥ የሥራ ቅርንጫፎች በኩል የሓሳብ የአስተያየት ልውውጥ ውይይት በቃልም ሆነ በደብዳቤ መልክ በግልም በይፋም ይከናወናል፣ ይኽ ደግም የተለመደ የሥራ የግኑንኘት ጉዳይ ተግባር ነው። በሰዎች መካከል እንደሚፈጸመውም የግል የልበ ምሥጢር ግኑኝነትም በቃልና በጽሑፍ ይከናወናል፣ የቢሮክራሲ ግንኙነት የሚመለከት ብቻ ሳይሆን የሰብአዊ ግኑኝነት ጭምር የሚመለከት ነው። ሆኖም ግን እነዚህ የውስጥ በደብዳቤ በኩል የተከናወኑት ግኑኝነቶች የሚገልጡ መልእክት የሰፈሩባቸው ደብዳቤዎችን በሥውር የስዕል ቅጅ በኩል በማስወጣት ልዩ የግል መብት በመጣስ የተፈጸመው ወንጀል በርግጥ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን በሕግ ጭምር የሚያስጠይቅ ነው። ስለዚህ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.ና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የግል መብት እንዲህ ባለ መልኩ ሲጣስ ታይተዋል። እነዚህ ሰነዶች በማሸሎክ የተፈጸመው የግል መብት ጥሰት፣ የቤተ ክርስትያን አንድነትን የሚያጠነክር እንጂ ለመከፋፈል ምክንያት ይሆናል ብሎ መጠበቅም ሆነ ማመን የዋህነት ነው። በሚሰጡትና በተሰጡት ውሳኔዎች አማካኝነት የእምነት ኃይል ያየለበት፣ ጽኑ መረጋጋት የተመሰከረበት ወቅት ነው። ቤተ ክርስትያን በእውነት ለማገልገል ለሚሹት ሁሉ የጥልቅ ውህደት ወቅት ነው ብለዋል።
የኵላዊት ቤተ ክርስትያን መሪ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሚቃወምና የሚጻረር ተግባር ሲፈጸም ማየቱ አያስገርምም ምክንያቱም የቤተ ክርስትያን ታሪክ ገጠመኝ ይመሰክረዋል። በማለት የር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ወቅት የነበረው ሁኔታ እንደ አብነት ጠቅሰው፣ በአሁኑ ወቅት የተፈጸመ ጸረ ቤተ ክርስትያን ተግባር ግን ሆን ተብሎ የገዛ እራሱ ድብቅ ዓላማ ያለው የተደራጀ አሳፋሪና አደገኛ ተግባር ነው። ሁሉም እንደሚያውቀውም ቅዱስ አባታችን ልባም አስተዋይ አቢይ የእምነት ጸጋ የታደሉ ጸላይ ናቸው። ስለዚህ በተከሰተው ጥቃት ይሰጥ በነበረውና ባለው በነበረው ጅምላዊ ቅድመ ፍርዶች ይደናገጣሉ ማለት ዘበት ነው። ከጎናቸው ሆኖ የሚያገለግልና ቅርብ የሆኑት ተባባሪዎቻቸው ጠንቅቀው የሚያውቁት የቅዱስ አባታችን መለያም ነው።
ቅዱስነታቸው በሚላኖ በተካሄደው ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ተሳትፈው ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው ለመመለስ ከሚላኖ ሊቀ ጳጳሳት ሲሰናበቱም ሆነ በጉባኤው ለወጣቶች ለባለ ትዳሮች ለካህናት ለቤተሰቦች ባሰሙት መልእክት በርቱ የሚል ቃል ሲጠቀሙ ታይተዋል፣ በጠቅላላም ለኵላዊት ቤተ ክርስትያን ያሉት ቃል ነው። በርቱ የሚሉትም እሳቸው ስለ በረቱ ነው። ካላቸው የእምነት ጽናት የመነጨ ቃልም ነው። በርቱ የሚለው ቃል በጥልቀት በማስተንተን በማጣጣም በቅዱስ አባታችን መሪነት ሥር ከጎናቸው እንሁን በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.