2012-06-06 14:40:02

ብፁዕ አቡነ ክይሪሎስ ዊሊያም፦ ቤተሰብና የአረብ አገሮች ጸደይ


በሚላኖ ከተማ እ.ኤ.አ. ከግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በተካሄደው ሰባተኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከመላ ዓለም የተወጣጡ ልኡካንና ቤተሰቦች መሳተፋቸው ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ በዚሁ ጉባኤ ከተሳተፉት ከዓረብ አገሮች ከተወጣጡት ውስጥ ከግብጽ የተወጣጡት ቤተሰቦች RealAudioMP3 የሚገኙበትም ሲሆን፣ አንዚህን ግብጻውያን ተሳታፊዎችን የመሩት የሲዩት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ክይሪሎስ ዊሊያም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የአረብ አገሮች ክርስትያን ቤተሰቦች በተለያዩ ሃይምኖቶች መካከል ለሚካሄደው የጋራው ውይይት አቢይ አስተዋጽዖ እንዳላቸው በማስታወስ፣ ከአረብ አገሮች የተወጣጡት የጉባኤው ተሳታፍያን ቤተሰቦች በእውነቱ የቤተ ክርስትያንነት መንፈስ ያረጋገጡበትና የቤተ ክርስትያ ኩላዊነት ገጠመኝ ያካበቱበት ወቅት ነበር ካሉ በኋላ፣ በግብጽ የካቶሊክ ማኅበረሰብ ውሁዳን በአገሪቱ ካሉት የተለያዩ የማህበረ ክርስትያን ክፍል ውስጥ ውሁዳን ናቸው፣ ስለዚህ የውሁዳን ውሁዳን መሆናቸው ገልጠው፣ እዚህ በሚላኖ ከተለያዩ አገሮች ከተወጣጡት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመናን ቤተሰቦች ጋር በመገናኘት የኩላዊነት ገጠመኝ በማካበት የማበረታቻ የአቢይነትና የብርታት መንፈስ ለማጣጣም ችለዋል። በአሁኑ ወቅት ሁሉም የግብጽ ዜጎች የግብጽ መጻኢ ጉዳይ ምን ይሆን በሚል ሓሳብ ተወጠው ይገኛሉ፣ ግብጽ ብዙዎች ምናልባት አክራርያን ሙስሊሞች ለብዙ ሙስሊሞችና ለሌሎች ሃይማኖት ምእመናን ጭምር ዓቢይ ሥጋት ተብሎ ወደ ሚነገርለት እስላማዊ አገረ ግዛት ይለውጡዋት ይሆን ወይ የሚል ሥጋት አለባቸው፣ እንዲህ እንዳይሆን ደግሞም ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በግብጽ ኤኮኖሚያ ችግር አለ የሥራ አጡ ብዛት የኑሮ ውድነት ከቀን ወደ ቀን ከፍ እያለም ነው። ሆኖም በጌታ ላይ ያለው ተስፋችን ሳናጨልም በእርጋታ በመኖር ስድስት ቀን ተሰርቶ ሰባተኛው ቀን ጌታን በማክበር በእርሱ በመታመን እየተኖረ ነው። እዚህ በሚላኖ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ በመሳተፍ ከቀረቡት አስተምህሮዎች በተለያዩ የክብ ጠረጴዛ የሥራ ጉባኤዎች በመሳተፍ በተለይ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከሰጡት ምዕዳንና ካሰሙት ስብከት ያካበትነው ልምድ ለእያንዳንዳችን ተሳታፊዎችና ተሳታፊው ለተወጣጣበት አገር ጭምር አቢይ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው አልጠራጠርም፣ በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ ለሚደረጉት ተመሳሳይ ጉባኤዎች አቢይ ድጋፍ ነው።
የግብጽ ሕዝብ በተለይ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ አዲሲቷ ግብጽ ነጻ ዴሞክራሲያዊት ኅብረ ብሔር ኅብረ ሃይማኖትና ኅብረ ባህል ተከባብሮ መኖር ተረጋግጦባት ለማየት አቢይ ጉጉት አለው። ለዚህ ዓላማም ካለ መታከት ዕለት በዕለት እየታገለ ነው ካሉ በኋላ የግብጽ ክርስትያኖች ሊደጋገፉና ሊተባበሩ ይገባቸዋል፣ በተለይ ደግሞ በዚህ ግብጽ ለዘርፈ ብዙ ችግር ተጋልጣ በምትገኝበት በአሁኑ ወቅት በበለጠ ትብብሩንና መደጋገፉን ማሳየል ይኖርባቸዋል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.