2012-06-04 13:37:01

“ቤተ ሰብ ዓለምን መለወጥ አለበት”


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት በሚላኖ ሃገረ ስብከት ተገኝተው ሶሙንን ሲካሄድ የሰነበተውን የቤተ ሰብ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ሲደመድሙ “ቤተ ሰብ ዓለምን መለወጥ አለበት” ሲሉ በወንጌል የሚያምን ቤተ ሰብ ፍቅር ለቤተሰቡ እና ለሚኖሩበት ለመላው ዓለም የኃይል ምንጭ መሆኑን በስብከታቸው አሳስበዋል፣ ቅዱስነታቸው በዚሁ ትናንትና ባሳረጉት የቤተ ሰብ ጉባኤ መዝጊያ ቅዳሴ በብረሶ መናፈሻ ሜዳ ከአንድ ሚልዮን በላይ እንደተሳተፉ ከቦታው የደረሰን ዜና ዘግበዋል፣ ደጋግመን በዜና ዘገባዎቻችን እንዳመለከትነው ይህ ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ በየሶስት ዓመት የሚደረግ ሆኖ ዘንድሮ በሚላኖ ለሰባተኛ ጊዜ ነው የተካሄደው፣ ቅዱስነታቸው የመልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ባደረጉት ጉባኤ አስተምህሮ ተከታዩ ስምንተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ከሶስት ዓመታት በኋላ እ.አ.አ. ብ2015 ዓም በተባበሩት አመሪካ በፊላደልፍያ ከተማ እንደሚካሄድ ገለጠዋል፣
ባለንበት ዘመን ቤተሰብ መምራት ከባድ መሆኑ ሲገልጡ “ውድ ሙሽራዎች ዛሬ ቤተ ሰብ መሆን ቀላል አይደለም ሆኖም ግን ዛሬ ዓለማችን እንዲሻሻል ተስፋ ያለ እንደሆነ እናንተን የመሰሉ ሰዎች የሚጠምር ፍቅር ብቻ ነው፣” ብለው እፊታቸው በነበሩ በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ የቤተሰብ ጥምዶች እየተመለከቱና እያመለከቱ “ይህ የሕያው ቤተ ክርስትያን ምሳሌ ነው፣ ምንም እንኳ በባልና ሚስት እንዲሁም በወላጆችና ልጆች መካከል ያለውን ግኑኘት እንደሚወድም የሚነበዩ ጎጂ በሆኑ ኅብረተስብአዊ አስተሳሰቦችና በመገናኛ ብዙኃን ፍርድ ቤቶች መጻረር ቢገጥመው የእነኚህ አውታሮች አስተሳሰብ ቤተሰባዊ ቤተክርስትያን ምን መሆንዋ ሊረዱ አይችሉምና፣” ሲሉ ቤተ ሰብ ትንሽዋ ቍምስና ወይም የቤት ቤተ ክርስትያን በመሆን የቤተ ክርስትያንና የማኅበረሰብ መሠረት መሆንዋን አብራርተዋል፣
ባለንበት ዘመን አስተሳሰብና ተስፋ መቍረጥ አንጻር ግን ከ150 አገሮች በላይ የመጡ ቤተሰቦች በዚሁ ጉባኤ ተገኝተዋል፣ ይህ ቍጥር በቀጥታ በመገናኛ ብዙኃን ሁኔታውን ከተከታተሉት ስፍር ቍጥር የሌላቸው ቤተ ሰቦች ሲነጻጸር እጅግ ትንሽ ነው፣ ቅዱስነታቸው ግን ለሁሉም እንደሚናገሩ በመረዳት “ፍቅራችሁ አንዱ ለሌላው ለመርዳት ስለምትታገሉ ፍርያም ነው፣ ለመጀመርያ የዚህ ፍቅር ፍሬ ተጠቃሚዎች ልጆቻችሁ ናቸው ምክንያቱም በልግስናና በኃላፊነት ስለምትቀበልዋቸው፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከእናንተ ነጻ የሆነ መከባበር የሞላበት እና በመተባበር የሚታወቅ ኅብረተሰብአዊ ኃይል ስለሚያገኝ ማኅበረሰቡ ነው፣
ውድ ሙሽሮች ልጆቻችሁን ተንከባከቡ፤ በዚሁ ዘመናዊ ተክኖሎጂ የተቆጣጠረው ዓለም ለልጆቻችሁ ከፍተኛ የሕይወት ዓላማዎች እያመለከታችሁ በድካማቸው እየረዳችሁዋቸው በጸጥታና በመተማመን የመኖር ትርጉም እና የሃይማኖት ኃይልን አስተላልፉላቸው፣ ሆኖም ግን እናንተም ልጆች ከወላጆቻችሁ ጋር ጠለቅ ያለ ፍቅር ያለበት ግኑኝነት እንዲኖራችሁና ርኅራኄ የሞላበት እንክብካቤ እንድታደርጉላችሁ ይሁን፣ ከወንድሞቻችሁና ከእኅቶቻችሁ ያላችሁ ግኑኝነትም በፍቅር የማደግ ዕድል ይሁንላችሁ፣ የእናንተው ጥሪ በተለይ ባለንበት ዘመን ልትኖረው ቀላል አይደለም፤ ሆኖም ግን ያ አስደናቂ የሆነው የፍቅር ኑሮ ዓለምን ሊለውጥ የሚችለው ብቸኛ ኃይል ነው፣ በዚሁ ዘመን ይህንን ከባድ ሕይወት በሙሉ ፍቅር ለመኖር ለሚጥር ሁሉ በየዕለቱ ልብንና ነፍስን የሚያቆስል ቅንዋት ነው፣ ቤተ ክርስትያን ስለቤተ ሰብ የምታስተምረውን እየተቀበሉ ኑሮ አስገድⶌአቸው ቃል ኪዳን በማፍረስ ወይንም ተለያይተው በሥቃይ ለሚኖሩ ም እመናን አንድ ቃል ለመናገር እወዳለሁ፣ ር.ሊ.ጳጳሳትና ቤተ ክርስትያን በምታደርጉት ትግል ይደግፍዋችኋል፣ ሃገረ ስብከቶቹ እናንተን የሚቀበሉበትና የሚቀርቡበት እርምጃዎች እንዲወስዱ መልካም ምኞቴን እየገለጥሁ በማኅበረሰቦቻችሁ ተዋህዳችሁ እንድትኖሩ አበረታታችኋለሁ፣” ሲሉ ለጠቅላላው የቤተ ክርስትያን አባል የሚሆን ስብከት አቅርበዋል፣
ቅዱስነታቸው ሚላኖ ከመምጣታቸው በፊት ጉባኤው ሲካሄድ ስለቤተሰብ ግብረተልእኮ በተደረገው ውይይት ቤተ ሰብ የሥራና የበዓላት ግዝያት ማመዛን እንዲችሉ እንዴት እንርዳቸው የሚል አር እስት ተነሥቶ ነበር፣ ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ይህንንም አወሱት፣ “የእግዚአብሔር ዓላማና የሕይወት ተመኵሮ የቤተ ሰብ የተዋሃሃደ እድገት የቤተሰብ በጎ ነገር እንዲሁም ፍትሓዊ ማኅበረሰብ የማነጽ እንዲያገጣጥም ነው፣ ሆኖም ግን ይህ ባንድ ጎን ብቻ የሚመለከት አይደለም፣ ምክንያቱም ለዚህ መልካም ነገር እየታገሉ ቅጥ ያጣ ውድድር አለእኩልነት የአከባቢ መውደም ጥቅም ብቻ የመፈለግ መንፈስ የቤተሰብ አለመጣጣም ሊያስከትል ስለሚችል ነው፣ በዚሁ አንጻር ሌላን የመርዳት መንፈስና አስተሳሰብ ያለን እንደሆነ ግን በግል እና በቤተሰብ ደረጃ በሚደረግ ግኑኝነት ሊከሰቱ የሚችሉት ከግል ጥቅም የሚነሱ አለመረዳዳቶችን በመቀነስና የማኅበረሰቡ ግኑኝነትን በማደላደል ሊረዳ ይችላል፣ ስለዚህ ዕለተ ሰንበት የቤተ ሰብ ቀን መሆኑን በመረዳት ሁላቸው በመሥዋዕተ ቅዳሴ በመሳተፍ ሁሉንም በመከፋፈል አብረው በመገኘትና በመደሰት የበዓል መንፈስ ያልብሱት፣ ውድ ቤተ ሰቦች በሁሉ ተጣብቦ በሚገኘው ዘመናችን የጌታ ዕለት መንፈስ ትርጉምን አትርሱ፣ የጌታ ዕለት እንደ በምድረበዳ የሚገኝ ለም ቦታ ነው፣ እዛ ላይ ላንዴ አረፍ በማለት እግዚአብሔር የማግኘት ደስታ የምናጣጥምበትና ያለንን የእርሱ ጥም የምናረካበት ቦታ ነው፣” ሲሉ ዕለተ ሰንበትን ማክበር በነፍስና በሥጋ ቤተ ሰብን እንደሚረዳና እንደሚያስተባብር ገልጠዋል፤
እኩለ ቀን ላይ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከም እመናኑ ጋር ለመጸለይ በተገኙበት ግዜም ለሚቀጥለው የቤተሰብ ጉባኤ የተመረጠ ቦታን በይፋ አውጀዋል፣ “የሚቀጥለው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ እ.አ.አ. 2015 በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በፊላደልፍያ ከተማ ይካሄዳል” ብለዋል፣
ቅዱስነታቸው የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ካሳረጉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬ ከመቸራቸው በፊት የጳጳሳዊ የቤተሰብ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኤንዮ አንቶነሊ ር.ሊ.ጳጳሳትን አመስገነውል፣ እዛ ለተገኙት ሁሉ ደግሞ የቤተሰብ ጉባኤ የተካሄደላቸው ቀኖች የማይረሱ ዕለታት መሆናቸውን ገልጠልዋል፣ እንዲሁም የሚላኖ ሃገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚኖ ደ እስካልሲ በጉባኤው ጊዜ የተሰበሰበ 500 ሺ ኤውሮ በር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በጎ ፈቃድ በኤሚልያ ሮማኛ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ለተጐዱ ወገኖች እርዳታ እንዲሆን መወሰኑን ገልጠዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.