2012-06-04 15:00:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ወደ ላቀው ፍጹም ዓላማ አቅኑ፣ ቅዱሳንም ሁኑ”


እ.ኤ.አ. ቅዳሜ ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ሚሥጢረ ሜሮን የተቀበሉት 80 ሺሕ የሚላኖ ሰበስካ ወጣቶችን በከተማይቱ በሚገኘው የሜአዛ አቢይ የእግር ኳስ ሜዳ ተቀብለው ወደ ላቀው ፍጹም ዓላማ ሁሉም ወጣት እንዲያዘነብል፣ ቅዱሳን ሁኑ በተሰኘው ዋነኛ ሓሳብ ላይ ያተኮረ ሥልጣናዊ ምዕዳን RealAudioMP3 አቅርበዋል።
ቅዱስነታቸው እዛው በእግር ኳስ ሜዳ ተገኝተው ከወጣቶቹና ከሚላኖ ሰበካ ህዝብ በሞቀ ልባዊ በጨብጨና በሆህታ አቀባበል ተደርጎላቸው ስለ ክብራቸው የቀረበው በባህር ዳርጃ ከጴጥሮስ ጋር የተሰየመው መንፈሳዊ በሙዚቃ የተሸኘ የሚያስደንቅ የትያትር ትርኢት ተከታትለው እንዳበቁ ባሰሙት ሥልጣናዊ ምእዳን፣ ምሥጢረ መሮን የተቀበሉት ወጣቶች ለእግዚአብሔር የተስተዋለና ነጻ እነሆኝ እንዳሉ ገልጠው ደስ ይበላችሁ፣ ውዶቼ የመላው ክርስትያናዊ ሕይወት ጉዞ ቁልቁለት ሳይሆን አቀበት የበዛበት ከባድ ቢሆንም በተቀበላችሁት ቅዱስ ምሥጢር አማካኝነት ከእርሱ (ከጌታ) ጋር በምታጸኑት ወዳጅነትና ጓደኝነት ጉዞውና መንገዱ እነተኛና ጠባብም ልብን በኃሴት የሚሞላ ይሆናል። ከእርሱ ጋር ሁሉም ይቻላል ብለዋል።
በመቀጠልም ቅዱስነታቸው የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ችላ ሳይሉ በመንፈሳዊው ሂደት በርትተው በጥልቅ ጥናት መሠረትም እንዲያድጉ አሳስበው፣ ለመጪው ሕይወት አቢይ እድል በከፍተኛ የትምርህት ጥናት የሚፈጸም ጉዞ የዕለታዊ ሕይወት ኃላፊነት ነውና’ ካለ መሰልቸት በትጋት እንዲኖሩት አደራ ብለዋል።
ወጣቶች እኔነትን ማእክል ከሚያደርግ የእውነተኛው ደስታ ጠላት ከሆነው ከራስ ወዳድነት ተቆጥባችሁ ደጎች ሌላውን ለመደገፍ ዝግቹዎች ሆናችሁ፣ ለላቀው መልካምና ፍጹም አላማ በማተኮር ለቅድስና ይተጉ ዘንድ በኃይለ ቃል አባታዊ ምዕዳኔን አቀርብላችኋለሁ ካሉ በኋላ፣ የሚላኖ ክተማ ጠባቂ ቅዱስ አምብሮዚዮስ እንደሚለውም “ማንኛውም ዕድሜ ለክርስቶስ የበሰለ ነው” ካሉ በኋላ ወጣቶችም ብትሆኑም ቅድስና ዕድሜ የሚከልለው አይደለም ብለዋል።
የክርስቶስ ፍቅር ለሁሉም ክርስትያን የሚመለከት ነው። ሆኖም ግን በክህነት ጥሪ እርሱን የሚከተሉ ለመናኝ ሕይወት፣ (ንጽሕናና ድኽነት ተአዝዞ) የተጠሩ፣ ሁሌ ክርስቶስን ለመከተል ብቻ የሚኖረው ሕይወት ምንጭ ክርስቶስ ለአባቱ ፈቃድ እሺ በማለት የኖረው ሕይወት መሆኑ እንዲገነዙ አደራ በማለት፣ የዚህ ሕይወት አብነትና በዕለታዊ ሕይወት መኖር ያለበት ሌላዊ ሕይወተ ክርስቶስ ነው ብለዋል።
የጸጋ ሁሉ ምንጭ የሆነውን ጌታ በታማኝነት የካህናት አገልግሎት ዘወትር ፍርያማ እንዲሆን የሚኖሩት የክህነት ሕይወት ለክርስቶስና ለቤተ ክርስትያን መሰጠት ያለውን ጥልቅ ውበት የሚገልጽ እንዲሆንና፣ ክርስትያን ቤተሰቦችን የጸጋና የቅድስና እንዲሁም ለጥሪ ‘ለክህነትና ለመናንያን ሕይውት ጥሪ’ ለም መሬት ሆነው እንዲገኙ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መታደስን ይኖርባቸዋል ስለዚህም ለዚህ ዓይነቱ የተቀደሰው ሕይወት በቃልና በሕይወት ምስክርነት የተካኑ ሆነው እንዲገኙ አደራ ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.