2012-05-31 10:07:25

የግልጸት ተአምራቶች እውነተኛነታቸውን የሚለይ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን መመዘኛዎች


ሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ግልጸት በተመለከተ እርሱም መለኮታዊ ግልጸት ተብለው በተለያየ ወቅት የሚነገሩት ተአምሮች ቤተ ክርስትያን ትክክለኛነቱን መለኮታዊነት አናሥር ያለው መሆኑ ለመመርመርና ለመለየት የተገባት ኃላፊነት መሆኑ ላይ በማነጣጠር እ.ኤ.አ. በ 1978 ዓ.ም. በዚሁ ቅዱስ ማኅበር ሥር በር.ሊ.ጳ. ፈቃድ መሠረት የተወሰነው ደንብ ታትሞ በቫቲካን ረዲዮ ይፋዊ ድረ ገጽ በኩል ለንባብ ቀርበዋል።
ይኽ በላቲን ቋንቋ የተጻፈው በአምስት አበይት ዓለም አቀፍ ይፋዊ ቋንቋዎች ሥር ተተርጉሞ በቫቲካን ረዲዮ ድረ ገጽ በኩል ለሁሉም ይፋ የሆነው ደንብ የሥርወ እምነት (አንቀጸ እምነተ) ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዊሊያም ለቫዳ የሰጡት የመግቢያ ሰነድ የታከለበት ሆኖ፣ መለኮታዊ ግልጸት ተብለው የሚነገርላቸው መልኮታዊ አናሥር አለው የሚባለው የግልጸት ክስተት በቤተ ክርስትያንና በቤተ ክርስትያን ተልእኮ ከጥንት ጀምሮ የነበረ መለኮታዊ ክስተት ነው። ስለዚህ በተለያየ ወቅት ግልጸት ተብለው የሚነገርላቸውና የግልጸት ጸጋ የተቀበሉት የሚገልጡት መለኮታዊ ክስተት መሳይ ለይቶ በማጤን እውነተኛነቱ ለማረጋገጥ የሚያበቃ በቤተ ክርስትያን የተደነገገው የመመዘኛው ደንብ እ.ኤ.አ. በ 1978 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ተመርምሮ በሳቸው ውሳኔ አማካኝነት የጸደቀ መሆኑ አስታውሰው፣ ሆኖም ደንቡ ለብፁዓን ጳጳሳት ብቻ ተላልፎ በብፁዓን ጳጳሳት እጅ ብቻ የሚገኝ ሆኖ መቆየቱ ዘክረው፣ በአሁኑ ወቅት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛው ውሳኔ መሠረት ለሁሉም ይፋ ሆነዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ለቫዳ በመቅድሙ እንዳመለከቱትም፣ የእግዚአብሔር ቃል በቤተ ክርስትያን ሕይወትና ተልእኮ በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 5 ቀን እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በቫቲካን ተካሂዶ የነበረው 12ኛው የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ መሠረት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ህዳር 11 ቀን በ 2010 ዓ.ም. Verbum Domini - ቃለ እግዚአብሔር በሚል ርእስ ሥር የሰጡት ሓዋርያዊ ምዕዳን ጠቅሰው፣ ብቸኛው ይፋዊ ግልጸት እምነት የሚጠይቅና የእግዚአብሔር ቃልና እምነትን የሚደግፍ ግላዊ ግልጸት መካከል ያለው ልዩነት ሲገልጡ፣ በግል የሚሰጡት ግልጸቶች እውነተኛነታቸው የሚረጋገጠው ወደ ክርስቶስ የሚመራ እና በእርሱ ግልጸት ላይ የሚጸና ከሆነ ብቻ ነው። ስለዚህ ግላዊ ግልጸት እምነት የሚደግፍ፣ ከእምነት ጋር የማይጋጭ ወንጌልን በጥልቀት ለመረዳት የሚያግዝ፣ ለእምነት ተስፋና ፍቅር ማበረታታቻ ነው በማለት ቅዱስ አባታችን የሰጡት ማብራሪያ በመቅድሙ በመጥቀስ አስምረውበታል።
ግልጸት ተቀበልኩኝ የሚለውና የግልጸቱ ትክክለኛነት መመዘኛው ግብረ ገባዊ እርግጠኝነት ሥነ አእምሮአዊ ጤንነት የሕይወት ዝንባሌ የሚመለከት አወንታዊ መመዘኛ የሠፈረበት ሲሆን በሌላው መልኩም አሉታዊ መመዘኛ የሚባሉት፣ እግዚአብሔር በተመለከተ የሥርወ እምነት ሥሕተት የሌለው ለግል ጥቅም ማርኪያና ሃብት ማካበቻ እቅድ ላይ ያላነጣጠረ፣ ግልጸቱ ተቀበልኩኝ የሚለው አካል ከክፉ ተግባርና ነጻ መሆኑ የተሰኙት መመዘኛዎች ጭምር የታከበለት ነው ብለዋል።
ሰነዱም ግልጸት ታይቶበታል የሚባለውና ግልጸቱ የተቀበለው ምእመን በሚኖርበት አካባቢ ለምትገኘው ቤተ ክርስትያን ጳጳሳ ስለ ግልጸቱ በተመለከተ ቅርብ ፈጣንና ጥብቅ ክትትል የማድረግ ሐዋርያዊ ኃላፊነት የሚል መሠረታዊ ውሳኔ ያለው፣ አክሎም ጉዳዩ ለክልሉ ብፁዓን ጳጵሳት ምርክ ቤት ቀጥሎም ለሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ይተላለፍ የሚል መመሪያ ያካተተ መሆኑ ብፁዕ ካዲናል ለቫዳ በመቅድሙ ጥልቅ ማብራሪያ እንደሰጡበት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.