2012-05-30 17:19:06

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ የትምህርተ ክርስቶስ አጠቃላይ አስተምህሮ (30.05.2012)


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ በዚሁ ወቅት በምናደርጋቸው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮዎች ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቶቹ ስለ ጸሎት የሚያስተምራቸውን እያሰላሰልን፤ የክርስትያን ጸሎት እውነተኛና በኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከእግዚአብሔር አብ ጋር የሚደረግ ግላዊ ግኑኝነት መሆኑን ለመረዳት ሞክረናል፣ በዛሬው ትምህርተ ክርስቶስ ይህ ግኑኝነት “አዎ - ይሁን” የሚለው የእግዚአብሔር አብ ታማኝ እሽታና፤ “አሜን” የሚለው የምእመናን እምነታዊ መልስ ድርድር ውስጥ እንደሚገቡ እንመለከታለን፣ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው ሁለተኛ መልክት ስለዚህ ድርድር የሚያቀርበውን ለማስመር እወዳለሁ፣ ቅዱስ ጳውሎስ ይህችን ኃይለኛ መልእክት ብዙ ጊዜ በሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮው ወዳስቸገረችው ቤተ ክርስትያን ይጽፋል፤ የመልእክቱ ተቀባዮች እርሱ በክርስቶስና በወንጌል ያለውን ታማንኝነት እንዲያረጋግጥላቸው ልቡን ይከፍትላቸዋል፣ ይህች ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች የተላከች ሁለተኛ መልእክት፤ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ካሉ ከፍተኛ በሆነው የምስጋና ጸሎት ይጀምራል፣ እንዲሁም ይላል፤ “የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል፥ ስለዚህም እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን።” (2ቆሮ 1፡3-4)፣ በዚህም ቅዱስ ጳውሎስ እጅግ ፈታኝ በሆነ ሁኔታ እንደሚገኝ፤ ሊሻገራቸው የነበራቸው ችግሮችና ስቃዮች ብዙ እንደነበሩ ሆኖም ግን ጠቅላላ ህልውናውን ለእርሱ በሰጠው እና የእርሱ ሐዋርያና ምስክርር በሆነው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ቅርበት ተደግፎ ስለነበር ተስፋ ለመቍረጥ እጁን አልሰጠም፣ ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ይህችን መልእክት ለእግዚአብሔር ምስጋና የማቅረብ እና በቡራኬ ጸሎት የሚጀምረው፤ ምክንያቱ ደግሞ የክርስቶስ ሐዋርያ ሆኖ በተጓዘው ሕይወቱ መሐሪ የሆነውና የመጽናናት ሁሉ ጌታ የሆነው እግዚአብሔር ድጋፍ ፈጽሞ ስላልተለየው ነው፣ በዚችው መልእክት እንደሚገልጸው አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተሰቃይተዋል፤ ሆኖም ግን በዚሁ መውጫ መግቢያ የማይገኝበት በሚመስለው ሁኔታ ውስጥ ሳለ ከግዚአብሔር መጽናናትና ምቾት አገኘ፣ ክርስቶስን ለመስበክ በወኅኒ ቤት እስከ መታሰር ብዙ ስደት አጋጠመው፤ ሆኖም ግን ኢየሱስ ከእርሱ ጋር በመኖሩ በመነሳሳት እና የተስፋ ወንጌል ቃልን ለመስበክ በመፈለግ በልቡ ሁሌ ነጻነት ይሰማው ነበር፣ ታማኝ ተባባሪው ለሆነው ለጢሞቴዎስ ከወኅኒ ቤት እንዲህ ሲል ይጽፍለታል፣ በሰንሰለት ታስሮ ሳለ “ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም። ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን መዳን ከዘላለም ክብር ጋር እንዲያገኙ ስለ ተመረጡት በነገር ሁሉ እጸናለሁ።” (2ጢሞ 2፡9-10) ብሎ ጽፈዋል፣ ለክርስቶስ በሚሰቃይበት ግዜም የእግዚአብሔር መጽናናትን እንዳጣጠብመ ደግሞ “የክርስቶስ ሥቃይ በእኛ ላይ እንደ በዛ፥ እንዲሁ መጽናናታችን ደግሞ በክርስቶስ በኩል ይበዛልናልና።” (2ቆሮ 1:5) ብሎ ጽፈዋል፣
በሁለተኛ ቆሮንጦስ መግቢያ ባለው የምስጋና ጸሎት በመል እክቱ ተመልክቶ ባለው ሥቃይ መንጽር የመጽ ጽናናት ይዘትም ይገኛል፣ ይህ መጽ ጽናናት ቀላል የማመቻቸት ሁኔታ ሳይሆን ከሁሉም በላይ በፈተናና በችግር እንዳንሸነፍ የሚቀርብልን መበረታታትና መማጠን ነው፣ የሚቀርብልን ጥሪ ሁሌ ማንኛውንም ሁኔታ፤ ብርሃን ተስፋና ደህንነት እንዲያመጣልን የዓለም ስቃይንና ኃጢአትን በገዛ ራሱ ከተሸከመው፤ ከክርስቶስ ጋር አንድ በመሆን መኖር እንዳለብን ነው፣ ኢየሱስ በዚህ ሁኔታ እኛም በተራችን በማንኛው የስቃይ ሁኔታ የሚገኙትን ማጽናናት የምንችልበት ጸጋ ይሰጠናል፣ በጸሎት ከኢየሱስ ጋር የሚኖረን ጥልቅ ግኑኝነትና እርሱ በማሃከላችን መኖሩን የማመን ጉዳይ በወንድምሞቻችን ሥቃይና ችግር እንድንሳተፍ ፍቃደኞች እንድንሆን ያደርጉናል፣ ቅዱስ ጳውሎስ “የሚደክም ማን ነው፥ እኔም አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው፥ እኔም አልናደድምን?”(2ቆሮ 11፡29) ብሎ ይጽፋል፣ ይህ ሱታፌ ከቀላል መልካም ፍላጎት ወይንም ከሰብአዊ ርኅራኄ ወይንም ለሌሎች በሚደረግ አጋርነት አይነሳም፤ ሆኖም ግን “የኃይሉ ታላቅነት ከእኛ ሳይሆን ከእግዚአብሔር እንደሚመጣው) (2ቆሮ 4፡7) ይህ ሱታሬ ከጌታ መጽናናት ይፈልቃል፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች፤ ኑሮ አችንና ክርስትያናዊ ጉዞ አችን ሁል ዘወትር በችግር ባለመረዳዳትና በሥቃይ የተሸኙ ናቸው፣ ይህንን ሁላችን እናውቀዋለን፣ በጽኑ ዕለታዊ ጸሎት እና ከጌታ ጋር ታማኝ የሆነ ግኑኝነት በመመስረት እኛም ከእግዚአብሔር የሚመጣውን መጽናናት ተጨባጭ በሆነ መንገድ ልናገኘው እንችላለን፣ ይህንም እምነታችንን ያበረታታትል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች “ይሁን እሺ” በማለት የሚመልሰውን በገሃድ እንድናጣጥም ያደርገናልና፤ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ልጁን እስከመስጠት ያደረገው ለኔና ለሁላችን ያለው የፍቅር ታማኝነትን ያሳውቀናል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ያረጋግጥልናል፣ “በእኛ ማለት በእኔና በስልዋኖስ በጢሞቴዎስም በመካከላችሁ የተሰበከ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም፥ ነገር ግን በእርሱ አዎን ሆኖአል። እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነውና፥ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ስለ ክብሩ በእኛ የሚነገረው አሜን በእርሱ ደግሞ ነው።” (2ቆሮ 1፡19-20) የእግዚአብሔር አዎን ማለት የተከፋፈለ አይደለም፤ አዎን በማለትና አይደለም በማለት መሃከል የሚገኝ ሳይሆን የማያጠያይቅ እርግጠኛ አዎን ነው፣ ለዚህ የእግዚአብሔር አዎን እኛም አሜን ብለን አዎን በማለት መመለስ አለብን፤ ለዚህም በእግዚአብሔር አዎን እርግጠኞች እንሆናለን፣
እምነት መነሻው ከሰው ሳይሆን የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ነው፣ እርሱንና ወንድሞቻችን በማፍቀር ሕይወታችን እንዴት መኖር እንዳለብን በሚያስረዳን የእግዚአብሔር “አዎን” በሚለው ታማኝነቱ ላይ የሚመሠረት ነው፣ የእኛ አለመተማመንና ክህደቶች ቢኖርም ቅሉ ሐዋርያ ጳውሎስ ወደ ሮማውያን በጻፈው መል እክት እንደሚለው “እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና” (11፡29) መላው የደህንነት ታሪክ የዚሁ የእግዚአብሔር ታማኝነት ተራማጅ መገለጥ ነው፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች፤ ከእኛው ተግባር እጅግ ልዩ የሆነ የእግዚአብሔር ተግባር መጽናናት ኃይልና ተስፋ ይሰጠናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አዎን በማለቱ አይጸጸትምና፣ ቍርጠኝነትና መስዋዕትነት የሚጠይቁ ግጭቶች በዕልታዊ ሕይወታችን እና በቤተ ሰቦቻችን ሲያጋጥሙን በፍቅር ጸጋ አንጸናም፣ እግዚአብሔር ግን በእኛ ጉዳይ አይደክምም፣ ሁሌ በትዕግስቱንና በወደር የለሽ ምሕረቱ አስቀድሞ ስለሚጐበኘን ይህ አዎን ማለቱ ፍጹም ታማኝ ነው፣ በመስቀሉ ክንዋኔ ስፍር ቍጥር የሌለው ፍቅሩ መጠን ያሳየናል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቲቶስ ሲጽፍ “የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ ተገለጠ” (ቲቶ 3፡4) ይላል፣ ምክንያቱም ይህ አዎን ማለት “በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፥ ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ስለሆነ” (2ቆሮ 1፡21-22) በየዕለቱ ይታደሳል፣
እንደ እውነቱም ከሆነ ይህንን የእግዚአብሔር አዎን ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር በመሃከላችን እንዲኖርና ሕያው እንዲሆን የሚደርገአን በልባችን በልበ ሙሉነት እንድንሻው የሚያደግ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ይህም የሚሆነው በፍቅሩ በሰው እጅ ያልተሠራው ማኅደር በሰማይ ስናገኝ ነው፣ ምንም እንኳ ብዙውን ጊዜ ልበ ደንዳናዎች ወይንም ከሓዲዎች በመሆን እምቢ በማለት ብንጓዝ፤ ይህ ታማኝ ፍቅር የማይደርሰውና በእርሱ የማይነካ ማንም ሰው የለም፣ እግዚአብሔር ይጠባበቀናል፤ ዘወትር ይፈልገናል፤ ለእያንዳንዳችን የተትረፈረፈ ሕይወት ተስፋና ሰላም በሚሰጠው በእርሱ ኅብረት ሊቀበለን ይፈልጋል፤
በዚሁ የእግዚአብሔር አዎን ማለት በሥር ዓተ አምልኮ ተግባ የሚያስተጋባው የቤተክርስትያን አሜን ይሰርጻል፣ አሜን የሚለው የግላዊና ማኅበራዊ ጸሎቶቻችን መዝጊያ እግዚአብሔር በሰጠን ጸጋ ለእርሱ የምንሰጠው አዎን የሚል የእምነት መለስ ነው፣ ዘወትር በዘልማድ እምብዛም ሳናስተውል በጸሎት ጊዜ አሜን ብለን እንመልሳለን፣ አሜን የሚለው ቃል ከዕብራዊና አረማይካዊ ቋንቋ የሚሰርጽ ቃል ነው፣ ትርጉሙም “ተረጋጋ” “ጸና” ማለት ነው፣ በዚህ ሳቢያ “እርግጠኛ መሆን” ወይንም “እውነትን መንገር” ማለት ነው፣ በቅዱስ መጽሐፍ የተመለከትን እንደሆነ “አመን” የሚለው ቃል በምስጋና እና በማኅሌት መዝሙሮች መጨረሻ ላይ እናገኘዋለን፣ ለምሳሌ በመዝሙር 41፡13-14 “እኔን ግን ስለ ቅንነቴ ተቀበልኸኝ፥ በፊትህም ለዘለዓለም አጸናኸኝ። ከዘለዓለም እስከ ለዓለም የእስራኤሌ አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። አሜን አሜን።” ይላል፣ እንዲሁም ሕዝበ እስራኤል ከባቢሎን ስደት ደስታ ተሞልቶ በተመለሰበት ጊዜ ለእግዚአብሔር እና ለሕጉ አሜን በማለት እንድሚገዛ ያመለክታል፣ በመጽሐፈ ነህምያ ይንን ታሪክ እናገኛለን፣ “ዕዝራም በሕዛቡ ሁለ ላይ ከፍ ብሎ ሕዝቡ ሁለ እያዩ መጽሐፈን ገለጠ፤ በገለጠውም ጊዜ ሕዝቡ ሁለ ቆሙ። ዕዝራም ታሊቁን አምላክ እግዘአብሔርን ባረከ፤ ሕዝቡም ሁለ እጃቸውን እየዘረጉ። አሜን፥ አሜን ብለው መለሱ።” (ነህ 8፤5-6)
ከመጀመርያ ዓመታት ጀምሮ የአይሁድ ሥር ዓተ አምልኮ “አመን” የመጀምርያዎቹ ማኅበረ ክርስትያን “አመን” ሆነ፣ዋነኛ የክርስትያን የሥርዓተ አምልኮ መጽሐፍ የሆነው ራእዩ ለዮሐንስ በቤተ ክርስትያን “አሜን” ይጀምራል፣ “መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን” (ራእ 1፡5-6) ይላል፣ ጸሐፊው በምዕራፍ አንድ በመጽሐፉ መክፈቻ እንዳደረገው ሁሉ በመጽሓፉ መዝጊያም በዚህ ጸሎት ይደመድማል “አሜን! ና! ኢየሱስ ጌታ” (ራእ 22፡21)፣
ውዶቼ፧ ጸሎት ሕያው ከሆነ አካል ከሚሰማና መወያየት ከምትችልበት አካል ጋር የሚደረግ ግኑኝነት ነው፣ የማይታጠፍ መተማመኑን ከሚያሳድስ ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ ግኑኝነት ነው፣ ለእያንዳንዳችን በሕይወት ዘመናችን በሚያጋጥሙን ፈተናዎች መጽናናቱን እንዲሰጠንና ከእርሱ ጋር አንድ በመሆን በእርሱ የዘለዓለማዊ ሕይወት ፍጽምና በሚያገኙ በደስታና በመልካም ነገሮች የተሞላ ሕይወት እንዲኖረን ያደርጋል፣
በጸሎታችን ለእግዚአብሔር “እሺ” ለማለት የተጠራን ነን፤ የእርሱ የመሆን ምልክትና መላው የኑሮ ዘመናችን ለእርሱ ታማኝ መሆናችንን በሚገልጠው “አሜን” መመለስ አለብን፣ ይህንን መተማመን በኃይላችን ልንደርሰው በፍጹም አይቻልም፤ የዕለታዊ ተግባራችን ፍሬ ብቻ አይደለችም፣ ይህች ከእግዚአብሔር በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ “እሺ” ማለት የተመሠረተች ናት፣ ክርስቶስ በወንጌል ይህን ሲያረጋግጥልን “የኔ ምግብ የአባቴን ፍቃድ ማድረግ ነው”(ዮሐ 4፡34) ይላል፣ በዚሁ የክርስቶስ “አዎን” ማለት ነው መግባት ያለብን፣ ለእግዚአብሔር ፈቃድ መገዛት፣ ይህን በማድረግ ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለው በመጨረሻ የምንኖር እኛ አይደለንም ነገር ግን ክርስቶስ ራሱ ነው በእኛ የሚኖረው እስከማለት መድረስ ማለት ነው፣ ስለዚህ የግላዊና ማኅበራዊ ጸሎታችን “አሜን” ማለት መላው ሕይወታችን በማጠቃለል ይለውጠዋል፣ በዚህም በዘለዓለማዊና በማይለወጥ ፍቅር የሰጠመ የእግዚአብሔር መጽናናት ያለበት ሕይወት ለመኖር እንችላለን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.