2012-05-29 09:32:14

የብፅዕና አዋጅ


እ.ኤ.አ. ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም. በፈረንሳይ የአብዮት ዘመን የነበሩት እ.ኤ.አ. በ 1803 ዓ.ም. የቅዱስ ልዊጂ የፍቅር ደናግል ማኅበር መሥራች እናቴ ማሬ ሳይንት ልዊሰ ደ ላሞይኞን ቅድስት ቤተ ክርስትያን ትላትና በይፋ ብፅዕና እንዳወጀችላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ትላትና እኩለ ቀን ጸሎት ንግሥተ ሰማይ ከመድገማቸው ቀደም በማድረግ ባስተላለፉት ኵላዊ መልእክት፣ እናቴ ማሬ ሳይንት ልዊስ ደ ላሞይኞን ለእግዚአብሔርና ለባለንጀራ የሚኖረው ክርስትያናዊ ፍቅር በቃልና በሕይወት የመሰከሩ የፍቅር መስካሪ በማለት እንደገለጡዋቸውም ሲገለጥ፣ ብፅዕናውን በይፋ ለማወጅ ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ባሰሙት ስብከት፣ ብፅዕት እናቴ ማረ ሳይንት ልዊስ ቋንቋቸውና ሕይወታቸው ወንጌላዊ ፍቅር በማድረግ የኖሩ ለተራቡት ለተጠሙት ለድኾች ከትምህርት ገበታ ለተገለሉት ሁሉ ቅርብ በመሆኑ ለነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል በወንጌላዊ ፍቅር አማካኝነት በሚያስፈልጋቸው መስክ በማገልገል ወደ ብፅዕና የሚመራው የላቀው ክብር በማስተማር፣ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር የተናቁትን በማገልገል የኖሩ የቤተ ክርስትያን ልጅ በማለት እንደገለጡዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
በመስቀል እግር ሥር የነበረቸው የቅድስት ድንግል ማርያም አብነት በመከተልም ይኸንን የመስቀል ቲዮሎጊያና መንፈሳዊነት መርህ በማድረግ ማለቂያ በሌለው የእግዚአብሔር ፍቅር ወንድሞችን ለማገልገል የፍቅር ብሔረ ሥልጣኔ እንዲገነባ በግል የቅድስና ሕይወት ለመኖር በእግዚአብሔር ድጋፍ የሚታገሉት የሚኖርበት የፍቅር የደናግል ማኅበር በቤተ ክርስትያን ፈቃድ ሥር የመሠረቱ መሆናቸውም እንዳስታወሱ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ዛሬ ጥላቻ አለ መግባባት ቅናት ምቀኝነት በተስፋፋበት ዘመን በቤተ ክርስትያንና በኅብረተሰብ ቅዱሳን እንደሚያስፈልጉ ብፁዕ ካርዲናል አማቶ በማብራራት ያሰሙት ስብከት እንዳጠቃለሉ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.