2012-05-29 09:33:25

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “ከባቢሎን ወደ ጸርሓ ጽዮን”


ሁሌ በሳምት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል “ከባቢሎን ወደ ጸርሓ ጽዮን” በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ለከበሩት 85ኛው ዓመት እድሚያቸውና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው በእግዚአብሔር ፈቃድ የተሾሙበት ሚያዝያ 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ዝክረ ሰባተኛው ዓመት ምክንያት የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ባቀረቡላቸው የምሳ ግብዣ ተገኝተው “በጸረ ክፍት መንፈስ ትግል ከጌታ ጋር የሚተባበሩና ኅብረት የሚኖራቸው” በማለት ብፁዓን ካርዲናሎችን ገልጠው፣ በዚህ በሚደረገው የጸረ ክፋት መንፈስ ትግል በተመሳሳይ ዓላማና ጥሪ የሚጠመዱ ጓደኞች መኖራቸው እንዴት ደስ ያሰኛል በሚል ቀዉም ነገር ላይ ያተኮረ ያሰሙትን ንግግር አባ ሎምባርድ በማብራራት፣ የቤተ ክርስትያን ኅዳሴ መሥዋዕትነት በሚል ቃል እርሱም በክፋታ መንፈስ እና በቅዱስ መንፈስ መካከል ባለው ትግል የሚገለጥ መሆኑ በመተንተን፣ ብርቱ አሳማኝ ድል አድራጊ መሳይ፣ የመልካምነት ካባ ለብሶ ሳይታወቅ ውስጥ ለውስጥ የሚንቀሳቀስን ተንኮለኛው የክፋት መንፈስ ለመቃወም ቤተ ክርስትያን በምታካሂደው የጸረ ክፋት ትግል ከባቢሎም ወደ ጸርሓ ጽዮን በሚል እርሱም በላቲን ሥርዓት እሁድ የተከበረው በዓለ ጰራቅሊጦስ ላይ በማተኮር ቅዱስ አባታችን በሁለት ዓይነት ፍቅር ዘንድ ያለው ውስጣዊ ትግል፣ እርሱም እኔ ባይነት ራስ ወዳድነት የሚልና ገዛ እራስ መካድ የተሰኘው እግዚአብሔርን ለማፍቀር የሚመራ እውነተኛ እራስ ማፍቀር የሚል መሆኑ በጥልቀት የሚገልጥ ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያሰሙት ሥልጣናዊ አጭር መልእክት ቅዱስ ኢግናዚዮስ ዘ ሎዮላ ቃል የተገባ ፍስኃ ሆኖም ግን በተግባር በዕለታዊ ጉዞ እንቅፋት የሚፈጥር ተገዥ የሚያደረግ በሁለተኛው ደረጃ ደግሞ እውነተኞች የጌታ ጓደኞችና አገልጋዮች በሆኑት አበ ነፍሳትና እውነተኛ የነፍሳት አስተማሪዎች አማካኝነት፣ የታደልነውን የመለየት ችሎታ በማጎልበት እውነት ከሐሰት ለይተን እውነትን ከመከተል የሚገኘው ፍስኃ በሚል አገላለጥ ያብራራው የእውነተኛው ደስታ መሠረት የሚያበክርና የእውነተኛ ወዳጅና ጓደኛ ትርጉም የሚገልጥ ነው።
ምንም’ኳ በዚህ በምንኖርበት ዘመን በቤተ ክርስትያንና በኅብረተሰብ ላይ የክፋት መንፈስ ያንዣበበ ቢመስልም፣ ድቅድቅ ያለ ጨለማ ቢጋረጥብንም ከዚህ ያለ መግባባትና የመለያየት ምልክት ከሆነው ከባቢሎናዊነት ወደ ሱታፌና መግባባት ምልክት ወደ ሆነው ጽርሓ ጽዮን እንድንልና ከመንፈስ ቅዱስ የሚለገሰው የመጽናናትና የብርታት ጸጋ በእኛ ላይ እንዲወርድ የምንጸልይበት ዓቢይ በዓል ነው በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.