2012-05-26 09:28:11

ጸሎት በቻይና ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን


በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በላቲን ሥርዓት ግንቦት 24 ቀን በሚውለው የረዳኢተ ክርስትያን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሚውልበት ቀን፣ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን በቻይና ስለ ምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሚጸለይበት ቀን እንዲሆን የሰጡት ውሳኔ በመከተል ይኸው እ.ኤ.አ. ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. በመላ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በቻይና ስለ ምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መጸለዩ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
“ረዳኢተ ክርስትያን ቅድስት ድንግል ማርያም” በአቢይ አክብሮት መንፈሳዊነቱ በሚኖርበት ሻንጋይ በሚገኘው ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ክብረ በዓሉ ምክንያት በቻይና ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መጸለዩ ያመለከተው የቅስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ቅዱስ አባታችን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥቃይና መከራ ከሌላ ሥፍራ ይልቅ በዚያች ዕለት በዕለት በሚኖርባት አገረ በቻይና ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በመላ ዓለም የሚገኙት ካቶሊክ ምእመናን እንዲጸልዩ ባለፈው እሁድ እኩለ ቀን ጸሎት ንግሥተ ሰላም ከማሳረጋቸው ቀደም በማቅረብ ባሰሙት ንግግር ሲያሳስቡ፣ በቻይና የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመናን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማበሰር ያለው የምነት ደስታ ትህትና በተሞላው መንገድ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይና ለሐዋርያት ተአምኖተ ኑዛዜ ታማኞች ሆነው እንዲመሰክሩ በቻይና ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያንና ምእመናን እንጸልይ እንዳሉም የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. በቻይና ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ባስተላለፉት ሓዋርያዊ መልእክት፣ የቻይና ካቶሊክ ምእመናን ለክርቶስና ለቤተ ክርስትያኑ ያላቸው ታማኝነት እጅግ ደስ የሚያሰኝ መንፈስን የሚያበረታታ መሆኑ ገልጠው፣ መሥዋዕትነት ለሚጠይቅ ሥፍራና ጊዜ የእምነት ምስክር ሆኖ መገኘት በእውነት የእምነት ጽናትና ብርታት የሚጠይቅ ነው። ገንቢ እና መከባበር የተካነው የጋራ ውይይት በቻይና ካቶሊክ ምእመናንና በቻይና በምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እንዲረጋገጥ በማሳሰብም በቻይና የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የራስ ጥቅም የማይል ለቻይና ካቶሊክ ሕዝብ ጥቅም መረጋገጥ ባቀና አገልግሎት በርትታ ትሰማራ ዘንድ አደራ እንዳሉም የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.