2012-05-26 09:29:46

ብፁዕ ካርዲናል ቨሊዮ፦ የሴቶች ተፈናቃዮችና ስደተኞች መብትና ክብር


በቅድስት መንበር ለተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ልኡከ መንግሥት ጽ/ቤት ያነቃቃው “ሴቶችና ጽናት” በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ ስለ ሴቶች ተፈናቃዮችና ስደተኞች መብትና ክብር ላይ አተኩሮ ያደረገ ሮማ በሚገኘው የሥነ አመሪካ የጥናት ማእከል በተካሄደው ጉባኤ ተሳትፈው ንግግር ያሰሙት የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ፣ ሴቶች ተፈናቃዮችና ስደተኞች ስንቱን መከራ ጅምላዊ ቅድመ ፍርድ መሰናክሎችና በተለያየ መልኩ የሚደርስባቸው ዘርፈ ብዙ አመጽ የተሻገሩ ስለ ልጆቻቸው ቤተ ሰቦቻቸው ወላጆቻቸው ሕይወት መሻሻልና እድገት ገዛ እራሳቸው ለተለያየ አደጋ በማጋለጥ ለስደት የተዳረጉ ሴቶች በቁጥር ብዛት ብቻ ሳይሆን በእለታዊ ኑሮአቸው ለዚያ መልካም ዓላማ ማለትም ልጆች ወላጆች ጥቅም ላይ በማተኮር እንደሚመሩ ጉዳያቸውን ቀርቦ ከመመልከት የተረጋገጠ ነው እንዳሉ አውደ ጥናቱን የተከታተሉት የቫትካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ካጠናቀርቡት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
በዚህ የፖሊቲካና የተለያዩ የግብረ ሠናይ ማኅበራት እንዲሁም የኢጣሊያ መንግሥት ልኡካንና የበላይ አካላት በተሳተፉበት ጉባኤ ንግግር ያሰሙት ብፁዕ ካርዲናል ቨሊዮ፣ ሴቶች ስደተኞች በተስተናገዱበት አገር ተዋህደው እንዲኖሩ ለማገዝ ታልሞ የሚቀርበው የግብረ ሠናይ አገልግሎት በተለየ መልኩ የስደተኞች ሴቶች ልጆች ዓቢይ ግምት የሚሰጥ መሆን አለበት ካሉ በኋላ አያይዘውም የተለያዩ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የግብረ ሠናይ ማኅበራት ለሴቶች ስደተኞችና ተፈናቃዮች በተለየ መልኩ ያተኮረ አገልግሎት እንደሚያቀርቡ አስታውሰው፣ የድኾች አገሮች ለውጭ ንግድ አቅርቦት፣ የአመራረት ሂደቱ የአምራቾቹ በዕለታዊ ሕይወት የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ አማካኝነት የሚመዘን መሆን አለበት። ምርት ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ሰብአዊነቱና ሰብአዊ መብቱና ክብሩ ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መከበር ግድ በሚል የላቀው እሴት ትግባሬ ወሳን ነው እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠና ጂሶቲ ገልጠዋል።
በጉባኤው ተገኝተው ንግግር ያሰሙት የካሪታስ ኢንተርናዚዮሊስ የፖለቲካ ጉዳይ ለሚከታተለው ቢሮ ተጠሪ ማርቲና ላይብሽ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን አደንዛዥ እጽዋትና ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ንግድ ይልቅ የሰው ልጅ ለአዲስ ባርነት ለሚዳረጉት ኢሰብአዊ ተግባር መሣሪያ እንዲሆኑ ታልሞ በወንጀል ቡድኖች የሚፈጸመው ሕገ ወጥ የሰው ልጆች ከቦታ ቦታ ማዘዋወር እጅግ የማያዳግት መሆኑ ገልጠው፣ ይኽንን የኅብረተሰብ ነቀርሳ የሆነው በሕገ ወጥ ተግባር የሰው ልጅ ከቦታ ቦታ የማዘዋዋሩ የወንጀል ቡድኖች የሚፈጽሙት ጸያፍ ኢሰብአዊ ተግባር፣ እንዲገታ በማድረጉ ዓላማ የዓለም ዓቀፍ መንግሥታት ይተጉ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ጋዜጠኛ ጆሶቲ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.