2012-05-21 14:32:16

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “የሃይማኖትና የኅሊና ነጻነት”


ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈረዲኮ ለምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል ይኸው ትላትና የሃይማኖትና የኅሊና ነጻነት በሚል ርእስ ሥር፣ የሃይማኖትና የኅሊና ነጻነት በዚህ ባለንበት ዘመን እየተስፋፋ RealAudioMP3 ባለው በተዛማጅ እርሱም በአልቦ እሴት ባህል ምክንያት ለአደጋ ተጋልጦ እንደሚገኝ፣ በቅርቡ የካናዳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሃይማኖት ነጻነት በተመለከተ ያወጣው የአቋም መግለጫ ምስክር መሆኑ ገልጠው፣ የካናዳ ብፁዓን ጳጳሳት “የሃይማኖትና የኅሊና ነጻነት” በሚል ርእስ ሥር ባስተላለፉት ግብረ ኖላዊ መልእክት፣ እሴቶችና የሕይወት ክቡር ዋጋ የሚያነቃቃ፣ በማንኛውም አገር የሚኖር የካቶሊክ ቤተ ርክስትያን ምእመን የሚመለከትና በእርሱ ሊመሰከር የሚግባውም ነው። ስለዚህ ብፁዓን ጳጳሳት ያተኮሩበት ነጥብ የቤተ ክርስትያን ኩላዊነት ባህርይ የሚያጎላ ነው ብለዋል።
ዘመናችን ታማኝና እውነተኛ ክርስትያናዊ ምስክርነት የሚጠይቅ ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዘንድሮ እ.ኤ.አ. 2012 ዓ.ም. መባቻ ምክንያት በቅድስት መንበር ለተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት ተቀብለው ባሰሙት የ2012 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት የአማኞች ተቀዳሚው ኃላፊነት እንዳሰመሩበት አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጽ በማስታወስ የካናዳ ብፁዓን ጳጳሳት ያንን የቅዱስነታቸው ሃሳብ በማጉላትና መሠረት በማድረግ በካናዳ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ያስተላለፉት ግብረ ኖላዊ መልእክት በዓለማችን የሃይማኖትና የኅሊና ነጻነት ምንኛ ለአደጋ መጋለጡ የሚያበክር ነው።
በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ከሰባ በመቶ በላይ አገሮች የሃይማኖት ነጻነት፣ የግልና የማኅበራዊ አምልኮና ስግደት ነጻነት ለአደጋ ተጋልጦ እንደሚገኝና በዓለማችን ይፈጸማል የሚባለው ስደትና መከራ ውስጥ ከጠቅላላ 75 በመቶ የሃይማኖት ስደት የሚመለከት መሆኑ፣ የማይማኖትና የብሔር ህይወት ጉባኤ ያወጣው መግለጫ ዋቢ በማድረግ ከገለጡ በኋላ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እጅግ አደገኛ የሆነው አጥቂው ተዛማጅ ባህል፣ እርሱም እውነት ነው ብሎ የሚነዛው ሥነ ሃሳብ ተቀባይነቱ ግድ የሚል እየሆነ፣ በተለያየ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘንድ ሥር እየሰደደ በመዛመት ላይ መሆኑ የሰጡት ማብራሪያ አባ ሎምባዲ አስታውሰው፣ ቤተ ክርስትያንና ምእመናን የሃይማኖትና የኅሊና ነጻነት መከበር እንዳለበት ጥሪ ሲያቀርቡ የማኅበራዊ ጥቅም የሚሹ መሆናቸው ነው የሚመሰክሩት፣ ቅዱስ አባታችን በሎንደን ዌስት ሚንስትር አዳራሽ እንዲሁም በጀርመን የሕዝብ ተመራጮች ምክር ቤት ፊት ተገኝተው ያሰሙዋቸው ንግግሮች፣ ከፍትኛ ገንቢ ውይይት እንዲረጋገጥ ያስገነዘቡት ሀሳብ መሠረት በማድረግ የሃይማኖትና የኅሊና ነጻነት እንዲከበር የምናደርገው ጥረት እንቀጥልበታለን በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.