2012-05-21 14:30:47

46ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን “ጽሞናና ቃል፣ የአስፍሆተ ወንጌል ሂደት”


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንዳስታወሱት፣ ትላትና 46ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን “ጽሞናና ቃል፣ የአስፍሆተ ወንጌል ሂደት” በሚል ርእስ ተመርቶ ታስቦ መዋሉ ሲታወቅ፣ ቅዱስነታቸው ቀኑን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን RealAudioMP3 የተመራበት ርእስ ጽሞናን ቃል፣ የመገናኛ ብዙኃን “ሚዛን፣ ሂደትና ውህደት” የሚያጎላ መሆን እንዳለበት የሚያመለክት እንደሆነም ጳጳሳዊ የመገናኛ ብዙሃን ጉዳይ የሚንከባከበው ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ክላውዲኦ ማሪያ ቸሊ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን በጽሞናና በቃል መካከል ያለው ግኑኝነት ሲያስረዱ፣ ቃል አለ ጽሞና ባዶ ነው። ስለዚህ ከጸጥታና ከአስተንትኖ ያልመነጨ ቃል ባዶ ቃል ከመሆኑም ባሻገር፣ ቃል አገናኝ ባህርዩንም ጭምር እንደሚያጠፋ ነው። ስለዚህ ጽሞናና ቃል ተሟይ ናቸው፣ ጸጥታ አለ ቃል፣ ቃል አለ ጸጥታ አይጸናም። የምጠቀምበት ቃል፣ ከጽሞናና ከአስተንትኖ የመነጨ መሆኑ አለበት፣ የቃል ጥልቅ ትርጉሙና የላቀው ክብሩ ከማስቀድመው ጽሞና ነው የምረዳው።
የእግዚአብሔር ቃል ያለው ጥልቅ መልእክቱን ለመረዳት በጽሞና ልናዳምጠው ይገባናል፣ ውስጣችንን የሚነካ ወደ ልባችንና አእምሮአችን የሚዘልቀው በጸጥታ ስናዳምጠው ብቻ ነው። በጽሞና ሲደመጥ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ለማስፋፋት በሚከናወነው አገልግሎት የምድር እርሾ እውነተኛና ታማኝ አገልጋይ ለመሆን ያበረታል። ስለዚህ ጸጥታ ጽሞና እንዲህ ባለ መልኩ ሲጤን አሉታዊ ገጽታ አይኖረውም።
ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት፣ በርግጥ የተለያየ መዋእል ሰው፣ እውነትን በመሻትና እርሷን በመፈለግ በጥያቄና በመልስ መድረክ የሚጓዝ ቢሆንም ቅሉ፣ ከጽሞና በማይመነጩ ቃላትና መልሶች መጥለቅለቅ የሚታይበት ዘመን ነው፣ ይኽ ደግሞ እውነትን ለመሻትና ከእርሷ ጋር ለመገናኘት የሚያደረገው ጉዞ የሚያሰናክል ሆኖ ይገኛል። ስለዚህ መልስ ይሆናል ያልነው መሰናክል ሆኖ ይቀራል። ቃል ያለው አቢይ ትርጉም በጽሞና መቅድም እስካልተሸኘ ድረስ ልንረዳው አንችልም። የእግዚአብሔር ቃል አዳምጦ አጣጥሞ የሕይወት መርህ በማድረግ ለሌሎች ለማካፈል ልክ እንደ ቅድስት ድንግል ማርያም በጽሞና ማዳመጥና በልብ መያዝ ያስፈልጋል።
የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ድረ ገጽ የተለያዩ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ዕለቱን ምክንያት በማድረግ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሥልጣናዊ መልእክት ሥር በመመራት የተከተሉት ጅምሮችና የነደፏቸው መርሃ ግብሮች በተመለከተ የተለያዩ መግለጫዎች አቅርቧል ይኽ ደግሞ መላ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ዕለቱ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መልእክት ሥር በተወሃደ መልክና ይዞታ እንዳከበረቸው የሚያረጋግጥ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.