2012-05-18 14:27:08

“Nostra Aetate-ያለንበት ዘመን”


ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝክረ 50ኛው ዓመት በተለያዩ ዓውደ ጥናቶችና ጉባኤዎች አማካኝነት በመከበር ላይ መሆኑ ሲታወቅ፣ ይኸው ከትላንትና በስትያ የክርስትያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤትና የቅድስት መንበር ከተለያዩ ሃይማኖቶችና ከአይሁድ ሃይማኖት ጋር የሚደረገው ግኑኝነት RealAudioMP3 ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኮኽ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ክርስትያን ካልሆኑት ሃይማኖቶች ጋር ግኑኝነት በተመለከተ “Nostra Aetate-ያለንበት ዘመን” በሚል ርእስ ሥር ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የሰጠው መግለጫ ዝክረ 50ኛው ዓመት ምክንያት ሮማ በሚገኘው በጳጳሳዊ ቅዱስ ተማዞ ዘአኵይኖ መንበረ ጥበብ ተገኘተው ሥልጣናዊ አስተምህሮ መስጠታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በዚህ የአይሁድ ሃይማኖት መምህር ጃክ በምፖራል አስተዳዳሪነት የሚመራው የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት የሚያነቃቃው ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ማእከል በየዓመቱ ከሚያካሄዳቸው የውይይት መርሃ ግብር መሠረት እ.ኤ.አ. በ2012 ዓ.ም. ክፍለ ጉባኤ ተገኝተው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያንና የአይሁድ ሃይማኖት የጋራ ግኑኝነት ዝክረ 50ኛው ዓመት “Nostra Aetate-ያለንበት ዘመን” ዋቢ በማድረግ የግኑኝነቱ ጅማሬና ታሪካዊ ሂደቱ ብሎም ያስጨበጠው ውጤት ዳሰው፣ “በክርስትያኖችና በአይሁዶች መካከል ላለው መንፈሳዊ ወንድማማችነት ጽኑና ዘለዓለማዊ መሠረቱ መጽሓፍ ቅዱስ ነው”። ከዚህ እርግጠኝነት በመንደደር ብፁዕነታቸው፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔ መሠረት የአይሁድ እና የክርስትያኖች የጋራው ውይይት 50ኛውን ዓመት በማስተንተን፣ “Nostra Aetate-ያለንበት ዘመን” የዚህ የጋራው ግኑኘንት መርህ መሆኑም ጠቅሰው፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአሁድ እምነት ተከታዮች ላይ ለተፈጸመው እልቂትና ዓመጽ ጠንሳሾች የክርስትናውን እምነት በተግባር የማይኖሩ ክርስያኖች ናቸው። የዚህ እልቂት ሰለባ ከሆኑት ውስጥም እውነተኞች ክርስትያኖች እንደሚገኙበት ዘክረው፣ ብዙዎች ይኽ የእልቂት ተግባር በዝምታ የተመለከቱ መሆናቸውም ገልጠው፣ ይኽ የእልቂት ውሳኔ ለክርስትናው እምነት ጥያቄ ከመሆኑ ባሻገር ወቀሳም ጭምር አስከትለዋል፣ ይኸንን ሁሉ ግምት በመስጠት ኵላዊት ቤተ ርክስትያን በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ “Nostra Aetate-ያለንበት ዘመን” በሚልው ውሳኔ መሠረት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያንና የአይሁድ እምነት ግኑኝነት ቲዮሎጊያዊ ፍችና ተነቦ” እንደሰጠችበትም አብራርተዋል።
ይህ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የተጀመረው አዲስ ሂደት፣ በሚከተስቱት አዳዲስ የጸረ ሴማዊ ተግባሮች አማካኝነት በተለያየ ወቅት ለተለያየ አደጋ ሲጋልጥም ይታያል፣ ይኸንን አዲስ ጸረ ሴማዊ ተግባር ከማንም በማንም ይነቃቃም፣ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ጸረ ሴማዊ ጸረ የክርስትና እምነት ወይንም የክርስትና እምነት መካድ ማለት መሆኑ በመግለጥ ከመቃወምና ከማውገዝ አልተቆጠበችም” ብለዋል።
“ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መጽሓፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ የክርስትያንና የአይሁድ እምነት ግኑኝነት በጋራ መከባበር መግባባት እና መተዋወቅ ላይ የጸና እንዲሆን ያሰመረበት ሃሳብ ፈጽሞ መዘንጋት የለበትም” ካሉ በኋላ ቅድስት ቤተ ክርስትያን በተለያዩ ዘርፎች ከአይሁድ ሃይማኖት ጋር የምታካሂደው የጋራው ግኑኝነት ፍጻሜዎችና ያስጨበጣቸው ውጤቶች በማስታወስ ለዚህ ውጤት የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊና የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አስተዋዖ ተንትነዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.