2012-05-18 14:28:50

ዓውደ ጥናት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” ፦ ሥነ ጥበብ ውበትና ከነገር ባሻገር


የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” በሚል ርእስ የተመራ የዓለማችን አበይት እና አንገብጋቢ ርእሰ ጉዳዮች በማስደገፍ በአማኞች እና በኢአማኒያን መካከል የሚሰጠው መልስ የሚያወያይ እምነት እና ምርምር የማይነጣጠሉ የሚደጋገፉ መሆናቸው ለማረጋገጥ RealAudioMP3 ዓልሞ ያነቃቃው፣ እምነት እና አልቦ እምነት በአንድ አንገብጋቢ ርእስ ሥር አገናኝቶ የሚያወያይ በኢጣሊያ ቦሎኛ ከተማ ያስጀመረው መርሃ ግብር በፓሪስ በቡካሬስት በፊረንዘ በሮማና በቲራና እ.ኤ.አ. በ2012 ዓ.ም ግንቦት ወር ማብቅያ በኢጣሊያ ፓለርሞ ከተማ “የሕጋዊነት ባህልና ኅብረሃይማኖተኛ ኅብረተሰብ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ ዓውደ ጥናት አካሂዶ ይኸው ወደ ስፐይን እንዳቀና ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚዘከር ሲሆን፣ ይኽ በስፐይን ባርቸሎና ከተማ እ.ኤ.አ.ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም. የተጀመረው ዓውደ ጥናት ዛሬ እ.ኤ.አ. ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ተጠናቀዋል።
ባርቸሎና በሚገኘው በራሞን ሊዩል መንበረ ጥበብ መምህር የቲዮሎጊያና የፍልስፍና ሊቅ ፕሮፈሰር ፍራንሰስ ቶራልባ ሮሰሎ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በስፐይን ታሪክ ባርቸሎና የግኑኝነትና የውይይት ከተማ መሆንዋ ነው የሚነገርላት፣ ትክክል ነው፣ ስለዚህ ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት ዓውደ ጥናቱ በባርቸሎና እንዲካሄድ መወሰኑ አለ ምክንያት አይደለም። ተፈጥሮአዊ ውበት፣ የሥነ ጥበብ ውበት የሥነ ሙዚቃ ውበት በጠቅላላ የፍጹም ውበት መግለጫዎች ናቸው፣ ስለዚህ ይኸንን ውበት ለመለየት የሚያበቃን በቅጽበት የመገንዘብ ባህይርያዊ ብቃት አማክኝነትም የእግዚአብሔር/የፈጣሪ ውበት መግለጫ መሆኑ እንረዳለን። ስለዚህ ውበት ከነገር ባሻገር / ዳር ማዶ ለመመልከት የሚገፋፋ ጥሪ ነው። ሆኖም በዚህ ግፊት አማካኝነት በርግጥ ወደ እግዚአብሔር በሙላት ይደረሳል ማለት አይደለም፣ ወደ እግዚአብሔር ከሚመሩት መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው ካሉ በኋላ ባርቸሎና በሥነ ጥበብ በሥነ ሙዚቃ በኅብረ ሃይማኖትና ኅብረ ኅብረተሰብ የታደለች አገር በመሆንዋ ዓወደ ጥናቱ በባርቸሎና መካሄዱ ምክንያታዊ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.