2012-05-16 15:01:09

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ምስል አለ አግባብ የተጠቀመው ድርጅት በነቶን በይፋ ይቅርታ ጠየቀ


የበነቶን ኩባኒያ ለንግድ የሚያቅርበው ምርቶቹ በንግድ ዓለም ውጤት እንዲኖረውና ገዢው ሕዝብ ለመማረክ ዓልሞ ባወጣው የምርት ማራኪ ማስታወቂያ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በመጠቀም ምክንያት በኵላዊት ቤተ ክርስትያንና በምእመናን ዘንድ ያሳደረው ቅሬታና የምእመን ሕዝብ RealAudioMP3 ስሜት በከፋ ሁኔታ በመንካቱ በቅድስት መንበርና በድርጅቱ መካከል ተከስቶ የነበረው አለ መግባባትና ጉዳዩ በፍርድ ቤት በኵል የሚታይ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ፣ ይኸው ድርጅቱ ባለፈው ዓርብ በይፋ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይና መላ መእመናን ይቅርት በመጠየቅ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲትክቶስ 16ኛ ምስል ያኖረበት አሰራጭቶት የነበረው የምርት ማስታወቂያ ማስወገዱ አስታውቀዋል።
እ.ኤ.አ. ህዳር 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ተከስቶ የነበረው የኵላዊት ቤት ክርስትያንና የመላ ምእመናን ስሜት በአሉታ የነካው በነቶን ድርጅት የፈጸመው ተግባር መሠረት ወዲያውኑ ቅድስት መንበር የዚያ ምስል ጸያፍነቱ በማብራራት አለ አግባብና ላልተገባ ዓላማ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ምስል መጠቀም ስህተት ብቻ ሳይሆን ሕገ ወጥና ለክስ የሚያጋልጥ፣ ለኵላዊት ቤት ክርስትያንና ለመላ ምእመናን ዘለፋ መሆኑ የይፋ መግለጫ በማውጣት አስታውቃ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ባለፈው ዓርብ የበነቶን ድርጅት በፈጸመው ተግባር ተጸጽቶ በይፋ የጠየቀው ይቅርታ ብዙ የታወቀም አይመስልም፣ ምክንያቱም በነቶን አውጥቶት የነበረው ማስታወቂያ በተመለከተ የመገናኛ ብዙሃን በፍጥነት ብዙ ለመናገር ባሳዩት ፍጥነትና ግንዛቤ፣ ድርጅቱ በይፋ የሰጠው የይቅርታ ጠያቂ መግለጫ በተመሳሳይ ፍጥነት ሲያሰሙ እንዳልታዩ፣ በነቶን ቅድስት መንበርንና መላ ካቶሊክ ምእመናንን በይፋ ይቅርታ መጠየቁ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ትላትና በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በማብራራት፣ ጉዳዩ ቀደም ተብሎ በፍርድ ቤት በኵል እንዲታይ ቀርቦ የነበረው የቅድስት መንበር ሃሳብ ድርጅቱ በይፋ በጠየቀው ይቅርታ ምክንያት ክሱ መነሳቱ ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.