2012-05-16 18:02:54

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፤ በመጨረሻዎቹ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮዎች በግብረ ሐዋርያት ስለሚገኘው ጸሎት አስተንትነናል፤ በዛሬው ትምህርታችን በአሕዛብ ሐዋርያው በቅዱስ ጳውሎስ መልእክቶች ስለሚገኘው ጸሎት ለመናገር እወዳለሁ፡፡ መልእክቶች በጸሎት የሚጀምሩትና የሚደመድሙት እንደአጋጣሚ ሳይሆን በዓላማ መሆኑን ለማስመር እወዳለሁ። እንደ መግቢያ የሚጠቀሙት ጸሎት የምስጋናና የስባሔ ሲሆን በመጨርሻም መልእክቱ ለሚጻፍለት ማኅበር ጉዞ የእግዚአብሔር ጸጋ እንዲመራው የሚማጠን መልካም ምኞት ነው። ከመግቢያ ጸሎቶች አንዱ “አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ” (ሮሜ 1፡8) ይላል፡ የመልካም ምኞት መዝጊያው ደግሞ “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን” (1 ቆሮ 16:23) ይላል፡ የሐዋርያው መልእክቶች ይዘትም በዚሁ መልክ ይሰፋሉ። የቅዱስ ጳውሎስ ጸሎት ከምስጋና ወደ ቡራኬ፡ ከስባሔ ወደ ልመናና መማጠን፡ ከማኅሌት ወደ ስለት የሚንቀሳቀሱ ታላቅ የጸሎት ሥርዓት ሃብቶች ይገልጣል። እነኚህ የተለያዩ የጸሎት አገላለጾች ጸሎት በግል ሕይወታችን ይሁን በምንኖርበት ኅብረስተሰብ ዕለታዊ ሁኔታዎች ላይ ምን ያህል ተራ እንዳለው ያሳያል።
ሐዋርያው ሊያስረዳን የሚፈልገው ዋነኛው ነገር፡ ጸሎት እኛ ለእግዚ አብሔር የምናቀርበው ቀለል ያለ የሰው ልጆች መልካም ሥራ አለመሆኑን ነው። ከሁሉም በላይ ጸሎት የሕያው ህልውና ፍሬ ማለት ሕይወት የሚሰጠው የእግዚ አብሔር አብና የኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ውስጥ መኖር ፍሬ የሆነ ስጦታ ነው። በሮማውያን መልእክት ላይ “እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤”(ሮሜ 8፡26) ብሎ ይጽፋል፣ ሐዋርያው እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅም፤ ለመጸለይ እንፈልጋን፤ እግዚአብሔር ግን ሩቅ ነው፤ ከእግዚአብሔር ጋር ለመናገር የሚሆን ቋንቋና ቃላትም ይሁን ሐሳብ የለንም፣ እኛ ማድረግ የምንችለው ልባችን ለእርሱ በመክፈት ግዝያችንን ለእርሱ በመስጠት ከእርሱ ጋር እውነተኛ ውይይት ለማድረግ ይረዳን ዘንድ እርሱን መጠበቅ ነው፣ ሐዋርያውም ይህንን ነው የሚለን፣ ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ያለን ግላጎት ቃላት ግን ማጣት ነው፣ ይህንን መንፈስ ቅዱስ ይረዳዋል፤ መረዳት ብቻ ሳይሆን ተርጕሞ ከእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል፣ ይህ ድክመት በመንፈስ ቅዱስ ረዳነት የእውነተኛ ጸሎትና የእውነተኛ ከእግዚአብሔር ጋር ግኑኝነት መሣርያ ይሆናል፣ መንፈስ ቅዱስ ራሱ እኛ ምን እንደምንፈልግ ልንረዳ ፍላጎታችንን የሚተረጕምልንና ምን ለማለት እንደፈለግን ለእግዚአብሔር እንደ ሚያስታውቅ ተርጓሚ ነው፣
ጸሎት ስናሳርግ በሁሉ ቻይና ከሁሉ በላይ በሆነ እግዚአብሔር ፊት ስለምንቆም፤ የምናረጋግጠው ነገር ያለ እንደሆነ ድክመታችን ድህነታችንና ፍጡራን መሆናችንን ነው፣ ጸሎት የሕይወታችንና የነፍሳችን ዕለታዊ እስትንፋስ ስለሆነ፤ ከእግዚብሔር ጋር በምናደርገውን ውይይትና እርሱን በማዳመጥ እንደገሰገስነው መጠን ውስንነታቸን በይበልጥ እንረዳለን፣ ይህ ውስንነት በየዕለቱ በሚያጋጥሙን ተጨባጭ ሁኔታዎች ብቻ ሳይሆን ከጌታ ባለን ግኑኝነትም ነው በዚህም ዘወትር በእርሱ እንድንተማመና በእርሱ መጠጋት ያለን ፍላጎት ያድጋል፣ “እንዴት አድርገን መጸለይ እንደሚኖርብን አናውቅም” (ሮሜ 8፡26) የሚለውን እንረዳለን፣ ይህንን ድክመታችን የሚረዳንና ወደ እግዚአብሔር የምናቀርበውን ጸሎት የሚመራው መንፈስ ቅዱስ ኅልናችን በማብራትና ልባችንን በማሞቅ ነው፣ ለቅዱስ ጳውሎስ ጸሎት ከሁሉም በላይ መንፈስ ቅዱስ በሰብአዊነታችን የሚያደርገው ሥራ ነው፤ ድክመታችንን ተሸክሞ በቍሳዊ ነገሮች የታሰሩ ሰዎች ከመሆን ወደ መንፈሳዊ ሰዎች ይለውጠናል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው አንደና መልእክት ላይ “እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም። “ (2፡12-13) ይላል፣ መንፈስ ቅዱስ በተንኮታኮተው ሰብ አውነታችን በመኖር ይለውጠናል፤ ለእኛ ይማልዳል፤ ወደ እግዚአብሔር ከፍታም ያደርሰናል (ሮሜ 8፡26 ተመልከት)፣
ይህ መንፈስ በእርሱ ውልድነት ያገኘንበት የወልደ እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ፤ በዚሁ የመንፈስ ቅዱስ በመሀከላችን መኖር ከክርስቶስ ጋር ያለን አንድነት ይረጋግጣል፣ ክርስቶስ የእግዚብሔር አብ ልጅ ከሆነ መንፈሱ የእግዚአብሒር አብ መንፈስም ነው፤ እንዲሁም ይህ የእግዚአብሔር አብና የክርስቶስ የሆነ መንፈስ፤ በእግዚብሔር ልጅና በሰው ልጅ የሆነው ጌታ የሰው ልጅ መንፈስም ይሆናል ስለዚህ ለእኛም ይመለከታል፣ ይህንን አለመቀበል የእግዚአብሔር አብ መንፈስ በልጁ ምሥጢረ ሥጋዌ ብቻ ተገለጠ እንደማለት ነው፤ ሆኖም ግን ይህ የእግዚአብሔር አብ መንፈስ በኢየሱስ ክርስቶስ ህይወትና ተግባርም ማለት በእና መሃከል የኖረ የተሰቀለ የሞተና ከሞት የተነሣ ይገለጣል፣ ሐዋርያው ይህንን ለማስታወስ “በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር። ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።” (1ቆሮ 12፡3) በማለት ያሳስበናል፣ ስለዚህ መንፈስ የምንኖር እኛ አይደለንም ነገር ግን ክርስቶስ በእኛ ይኖራል” (ገላ 2፡2) እስከማለት ልባችንን ወደ ኢየሱስ ይመራል፣ በአዲሱ ትምህርተ ክርስቶስ ምሥጢራት በሚመለክት ቅዱስ አምብሮዝዮስ ስለ ቅዱስ ቍርባን የሚለውን ይደግማል “በመንፈስ የሚሰክር በክርስቶስ የተመሠረተ ነው” ይላል፣ (ቍ 5.3.17)፣
በክርስትያናዊ ሕይወታችን የዓለም መንፈስ ሳይሆን የክርስቶስ መንፈስን እንደ የሁሉ ተግባራችን ዋና ምንጭ እንዲሆን የተውነው እንደሆነ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ሶስት ነገሮች ማብራራት እወዳለሁ። ከሁሉም በላይ በመንፈስ በታነጸ ጸሎት ማንኛው የፍርኃትና የባርነት አቋምን ጥለን ከዛ ባሻገር እንሄዳለን እንዲህ ባለ ሁኔታም፤ በእውነተኛ የእግዚአብሔር ልጆች ነጻነት እንኖራለን፣ በየዕለቱ ጥልቅ በሆነና በቀጣይ በሚያድግ ግኑኝነት ከክርስቶስ ጋር አንድ ለመሆን ጸሎት ያላሳረግን እንድሆነ፤ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮማውያን በጻፈው መልእክት “የምንፈልገውን መልካም ነገር ለማድረግ ያቅተናልና የማንፈልገውን መጥፎ ነገር እናደርጋለን” (7፡19) ብሎ በገለጠው ሁኔታ እንገኛለን፣ ይህም በአባታችን አዳም ኃጢአት ሳቢያ የመጣው የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የመራቅ ሁኔታ፤ እና የህልውናችን ነጻነት መደምሰስ መግለጫ ነው፣ መልካም ሥራን ለመሥራት እንመኛለን ሆኖም ግን አናደርገውም ይልቅስ ለማድረግ የማንፈልገው መጥፎ ሥራን እንሠራለን፣ ሐዋርያው ከዚህ ሁኔታ ነጻ ሊያወጣን የሚችል ፍላጎታችን ወይንም ሕግ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ሊያስረዳን ይፈልጋል፣ ስለዚህ “የጌታ መንፈስ ባለው ነጻነት አለ” (2ቆሮ 3፡17)፤ በጸሎት ከመንፈስ የተሰጠን እውነተኛ ነጻነትን እናጣጥማለን፣ ይህም ከመጥፎ ነገርና ከኃጢአት ነጻ ያወጣናል ለመልካም ሥራ ለሕይወት ለእግዚአብሔር እንድንኖርም ያደርገናል፣
በዕለታዊ ሕይወታችን የክርስቶስ መንፈስ በእኛ ላይ እንዲሠራ የፈቅድንለት እንደሆነ ከዛ የሚፈልቀው ሁለተኛው ነገር ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግኑኝነት ጥልቅ ይሆናል፤ ይህም በማንም ነገር ወይም ሁኔታ አይነካም፣ ስለዚህ ጸሎት ስናሳርግ ከፈተናና ከስቃይ እንዳልተላቀቅን እንረዳ፤ ሆኖም ግን ከእነርሱ ጋር ሳለን ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነን በክብሩ እንድምንሳተፍ ተስፋ በማድረግ ስቃዩንም እንሳተፋለን (ሮሜ 8፡17)፣ ብዙውን ጊዜ በጸሎታችን እግዚአብሔርን ከሥጋዊና ከመንፈሳዊ ክፋት ነጻ እንዲያወጣን እንለምናለን፤ በኃይል መተማመንም እንዳደርገዋልን፣ በመጨረሻም ጸሎታችን ያልሰማን ሆኖ ይሰማናል፤ በዚህም ተስፋ እንደመቍረጥ ይሰማናልና ጸንተን ከመጸለይ ልንቆም እንችላለን፣ ቅዱስ ጳውሎስ “ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።” (ሮሜ 8፡18) እንደሚለው እንደእውነቱ ከሆነ በእግዚአብሔር የማይሰማ ጸሎት እንደሌለና ካለማቋረጥና በእምነት የሚደረግ ጸሎት እንደሚሰማ እንረዳለን፣ ጸሎት ከፈተናና ከሥቃይ አያላቀንም፤ ለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ “በልባቻን እያቃተትን የሰውነታችን ድህነት እና የእግዚአብሔር ልጆች መሆንን እንጠብቃለን” ይላል፣ እንዲሁም ጸሎት ከሥቃይ አያላቀንም ሆኖም ግን ልክ በኢየስይስ እንደነበረው የመተማመን ኃይል በመልበስ በአዲስ ኃይል እንድንኖራትና እንድንጋፈጣት ይፈቅድልናል፣ ይህም በዕብራውያን መል እክት እንደተጻፈው “እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤”(5፡7) እግዚአብሔር አብ ለልጁ ለጥሪውና ለእንባው የሰጠው መልስ ከሥቃይ ከመስቀልና ከሞት መዳንን አይደለም፤ ግን ከዚህ የላቀና የጠለቀ መልስ ነበር፤ በመስቀልና በሞት አማካኝነት የልጁ ትንሣኤ በአዲስ ሕይወት መለሰለት፣ በመንፈስ ቅዱስ የተሰላሰለ ጸሎት ዛሬ ለእኛም ለልጁ እንደመለሰ ለእኛም ሊመልስ በሚችል እግዚአብሔር ሙሉ ተስፋና መተማመን በማኖር ዕለታዊ የሕይወታችን ጉዞን ከፈተናውና ከሥቃዩ ጋር ልንኖረው እንድምንችል ያስተምረናል፣
በሶስተኛ ደረጃ የአማኙ ጸሎት ለሰው ልጅና ለመላው ፍጥረ ክፍት እንድንሆን ያደርገናል፤ ይህንም ቅ.ጳውሎስ እንደሚለው “የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።” (ሮሜ 8፡19)፣ ይህ የሚያመልከተው ነገር ቢኖር በክርስቶስ መንፈስ የተደገፈ ጸሎት በገዛ ራሳችን ተዘግተን እንድንቀር አያደርገንም፤ ለገዛ ራሳችን ብቻ የሚደረግ ጸሎት አይደለም፤ ነገር ግን የሌሎች ሥቃዮችን ለመካፈል ክፍት እንድንሆን ያደርገናል፣ ስለሌሎች የመማጠን ጸሎት ይሆናል፣ በዚህም ከእኔነት ነጻ መሆን ለመላው ፍጥረት የተስፋ ዕድል ይከፍታል፤ ይህም “በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም” ሮሜ 5፡5 ለሚለው መግለጫ ነው፣ ይህ ለግል ብቻ ላልተደረገ ነገር ግን ለሌሎች ክፍት የሆነ ጸሎት እውነተኛ ምልክት ናት፣እንዲህ ባለ መንገድ ነጻ ያወጣኛል፣ እንዲሁም ለዓለም ደህንነት ይረዳል፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ ቅዱስ ጳውሎስ በጸሎታችን በሙሉ ልባችንና በመላው ህልውናችን ለእግዚአብሔር እንድንገዛ ሊገለጥ በማይቻለው መቃተት በውስጣችን ሆኖ ለሚጸልየው ለመንፈስ ቅዱስ ሥራ ክፍት መሆን እንዳለብን ያስተምረናል፣ የክርስቶስ መንፈስ እውነተኛ ውሳጣዊ ነጻነትን በመስጠት ከኑሮ ፈተናዎች ጋር እየተጋፈጡ መኖርን እያስተማረ፤ ብቻችን አለመሆናችንን እያረጋገጠልን፤ “በመቃተትና በምጥ” ለሚኖረው ተፈጥሮና ሰብአውነት ራእይ ኅልናችን እየከፈተ፤ ለደካማው ጸሎታችን ኃይል፤ ለጨለመው ጸሎታችን ብርሃን፤ ለደረቀው ጸሎታችን እሳት ይሆነዋል፤ እግዚአብሔር ይስጥልን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.