2012-05-16 14:59:34

ከዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ ጀርባ (ሥር) የእሴቶችና የእምነት ቀውስ


እ.ኤ.አ. በዚህ በተገባው የማርያም ወር ተብሎ የሚለየው ግንቦት ወር የተለያዩ ማርያማዊ መንፈሳዊነት የሚያነቃቁና የሚያጎሉ ጅማሬዎች በተለያዩ አገሮች በሚገኙት ሰበካዎች ቁምስናዎችና ምእመናን እየተረጋገጠ መሆኑ ሲታወቅ፣ ይኸው እነዚህ የማርያማዊ መንፈሳዊነት የሚያነቃቁ ጅማሬዎች በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. RealAudioMP3 ውሳኔ መሠረት እ.አ.አ. ከጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ሊከበር እየተቃረበ ባለው በእምነት ዓመት ላይ እይታቸው ያኖሩ መሆናቸው አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊሲከላ እ.ኤ.አ. ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ዓመታዊ የቅድስት ድንግል ማርያም ዘፋጢማ ምክንያት የነጋዲት ቅድስት ድንግል ማርያም ዘፋጢማ ቅዱስ ምስልና የብፁዓን ፍራንቸስኮና ጃቺንታ ቅዱሳት ትሩፋት ባስተናገደው ሮማ በሚገኘው በምልእተ ጸጋ ቤተ ክርስትያን መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት እንደገለጡ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
ብፁዕነታቸው ከመሥዋዕተ ቅዳሴ ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ እጅግ አሳሳቢው በዓለማችን የሚታየው የእምነት ቀውስ ነው፣ ይኸውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንደገለጡትም የእምነት ቀውስ እጅግ የከፋ ለተለያዩ ዘርፈ ብዙ ቀውሶች የሚያጋልጥም ነው። የእምነት ቀውስ በሰው ዘር ዘንድ ጥልቅ አለ መረጋጋት እያስከተለ መሆኑ ጠቅሰው፣ ይኽ ዓይነት መቃወስ በዚሁ ዘመን በሚኖረው ሰው ዘንድ የሚታዩት ወደ ተለያዩ ዘርፈ ብዙ ቀውሶች እርሱም ግዴለሽነት ግለኛነት በዚህ ብቻ ሳይታጠርም አልቦ ሥነ ምግባርና ግብረ ገብ መመዘኛ ምክንያት ለማኅበራዊው ተከትሎ ግብረ ገብና ሥነ ምግባር ሥርዓትና ስሜት እምቢተኝነት እያስፋፋ ይኸው በአሁኑ ሰዓት ተከስቶ ላለው ዓለም አቀፍ ብሎም ብሔራዊ አቀፍ የኤኮኖሚና የቁጠባ ቀውስ አጋልጦ ይገኛል።
ይኸንን ሁሉ እግምት ውስጥ በማስገባትም የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ዓላማና ሂደት በትክክል የሚያተኩርባቸው ማእከላዊ ጉዳዮች፣ ማኅበረ ክርስትያን እንደ አማኝ መጠን ያለው ኃላፊነት እውቅና ግንዛቤ ዳግም እንዲሰጥበት፣ ስለዚህ እምነት በማኅበረ ክርስትያን ዳግም ኅያው ማድረግ ቀጥሎም ከእምነት ርቀው የተቀበሉትን እምነት ትተው እምነት ግድ የማይሰጠው ወደ መሆን ተለውጠው ክርስትያን ነኝ ነገር ግን ቤተ ክርስትያን አልሄድም ወይንም ኢፈሊጣዊነት እርሱም ስለ እግዚአብሔር ኅላዌም ይሁን ከምድራዊ ሕይወት በኋላ ሌላ ሕይወት መኖሩ ለማወቅ አይቻልም ወደ ሚለው አመለካከት የተለወጡትን በሦስተኛ ደረጃ እነዚህ የተጠቀሱት ሁለት ክፍሎችን በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል፣ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት ቀርቦ የእግዚአብሔር ፍቅር በመመስከር መወያየት የተሰኙ መሆናቸው አብራርተዋል።
አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በውስጣችን የሚሠራ የእግዚአብሔር ጸጋ ተግባር መሆኑ መገንዘብ ይኖርብናል። ስለዚህ እኛ ክርስትያኖች ተብለን ስንጠራም እምነት የምታስተላልፍልን ቤተ ክርስትያን ስላለች ነው። በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ሁሉ እንደየ ጥሪው መሳተፍ ይኖርበታል። ክርስትያን አለ ቤተ ክርስትያን የሚለው አነጋገር ባዶና ሥነ አመክንዮ አልቦ አነጋገር ነው።
ብዙውን ጊዜ ስለ ማርያም ዘፋጢማ ስንናገር ስለ እምነትና የእምነት ጸጋ...ወዘተ ሳይሆን የማርያም ዘፋጢማ ግልጸት ላይ በማተኮር፣ የዚያ ግልጸት ምሥጢር ለማወቅ ባለው ጉጉት የተነቃቃ ነው፣ በወንጌል እንደተመለከተውም የመጀመሪያዎች የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃላቶች፣ ተለወጡ በወንጌልም እመኑ የሚሉት ናቸው፣ ስለዚህ ከግልጸት ማርያም ዘፋጢማ የሚገለጠው መልእክት በተሰጠህ ጥሪ እግዚአብሔርን ማገልገል፣ ለተቀበልከው የክርስትና እምነት የላቀ ግንዛቤ ኖሮህ በቃልና በሕይወት በተሸኘው አኗኗር አብሣሪ እንድትሆን የሚያሳስብ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.