2012-05-16 15:02:48

ሱዳን፦ ውጥረትና ተፈናቃዮች


በሱዳንና በደቡብ ሱዳን መካከል ተከስቶ ያለው ውጥረት እጅግ አሳሳቢ መሆኑ በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት፣ የሱዳን መንግሥት በአገሩ የሚኖሩት የደቡብ ሱዳን ዜጎች RealAudioMP3 አለ መኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ናቸው በሚል ክስ ወደ አገራቸው ደቡብ ሱዳን እያባረራቸው መሆኑ ሲገለጥ፣ እ.ኤ.አ. ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ሊባረሩ ናቸው ከሚባሉት ውስጥ የመጀመሪያዎቹ 164 የደቡብ ሱዳን ዜጎች ጁባ መግባታቸው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው ድርጅት ባወጣው መግለጫ በማስታወቅ አክሎ፣ በሚቀጥሉት ቀናት 12 ሺህ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ተገደው ሱዳንን ለቀው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ በሱዳን መንግሥት ትእዛዝ እንደተሰጣቸውም ያመለክታል።
እ.ኤ.አ. ከ 2011 ዓ.ም. የደቡብ ሱዳን ሉኣላዊነት መረጋገጥ ወዲሁ በሱዳን የሚኖሩ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ከተቀጠሩበት የሙያ ዘርፍና ሥራ የተባረሩት በብዙ ሺሕ የሚገመቱት የደቡብ ሱዳን ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ በሱዳን መንግሥት መገደዳቸው የገለጠው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ተንከባካቢ ማኅበር አክሎ እስከ አሁን ድረስ ውጥረት ከሚታይበት የሁለቱ አገሮች አዋሳኝ ክልል ከደቡብ ኮርዶፋ የተፈናቀሉት ስደተኞችና ከሱዳን የተባረሩት የደቡብ ሱዳን ተፈናቅዮች ዜጎች ደቡብ ሱዳን የገቡት ብዛት እጅግ ከፍ እያለ መሆኑ ጠቅሶ በጠቅላላ 100 ሺሕ እንደሚገመቱም አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.