2012-05-15 15:39:27

ሐዋርያዊ ጉብኝት ር ሊ ጳጳሳት በነዲክት በተስኮና ክፍለ ሀገር ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ትናትና ሰንበት በመካከለኛው ጣልያን በቶስካና ክልል በአረጾ ላ ቨርና እና ሳን ሰፖልኮሮ የአንድ ቀነ ሐዋርያዊ ጉብኝት አካሄደው በሰላም ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው ተመልሰዋል።

በነዲክትስ 16ኛ ትናትና ረፋድ ላይ በሮማ ሰዓት አቁጣጠር ዘጠኝ ሰዓት ላይ አረጾ ሲገቡ የክልሉ ካርዲናላት ጳጳሳት ካህናት በሶስት ሺ የሚገመቱ ምእመናን እና የጣልያን መንግስት ጠቃላይ ሚኒስትር ማርዮ ሞንቲ ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል።

ቅድስነቶም በሆሊኮፕተር አረጾ ሲገቡ የከተማይቱ አብያተ ክርስትያናት ደወሎች ተድውለዋል ህዝቡ በጭበጨባና በደስታ በደማቅ አኳኀን ተቀብሎዋቸዋል።

የአረጾ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሪካርዶ ፎንታና የአንኳን ደህና መጡ ንግግር አድርገዋል። ቅድስነታቸው በክልሉ ሐዋያዊ ጉብኝት ማድረጋቸው አመስግነው የክልሉ ምአመናን እና ህዝብ የቅዱስ ጰጥሮስ ወኪል በመሃአከላችን በመገኘትዎ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል ብለዋል።

ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሪካርዶ ፎንታና በወቅቱ ጣልያን ላይ የተከሰተው ኤኮኖምያዊ ቀውስ በማስመልከት የሰው ልጅ በነፍስ እና በስጋ የቆመ ነው ለነፍስ የሐቅ ምግብ ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ ሐቅነት ምግብ ታገኛለች ስጋ ግን ማተርያላዊ የሆኑ ነገሮች ለምሳሌ ስራ ያስፈልጋታል በክልላችን ከአራት ሰቦች አንድ ቤተ ሰብ ስራ ስለሌለው ሕይወት ከባድ እየሆነ መምጣቱ ለቅድስነታቸው ገልጾውላቸዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ታልያን መንፈሳዊ እና ግብረ ገብነታው ተሐድሶ መንገድ መልሳ መያዝ እንዳለባት ጠቅሰው ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ለሽግር ከተጋለጡ ማህበረ ሰቦች ጋር ለመትባበር ዝግጁ መሆናው ገልጠዋል።

ማሕበራዊ ሕይወት የሚሻሻለው የሰው ልጅ መንፈሳዊ እና ሞራላዊ ተሐድሶ ሲያደርግ እና ከስስት ሲርቅ እንደሆነም ቅድስነታቸው በተጨማሪ አመልክተዋል።

ነፍስ ወከፍ ሰው የእግዚአብሔር ጥሪ በመቀበል ለማሕበረ ሰብ መልካም ስራ ሊሰራ እንደሚችልም አያይዘው አስገንዝበዋል ።

በነዲክት 16ኛ የተስኮና ሀገረ ስብከት በመካከለኛው ዘመን ስራ እና ነፃነት ፍለጋ ወድ ክልሉ ለገቡ ማበረ ሰቦች ከላላ መስጠቱ ታሪክ ላይ ተተንተርሰው አስገንዝበዋል። እሴቱ እና መልካም ባህሉ የታቀበ እንዲሆንም አሳስበዋል።

ሀገረ ስብከቱ የታላቅ ቅዱሳን መካን መሆኑ አመልክተው ፡ በአራተኛ ሚእተ ዓመት ይኖር የነበረ የአረጾ ከተማ ጠባቂ ቅዱስ ዶናቶ በቅዱስ ዶናቶ ካተድራል ውስጥ የተቀበረ ብጹዕ ግረጎርዮ አስረኛን አስታውሰዋል።

መጻኢ ግዜ በተስፋ ለመመልከት ያለፈውን ታሪክ ማስታወስ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ዱካ መከተል እንደሚያሻም ቅድስነታቸው ገልጸዋል።

ለመጀመርያ ግዜ በቶስኮና ክልል ሐዋርያዊ ጉብኝት የደረጉ በነዲክት 16ኛ ፕራቶ ላይ በሚገኘው ዓቢይ ፓርክ በብጹዓን ካርዲናላት እና ጳጳሳት ተሸንተው መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል። በነዲክት 16ኛ መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ግዜ ባሰሙት ስብከት ከ500 መቶ ዓመታት በፊት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በዚሁ ክልል ሐዋያዊ ጉብኝት ማካሄዳቸው ተዘግበዋል።

ይሁን እና ቅድስነታቸው ከአረጾ ጳጳሳት በወል ለምሳ መቀመጣቸዋ ይታወቃል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆነ የአረጾ ከተማ ከንቲባ ጁሰፐ ፋንፋኒ ቅድስነታቸው የቸሩት ቃል እና ለሰጡት ትምህርት በምእመናን ስም ለበነዲት 16ኛ ማመስገናቸው ታውቆዋል።የአረጾ ከተማ ወጣቶች የበነዲክት 16ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት ዋዜማ ቅዳሜ ማታ ተሰብሰበው ሲጸልዩ ማምሸታቸው እና ማደራቸው ይታወቃል።

ሐዋርያዊ ጉብኝቱ በአጠቃላይ ለሀገረ ስብከቱ ምእመናን በተለይ ለወጣቶች ዓቢ ተስፋ እና ሞራል የሰጠ መኖሩ ተዘገበዋል።ቅድስነታቸው አረጾ ላይ ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል አምስገነዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ከአረጾ ከተማ ሌላ የከተማይቱ ተጓራባች የሆኑትን ላ ቨርና ሳን ሰፖልክሮን መገብኘታቸው የሚታወስ ሲሆን በ ላቨርና የሚገኘው የንዑሳን አኀው ካፑቺኒ ገዳም ጐብኝተዋል ። ከገዳሙ መነኮሳን ጋር ተገናኝተው በጋራ ጸልየዋል።

የንዑሳን አኀው ካፑቺኒ አባል አኀው ሚኪኤለ ፒኒ እንደገለጡት የቅድስነናታቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት ክርስትናዊ ሕይወት እና አገልግሎት እግዚአብሔር የመሰከረ እና ያረጋገጠ ሀዋርያዊ ጉብኝት መኖሩ ገልጠዋል። ቅድስነታቸው ከላ ቨርና ወደ ሳን ሰፖልክሮ የዘለቁ ሲሆን በዚሁ ቦታ በሚገኘው ቶረ ዲ በርታ በተባለ አደባባይ ከህዝበ ክርስትያን ጋር ተገናኝተዋል።

ሳን ሰፖልክሮ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ በ1224 እኤአ ቅንዋት ተቀበለበት እና ሁለንትናው ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠበት ገዳም እንደሆነ ይታወቃል።

ይህ ሳን ሰፖልክሮ የተባለ መካን ከኢየሩሳሌም በመጡ ኤጂድዮ እና አርካኖ በተባሉ ሁለት ቅዱሳን ከአንድ ሺ ዓመታት በፊት የተቁረቁረ መሆኑ ይታወቃል።

ጭር ያለ ገዳሙ እግዚአብሔር የሚናገርበት መካን እንደሆነ ቅድስነታቸው ከመነኮሳኑ ጋር በተገናኙበት ግዜ ገልጠዋል።የሳን ሰፖክልሮ ቆመስ ዶን አልበርቶ ጋሎሪኒ ሳን ሰፖልክሮ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት በማሰብ ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በመጡ ሁለት ቅዱሳን ስለ ተቁረቀረች የኢየሩሳሌም ተምሳሌት መሆንዋጠቅሰው በየቅድስነታቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት በእጅጉ መደሰታቸው አስገንዝበዋል። ክርስትና ፍትሕ እና ሰላም በማስመልከት በነዲክት 16ኛ ያደረጉት ንግግርም ማህበረ ሰቡ እንደረካ ዶን አለበርቶ ጋሎሪኒ ገልጠዋል።የትንሽዋ ሳን ሰፖልክሮ ከተማ ከንቲባ ሐዋርያዊ ጉብኝቱ ሲቪል ማሕበረ ሰቡ ያነቃቃ መንፈሳዊ እና እምነተ ክርስትና የሚያረጋጥ ህዝቡ በጉጉት የጠበቀው መኖቱ ገልጸዋል። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት በቶስኮና ክፍለ ሀገር በአረጾ ላ ቨርና እና ሳን ሰፖልክሮ ያደረጉት የአንድ ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠቃለው አምሻቸው ወደ በሰላ ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው ተመልሰዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.