2012-05-11 15:06:02

የአረብ አገሮች ክርስትያኖች ሁኔታ ከአረብ አገሮች ጸደይ በኋላ


የኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶችን የሚያቅፈው የመላ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት “የአረብ አገሮች ማኅበረ ክርስትያን ከአረብ አገሮች ጸደይ በኋላ” በሚል ርእስ ሥር RealAudioMP3 ያነቃቃው ከትላንትና በስትያ የተለያዩ የሃይማኖትና የፖለቲካ ሊቃውንት ያሰባሰበ ዓወደ ጥናት በብራሰልስ መካሄዱ ሲገለጥ፣ በተካሄደው ዓወደ ጥናት ንግግር ያሰሙት በቅድስት መሬት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስያን ንብረትና ቅዱሳት ሥፍራ አቃቢ አባ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ ከቫቲካ ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዓረብ አገሮች ለ 40 ዓመታት የተኖረው የአልቦ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ሁኔታ እምቢ በቃ በማለት የተቀጣጠለው በመቀጠ ላይ ያለው ሕዝባዊ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጸደይ ተስፋ ያለው ቢሆንም በትክክል ካልተመራ አሉታዊ ሆኖ ሊገኝ ይችላል። ስለዚህ አለ ምንም ቅድመ ፍርድ ያለው ሁኔታ በሁሉም አቅጣጫ አወንታዊ እንዲሆን የሁሉም ትብብርና ድጋፍ ወሳኝ ነው ብለዋል።
በፖለቲካው መስክ ብቻ ሳይሆን በአረብ አገሮች የሚገኙት የተለያዩ ሃይማኖቶች ለጋራ ውይይት እንዲተጉ የሚጠይቅ ነው። የሃይማኖቶች የጋራው ውይይት ለዚያ ክልል ሰላም መሠረት ነው። የአረብ አገሮች ዜጋ አለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት በእኩልነት መተዳዳር ይገባዋል። በመክከለኛው ምስራቅ ለማኅበረ ክርስትያን የማያመች ሁኔታ የሚከሰት ቢሆንም የሃይማኖቶች የጋራው ውይይት የሚያነቃቁ ተግባሮች እየተረጋገጠ ነው። በማኅበራዊ መስክ አድልዎ አልባ የሁሉም ተሳታፊነት ዋስትና ማረጋገጥ አንገብጋቢ መሆኑ ገልጠው፣ የሚታየው ወቅታዊው ችግር በመመልከት ከለውጥ በፊት ሕይወታችን ዋስትና ነበረው በማለት ከመተከዝና ከማልቀስ ወይንም ከለውጥ በኋላ ያለው ሁኔታ በጣም ጥሩ ነው ብሎ አለ ተገቢ የመተቸት ብቃት በግል ጥቅም ተገፋፍቶ ከመናገር ተቆጥበን የተረጋገጠው ለውጥ ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ የሁሉም እኩልነት የሚረያጋገጥ እንዲሆን የሁሉም ትብብር ያስፈልጋል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.