2012-05-11 15:01:38

ዓውደ ጥናት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” ፦ ሥነ ጥበብ ውበትና ከነገር ባሻገር


የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” በሚል ርእስ የተመራ የዓለማችን አበይት እና አንገብጋቢ ርእሰ ጉዳዮች በማስደገፍ በአማኞች እና በኢአማኒያን መካከል የሚሰጠው መልስ የሚያወያይ እምነት እና ምርምር የማይነጣጠሉ የሚደጋገፉ መሆናቸው RealAudioMP3 ለማረጋገጥ ዓልሞ ያነቃቃው፣ እምነት እና አልቦ እምነት በአንድ አንገብጋቢ ርእስ ሥር አገናኝቶ የሚያወያይ በኢጣሊያ ቦሎኛ ከተማ ያስጀመረው መርሃ ግብር በፓሪስ በቡካሬስት በፊረንዘ በሮማና በቲራና እ.ኤ.አ. በ2012 ዓ.ም ግንቦት ወር ማብቅያ በኢጣሊያ ፓለርሞ ከተማ “የሕጋዊነት ባህልና ኅብረሃይማኖተኛ ኅብረተሰብ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ ዓውደ ጥናት አካሂዶ ይኸው ወደ ስፐይን በማቅናት እ.ኤ.አ. ከግንቦት 17 ቀን እስከ ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም. በባርቸሎና ከተማ “ሥነ ጥበብ፣ ውበትና ከነገር ባሻገር” በሚል ርእስ ሥር እንደሚካሄድ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ከትላትና በስትያ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ ስለዚሁ እቅድ በማስመልከት የባርቸሎና ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ልዊስ ማርቲነዝ ሲስታች ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ምሁራን እና የሥነ ጥበብ አካላት የሚያወያይ የስፐይን መናብርተ ጥበብ’ የሥነ ጥበብ ተቋሞች ሊቃውንት የሚያገናኝ ሆኖ በቅድስት ቤተ ሰብ ባሲሊካ የሚጠቃለል፣ ሥነ ግጥም ሥነ ሙዚቃ ሥነ ጥበብ የማስታወቂያ ጥሪ ሳይሆን በውስጡ ያለው ተመስጦና መንፈሳዊነት መሆኑ የሚገለጥበት ጥልቅ ስሜት በሌላ አገላለጥም ዳር ማዶነት ጠቋሚ ነው። ዓውደ ጥናቱ ዳር ማዶነት በተለያየ ዘርፉ የሚጎላበት ነው። ስለ ሥነ ጥበብና ስለ እግዚአብሔር መናገር ብቻ ሳይሆን ኢአማንያን የሥነ ጥበብ ሊቃውንት በማሳተፍም በሥነ ጥበብና በኢእግዚአብሔርነት አመለካከት አለ የሚሉትን ግኑኝነት በማጤን መልስ ለማቅረብ አማንያን የሚያነቃቃ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.