2012-05-11 14:59:34

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የክርስቶስ ግልጽነትና ቁጥብነት የተካኑ ካህናት


ትላትና ጧት ሮማ የሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ጳጳሳዊ የስፐይን ተቋም 50ኛው ዓመት ምሥረታና የስፐይን የሰበካ ካህናት ጠባቂ በቅርቡ የቤተ ክርስትያን ሊቅነት ለሚታውጅለት ዓመታዊ የቅዱስ ዮሐንስ ዘ አቪላ ሊጡርጊያዊ በዓል ምክንያት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተቋሙ አለቆችና RealAudioMP3 የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ተቀብለው ግልጽ፣ በሕይወት የሚንጸባረቅ ስለ ክርስቶስ ምስክር በሚል ርእስ ሥር ሥልጣናዊ ምዕዳን መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ግልጽ የክርስቶስ ምስክር ሲባል በቃል እና በሕይወት የሚኖር ምስክርነት ማለት መሆኑ በማብራራት፣ ቅዱሳት ካህናት፣ ክርስቶስን ለሌሎች ለማድረስ የሚችሉ፣ ስለዚህ ክርስቶስ ካለህ ብቻ ነው ወደ ለሌሎች እርሱን ማድረስ የሚቻለው፣ የሌለህን ለሌሎች ለማካፈል እንዴት ይቻላልን ካሉ በኋላ በማድሪዲ በተካሄደው ዓለም አቅፍ የወጣቶች ቀን ቅዱስ አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ ዘ አቪላ የቤተ ክርስትያን ሊቅነት እንደሚታወጅለት ቀደም በማረግ ገልጠው እንደነበርም በሰጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን በማስታወስምዳግም አረጋግጠው፣ የካህናትና የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ሕንጸት በቤት ክርስትያን ቅድሚያ የሚሰጠው ኃላፊነት ነው። ጳጳሳዊ የስፐይን ዘረአ ክህነት ተማሪዎች ተቋም፣ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደ የእግዚአብሔር ፈቃድና ፍላጎት ለማገልገል የሚሰዉ የማያወላውል ቁርጥ ፈቃድ የሚያስቀድሙ በላቀ ቅድመ ዝግጅትና ሕንጸት አማካኝነት የተሰናዱ በተቀደሰ ሕይወት በመኖር የእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ለተጠራበት ቅድስና የሚያገለግሉ የሚዘጋጁበት ተቋም ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅድሚያ በጥልቅ እና በጋለ መንፈስ በሙላት በሚፈጸም ጸሎት አማካኝነት ካላገኘነው፣ ለሌሎች ክርስቶስን ለማቅረብም ይሁን በድኾችና በስቃይ ላይ በሚገኙት ጭምር የሚገለጠው ክርስቶስ ለይቶ ለማወቅና ለማግኘት አዳጋች ነው። ስለዚህ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በቅድሚያ ግላዊ ግኑኝነት ማነቃቃት፣ ብሎም ይኸንን ግኑኝነት በማኅበር ደረጃ በመኖር የተገናኘነው ክርስቶስ ማበሰር፣ ማክበርና ለሌሎች ማቅረብ ይጠበቅብናል። ጥልቅ የክህነት መንፈሳዊነት፣ የመልካም እረኛ ግልጽና ኅያው መስካሪ መሆን ማለት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በቅዱስ ዮሐንስ ዘአቪላ አብነትና የተወደሰ የኖረው ክብር አማካኝነት ተበረታታችሁ የተቀበላችሁትን ምሥጢረ ክህነት ልዩ በሚያደረገው በቀናተኛ መንፈስ ለመኖር እድትችሉ፣ የእርሱን የተስተካከለ ቁጡብና ለካህናት እናት ለቅድስት ድንግል ማርያም የኖረው አክብሮት ፍቅርማ ቅርበት በመኖር እንዲመሰክሩትም አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.