2012-05-08 09:33:20

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “የማስተዋል ብቃት እምነትና ፍቅር”


ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምያርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ በመቀጠል ይኸው እ.ኤ.አ. ባለፈው ግንቦት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሮማ በሚገኘው ጀመሊ RealAudioMP3 አቢይ ሀኪም ቤት የዛሬ 50 ዓመት በፊት የተመሠረተው ቅዱስ ልበ ኢየሱስ የሥነ ህክምናና የሥነ ቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት መስጫ ቅዱስ ልብ በተሰየመው መንበረ ጥበብ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማከናወን ለሀኪም ቤቱ ሠራተኞች የሥነ ህክምና ሊቃውን የህክምና ባለ ሙያዎች እና ተማሪዎች “የማስተዋል ብቃት እምነትና ፍቅር” በሚል ርእስ ሥር፣ ባሰሙት ሥልጣናዊ አስተምህሮ ሥነ ምርምር፣ ሥነ እውቀት አለ ፍቅር ልኡል ክብሩን እንደሚያጣ በማብራራት፣ ፍቅር ብቻ ነው ለሥነ እውቀት ሰብአዊነት ዋስትና በማለት የሥነ ህክምናና የሥነ ቀዶ ጥገና የህክምና አገልግሎት ጥልቅና ጽኑ የላቀው ክብሩ በመለየት በዚሁ ክብር ተመርቶ መስፋፋት እንዳለበት አሳስበዋል።
በዚህ ባለፈው እሁድ አባ ሎምባርዲ ባቀረቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ የዘመናችን ሰውና ሥልጣኔ የሕይወት የፍጥረት ሁሉ መሠረታዊ ትርጉም አድማስ ማእከል ከማድረግ ይቅል ፍጡት የግብረአዊ ሙያ ውጤት ግድ የሚል በመሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ክርስትና የቃልና የቀልብ ሃይማኖት እርሱም በሰብአዊ ፍጥረት ዘንድ ያለው አእምሮአዊ የማስተዋል ብቃትና ቀልብ እማኔ እንዳለ በመግለጥ፣ ስለዚህ ክርስትና ተጨባጭ ያልሆነ መሠረተ ቢስ ማለትም ኢምክንያታዊ ሳይሆን፣ የሁሉም ፍጥረት አናሥርና ትርጉም መነሻውና ዓለማው የሆነው ምክንያታዊ-አስተዋይ ፈጣሪ ለይቶ የሚመለከት ነው። ስለዚህ የእምነት እና የሥነ ምርምር (ቀልብ) ውህደት ለሥነ ምርምርና ለእምነት ውጤታማነት ዋስትና ነው። የሁለቱም መለያየት ወደ ሥነ ምግባር ድኽነት የሚዳርግ ሆኖ በግብረአዊ ሙያ ተቻይ የሆነውን ሁሉ በግብረ ገብ ሚዛን አማካኝነት ትክክልና መልካም መሆኑ ለመለየት የሚደረገው አስተዋይ ግምገማ እንዳይኖር ያደርጋል፣ ስለዚህ በግብረአዊ ሙያ የሚቻለው፣ በግብረ ገብ ሚዛን ትክክለኛና መልካም መሆኑ ሲገመገም ለሰው ዘር ጥቅም ይውላል በማለት ቅዱስ አባታችን በሰጡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ ያሰመሩበት መሠረታዊ ሃሳብ በማስታወም አክለውም ሥነ ህክምናን ሥነ እውቀት በቀጥታ ለሰው ዘር ጥበቃና ፍወሳ ከሚለው ዓላማ ጋር የተቆራኙ ናቸው። ስለዚህ ሙያው በፍቅር የተመራ መሆን እንዳለበት መሠረታዊ ዓላማቸው በኑባሬ ያረጋግጠዋል። ለሰው ልጅ በጠቅላላ ለሰብአዊ ጥቅም ያቀና በመሆኑ የሥነ ህክምና ሙያ ጥሪ ነው። በአገልግሎት መንፍስ የሚከናወን እውቀትና ልብን የሚያጣምር የእግዚአብሔር መኃሪነትና ሞትን በትንሣኤ ድል ማድረጉን የሚያረጋግጥ ምልክት እምደሆነም ቅዱስ አባታችን የሥነ ህክምናና የሥነ ቀዶ ጥገና ህክምና የላቀውና ተገቢው ክብሩን በጥልቀት እንዳብራሩ አባ ሎምባርዲ ጠቅሰው ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.